am_ulb/19-PSA.usfm

5038 lines
327 KiB
Plaintext

\id PSA
\ide UTF-8
\h መጽሐፈ መዝሙር
\toc1 መጽሐፈ መዝሙር
\toc2 መጽሐፈ መዝሙር
\toc3 psa
\mt መጽሐፈ መዝሙር
\s5
\c 1
\p
\v 1 በክፉዎች ምክር የማይሄድ በኃጢአተኞች መንገድ የማይቆም በፌዘኞች ወንበር የማይቀመጥ ምስጉን ነው፡፡
\v 2 ነገር ግን ደስ የሚሰኘው በያህዌ ሕግ ነው ሕጉንም ቀንና ሌሊት ያሰላስላል፡፡
\s5
\v 3 እርሱም ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣ ቅጠሏም እንደማይጠወልግ፣ በወራጅ ውሆች እንድ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል፡፡
\s5
\v 4 ኃጢአተኞች ግን እንዲህ አይደሉም ነገር ግን ነፋስ ጠራርጐ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው፡፡
\v 5 ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ጉባኤ አይቆሙም፡፡
\s5
\v 6 ያህዌ የጻድቃንን አካሄድ ይጠብቃልና የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 አሕዛብ ለምን ያሤራሉ? ሕዝቦችስ ለምን በከንቱ ያድማሉ?
\v 2 የምድር ነገሥታት በአንድነት ተነሡ ገዦችም በአንድነት አሤሩ እንዲህ በማለትም በያህዌና በመሲሑ ላይ አሤሩ
\v 3 «እግር ብረታቸውን ከእግራችን እንቁረጥ፣ ሰንሰሰታቸውንም በጥሰን እንጣል፡፡»
\s5
\v 4 በሰማያት የሚቀመጥ እርሱ ያፌዝባቸዋል ጌታም ይሳለቅባቸዋል፡፡
\v 5 ከዚያም በቁጣው ያናግራቸዋል እንዲህ በማለትም በመዐቱ ያስፈራቸዋል
\s5
\v 6 «እኔ ራሴ በጽዮን፣ በተቀደሰውም ተራራዬ ንጉሤን ሾምሁ፡፡»
\v 7 የያህዌን ዐዋጅ ዐውጃለሁ፡፡ እርሱም እንዲህ አለኝ፣ «አንተ ልጄ ነህ! በዚህ ቀን አባትህ ሆኛለሁ፡፡
\s5
\v 8 ለምነኝ፤ አሕዛብን ለርስትህ የምድር ነገሥታትንም ለግዛትህ እሰጥሃለሁ፡፡
\v 9 በብረት በትር ትቀጠቅጣቸዋለህ ሸክላ ሠሪው እንዳበጀው ዕቃ ታደቃቸዋለህ፡፡»
\s5
\v 10 ስለዚህ አሁን እናንት ነገሥታት ተጠንቀቁ እናንት የምድር ገዦች አስተውሉ፡፡
\v 11 ያህዌን በፍርሃት አምልኩት በመንቀጥቀጥ ተገዙለት፡፡
\s5
\v 12 እንዳይቆጣ በመንገድም እንዳትጠፉ ልጁን ሳሙት፡፡ ቁጣው ፈጥኖ ይነዳልና፡፡ እርሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ የተባረኩ ናቸው፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ጠላቶቼ ምንኛ በዙ! በእኔ ላይ የተነሡ ብዙዎች ናቸው፡፡
\v 2 ብዙ ሰዎች፣ «እግዚአብሔር አያድነውም» እያሉ ስለ እኔ ይናገራሉ፡፡
\s5
\v 3 አንተ ግን ያህዌ ሆይ፣ ዙሪያዬን እንደ ጋሻ ትከልለኛለህ፣ ክብሬንና ራሴንም ከፍ የምታደርግ አንተ ነህ፡፡
\v 4 ድምፄን ወደ ያህዌ አነሣለሁ እርሱም ከተቀደሰው ተራራው ይመልስልኛል፡፡ ሴላ
\s5
\v 5 በሰላም እተኛለሁ፤ እንቀላፋለሁ ያህዌ ስለ ጠበቀኝ ከእንቅልፌ ተነሣሁ፡፡
\v 6 በየአቅጣጫው ከተነሡብኝ ሰዎች ብዛት አልፈራም፡፡
\s5
\v 7 ያህዌ ሆይ ተነሥ፤ አምላኬ ሆይ አድነኝ! አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መታህ የክፉዎችን ጥርስ ሰበርህ፡፡
\v 8 መዳን ከያህዌ ነው በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 የጽድቄ አምላክ ሆይ፣ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ ከጭንቀቴም አሳርፈኝ ማረኝ ጸሎቴንም ስማ፡፡
\s5
\v 2 እናንተ ሰዎች እስከ መቼ ክብሬን ታወርዳላችሁ? እስከ መቼ ከንቱ ነገር ትወዳላችሁ፤ ሐሰትንስ ትፈልጋላችሁ? ሴላ
\v 3 ያህዌ ጻድቁን ለራሱ እንደ ለየ ዕወቁ፡፡ በጠራሁት ጊዜ ያህዌ ይሰማኛል፡፡
\s5
\v 4 የቱንም ያህል ብትፈሩ ኃጢአት አትሥሩ! በመኝታችሁ እያላችሁ በልባችሁ አሰላስሉ፤ ጸጥም በሉ፡፡ ሴላ
\v 5 ለያህዌ የጽድቅ መሥዋዕት አቅርቡ እምነታችሁንም እርሱ ላይ አድርጉ፡፡
\s5
\v 6 ብዙዎች፣ «መልካሙን ማን ያሳየናል?» ይላሉ፡፡ ያህዌ ሆይ፣ የፊትህን ብርሃን እኛ ላይ አብራ፡፡
\v 7 ብዙ እህልና ወይን ካገኙ ሰዎች ይበልጥ አንተ ልቤን በታላቅ ሐሤት ሞልተኸዋል፡፡
\v 8 በሰላም የምታኖረኝ አንተ ብቻ ስለሆንህ በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ ወደ አንተ ስጣራ ስማኝ መቃተቴንም አስብ፡፡
\v 2 ንጉሤና አምላኬ ወደ አንተ እጸልያለሁና የልመናዬን ጽምፅ አድምጥ
\v 3 ያህዌ ሆይ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ በማለዳ ልመናዬን ወደ አንተ አቀርባለሁ፤ እጠባበቃለሁም፡፡
\s5
\v 4 በእርግጥ አንተ በክፋት ደስ የምትሰኝ አምላክ አይደለህም ክፉ ሰዎች ከአንተ አያድሩም፡፡
\v 5 እብሪተኛ በፊትህ አይቆምም ዐመፃን የሚያደርጉትህን ሁሉ ጠላህ፡፡
\v 6 ሐሰተኞችን ታጠፋለህ ደም የተጠሙትን አታላዮችን ያህዌ ይጸየፋል፡፡
\s5
\v 7 እኔ ግን በኪዳናዊ ታማኝነትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ በአክብሮት ፍርሃትም የተቀደሰ ማደሪያህ ውስጥ እሰግዳለሁ፡፡
\v 8 ጌታ ሆይ፣ በጠላቶች ምክንያት በጽድቅህ ምራኝ መንገድህንም በፊቴ አቅና፡፡
\s5
\v 9 በአፋቸው እውነት የለም ልባቸው ተንኰለኛ ነው፡፡ ጉሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፡፡ በአንደበታቸው ይሸነግላሉ፡፡
\v 10 እግዚአብሔር ሆይ፣ የእጃቸውን ስጣቸው ተንኰላቸው መጥፊያቸው ይሁን! አንተ ላይ ዐምፀዋልና ከኃጢአታቸው ብዛት የተነሣ አስወግዳቸው፡፡
\s5
\v 11 በአንተ የተማመኑ ሁሉ ደስ ይበላቸው አንተ ከለላ ሁነሃቸዋልና ለዘላለም ሐሤት ያድርጉ፡፡ ስምህን የሚወዱ በአንተ ደስ ይበላቸው
\v 12 ያህዌ ሆይ፣ አንተ ጻድቁን ትባርካለህ እንደ ጋሻ በሞገስ ትከልላቸዋለህ፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ በቁጣህ አትገሥጸኝ በመዐትህም አትቅጣኝ፡
\v 2 ያህዌ ሆይ፣ ደካማ ስለሆንሁ ምሕረት አድርግልኝ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ አጥንቶቼ ተናውጠዋልና፣ ፈውሰኝ፡፡
\s5
\v 3 ነፍሴም ታወካለች፤ ያህዌ ሆይ፣ ይህ እስከ መቼ ይቀጥላል?
\v 4 ወደ እኔ ተመለስ፤ አድነኝም፡፡ ከታማኝ ኪዳንህ የተነሣ አድነኝ
\v 5 በሞት የሚያስታውስህ የለም መቃብር ውስጥ ሆኖ፣ የሚያመሰግንህ ማን ነው?
\s5
\v 6 ከመቃተቴ የተነሣ ዝዬአለሁ ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ አልጋዬን በእንባ አርሳለሁ መኝታዬንም በእንባ አረጥባለሁ፡፡
\v 7 ከሐዘን የተነሣ ዐይኖቼ ፈዘዙ፤ ከባላጋራዎቼ የተነሣ ደከሙ፡፡
\s5
\v 8 እናንት ዐመፃን የምታደርጉ ሁሉ ከእኔ ራቁ ያህዌ የለቅሶዬን ድምፅ ሰምቷልና
\v 9 እንዲምረኝ ወደ እርሱ ያቀረብኩትን ልመና አድምጧል፤ ያህዌ ጸሎቴን ተቀብሏል፡፡
\v 10 ጠላቶቼ ሁሉ ይፈሩ፤ እጅግም ይታወኩ ወደ ኋላ ይመለሳሉ፤ በድንገትም ይዋረዳሉ፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ያህዌ አምላኬ ሆይ፣ አንተ መጠጊያዬ ነህ! ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ ታደገኝም
\v 2 አለበለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል የሚያድነኝ በሌለበት ሁኔታ ያደቁኛል፡፡
\s5
\v 3 አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ ጠላቶቼ አድርጓል የሚሉትን አላደረግሁም በእኔ ላይ ምንም በደል የለም፡፡
\v 4 በጐ ለዋለልኝ ክፉ አልመለስሁም፡፡ጠላቶቼን በከንቱ አልጐዳሁም፡፡
\s5
\v 5 የምናገረው እውነት ካልሆነ ጠላቴ አሳድዶ ይያዘኝ ሕይወቴን ከምድር ይቀላቅል ክብሬንም ከትቢያ ጋር ይደበልቅ፡፡ ሴላ
\s5
\v 6 ያህዌ ሆይ፣ በቁጣህ ተነሥ በጠላቶቼ ዛቻ ፍረድ አምላኬ ሆይ ንቃ ትእዛዝም አስተላልፍ፡፡
\v 7 ሕዝቦችን ሁሉ በዙሪያህ ሰብስብ ከላይም ሆነህ ግዛቸው፡፡
\s5
\v 8 ያህዌ በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል ያህዌ ሆይ፣ እንደ ጽድቄ ፍረድልኝ ልዑል ሆይ፣ እንደ ንጽሕናዬ መልስልኝ፡፡
\v 9 ልብንና አእምሮን የምትመረምር ጻድቅ አምላክ ሆይ፣ የክፉዎችን ዐመፅ አጥፉ፤ ጻድቃንን ግን አጽና፡፡
\s5
\v 10 ጋሻዬ ልዑል እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ ልበ ቅኖችን ያድናቸዋል፡፡
\v 11 እግዚአብሔር ጻድቅ ዳኛ ነው፤ ቁጣውንም በየዕለቱ የሚገልጥ አምላክ ነው፡፡
\s5
\v 12 ሰው በንስሐ የማይመለስ ከሆነ እግዚአብሔር ሰይፉን ይስላል፤ ለውጊያም ቀስቱን ይገትራል
\v 13 የሚገደሉ ጦር ዕቃዎቹን አዘጋጅቷል የሚንበለበሉትን ፍላጻዎቹንም አሰናድቶአል፡፡
\s5
\v 14 ክፋትን ያረገዘ፣ ክፉ ዕቅዶችን የፀነሰና አጥፊ ሐሰቶችን የወለደ ሰውን አስቡ፡፡
\v 15 ጥልቅ ጉድጓድ ይቆፍራል በቆፈረው ጉድጓድ እርሱ ይገባበታል፡፡
\v 16 ለሌሎች ያዘጋጀው ክፉ ዕቅድ ወደ ራሱ ይመለሳል፤ ዐመፃውም በገዛ ዐናቱ ላይ ይወርዳል፡፡
\s5
\v 17 ስለ ጽድቁ ያህዌን አመሰግናለሁ ለልዑል አምላክም እዘምራለሁ፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 ክብርህን በላይ በሰማያት የምትገልጥ አንተ ጌታችን ያህዌ፣ ስምህ በምድር ሁሉ ምንኛ ገናና ነው፡፡
\v 2 ከጠላትህ የተነሣ፤ ባላንጣንና ቂመኛን ጸጥ ለማሰኘት ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡
\s5
\v 3 ጣቶችህ የሠሯቸው ሰማያትን፣ በየቦታቸው ያደርግሃቸው ጨረቃና ከዋክብትን ስመለከት
\v 4 በአሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድነው? ትጠነቀቅለትስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?
\v 5 ከመላእከት በጥቂት አሳነሰኸው የክብርና የሞገስ ዘውድ አቀዳጀኸው፡፡
\s5
\v 6 በእጆችህ ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አደረግህለት
\v 7 በጐችና በሬዎችን፣ የዱር አራዊትን፣
\v 8 የሰማይ ወፎችን፣ የባሕር ዓሦችን ባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትን ሁሉ አስገዛህለት፡፡
\s5
\v 9 ጌታችን ያህዌ፣ ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ገነነ!
\s5
\c 9
\p
\v 1 በፍጹም ልቤ ያህዌን አመሰግናለሁ ስለ ድንቅ ሥራዎችህም እናገራለሁ፡፡
\v 2 በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ ልዑል ሆይ፣ ለስምህ እዘምራለሁ!
\s5
\v 3 ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ ተሰነካክለው በፊትህ ይጠፋሉ፡፡
\v 4 በዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ ጻድቅ ፈራጅ ነህ! የእኔን ጉዳይም ትፈርድልኛለህ፡፡
\s5
\v 5 ሕዝቦችን ገሠጽህ ክፉዎችን አጠፋህ ስማቸውን ከዘላለም እስከ ዘላለም ደመሰስህ፡፡
\v 6 ጠላቶች ለዘላለም ጠፍተዋል ከተሞቻቸውንም ገለባበጥሃቸው መታሰቢያቸውንም አጠፋህ፡፡
\s5
\v 7 እግዚአብሔር ግን ለዘላለም ዙፋኑ ላይ ነው ዙፋኑንም ለፍርድ አጽንቶአል፡፡
\v 8 ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል ለሕዝቦችም በፍትሕ ይፈርዳል፡፡
\s5
\v 9 ያህዌ ለተጨቆኑት ዐምባ ነው፡፡ በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል፡፡
\v 10 ስምህን የሚያውቁ በአንተ ይታመናሉ አንተ ያህዌ፣ የሚፈልጉህን አትተዋቸውም፡፡
\s5
\v 11 በጽዮን ለሚገዛ ለያህዌ ምስጋና ዘምሩ ድንቅ ሥራውን ለሕዝቦች ተናገሩ፡፡
\v 12 ደም ተበቃዩ አስቦአቸዋልና የጭቁኖችን ጩኸት አልዘነጋም፡፡
\s5
\v 13 ያህዌ ሆይ፣ ማረኝ በሚጠሉኝ የደረሰብኝን ጭቆና ተመልከት አንተ ከሞት አፋፍ ነጥቀህ አድነኝ፡፡
\v 14 ይህን ብታደርግልኝ፣ በጽዮን አደባባይ ምስጋናህን ሁሉ ለሕዝብ እናገራለሁ በማዳንህም ደስ እሰኛለሁ!
\s5
\v 15 ሕዝቦች ባዘጋጁት አዘቅት ሰጠሙ እግሮቻቸውም በሰወሩት ወጥመድ ተያዙ፡፡
\v 16 እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍርዱ ታወቀ ክፉዎችም በእጃቸው ሥራ ተጠመዱ፡፡
\s5
\v 17 ክፉዎች ተመልሰው ወደ ሲኦል ይወርዳሉ፡፡ እግዚአብሔርን የሚዘነጉ ሰዎች ሁሉ ፍጻሜ ይኸው ነው፡፡
\v 18 ችግረኞች መቼም ቢሆን አይዘነጉም የድኾችም ተስፋ ከንቱ ሆኖ አይቀርም፡፡
\s5
\v 19 ያህዌ ሆይ ተነሥ፣ ሰውም አያይል ሕዝቦችም በፊት ይፈረድባቸው፡፡
\v 20 ያህዌ ሆይ፣ አስደንግጣቸው ሕዝቦች ሰዎች ብቻ መሆናቸውን ይወቁ፡፡ ሴላ
\s5
\c 10
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ለምን ርቀህ ቆምህ? በመከራ ጊዜ ለምን ራስህን ሰወርህ?
\v 2 በእብሪት ተነሳሥተው ክፉዎች ጭቁኖችን ያሳድዳሉ እባክህ ክፉዎች ባጠመዱት ወጥመድ ይጠመዱ፡፡
\v 3 ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኩራራል ስግብግቡን ይባርካል፤ ያህዌን ይሰድባል፡፡
\s5
\v 4 ክፉ ሰው በራሱ ይመካል፤ እግዚአብሔርንም አይፈልግም፡፡ ስለ እርሱ ምንም ደንታ ስለሌለው ስለ እግዚአብሔር አያስብም፡፡
\v 5 ነገሩ ዘወትር ለእርሱ የተሳካ ነው የእግዚአብሔርን ፍርድ ግን ሊረዳ አይችልም፡፡ በጠላቶቹ ላይ ይሳለቃል፡፡
\s5
\v 6 በልቡም፣ «በፍጹም አልወድቅም ከትውልድ እስከ ትውልድ መከራ አያገኘኝም» ይላል፡፡
\v 7 አፉ መርገምን፣ ሸፍጥንና ግፍን የተሞላ ነው፤ በምላሱ ይጐዳል፤ ይገድላልም፡፡
\s5
\v 8 መንደሮች አጠገብ አድፍጦ ይጠብቃል በሰዋራ ቦታ ንጹሐንን ይገድላል ዐይኖቹም ምስኪኖች ላይ ያነጣጥራሉ፡፡
\v 9 ደን ውስጥ እንዳለ አንበሳ በስውር ያደባል ረዳት የሌለውን ለመያዝ ያሸምቃል፡፡ መረቡን ዘርግቶ ጭቁኖችን ያጠምዳል፡፡
\v 10 እርሱ መትቶ ይጥላቸዋል፤ ረዳት የሌላቸው ደካሞች ምስኪኖችም የእርሱ ሰለባ ሆነው ይወድቃሉ፡፡
\s5
\v 11 በልቡም፣ «እግዚአብሔር ረስቶአል እንዳያይም ፊቱን ሸፍኖአል» ይላል፡፡
\v 12 ያህዌ ሆይ፣ ተነሥ! አምላክ ሆይ ኃያል ክንድህ ይነሣ! የተጨቆኑትን ችላ አትበላቸው፡፡
\s5
\v 13 ክፉ ሰው ለምን እግዚአብሔርን ይንቃል? በልቡም ለምን፣ «እግዚአብሔር አይቀጣኝም» ይላል?
\v 14 አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤ ለድኻ አደጉም አንተ ረዳቱ ነህ፡፡
\s5
\v 15 የክፉና የበደለኛውን ክንድ ስበር አንተ እንደማታገኘው አስቦ ነበር የእጁንም ሰጠው፡፡
\v 16 ያህዌ ከዘላለም እስከ ዘላለም ንጉሥ ነው ሕዝቦችም ከምድሩ ይወገዳሉ፡፡
\s5
\v 17 ያህዌ የጭቁኖቹን ጩኸት ሰምቷል ልባቸውን ታበረታለህ፤ ጸሎታቸውንም ትሰማለህ
\v 18 ከእንግዲህ ማንም በምድር ላይ ሽብር እንዳያደርግ አንተ አባት ለሌላቸውና ለጭቁኖች መከታ ሆንህላቸው፡፡
\s5
\c 11
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አደረግሁ ታዲያ፣ ነፍሴ፣ «እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ብረሪ» እንዴት ትሏታላችሁ?
\v 2 ደግሞም ለምን እንዲህ ትሉኛላችሁ? ልበ ቅኖችን በጨለማ ለመግደል ክፉዎች ቀስታቸውን ገትረዋል፤ ፍላጻቸውንም በአውታሩ ላይ ደግነዋል፡፡
\s5
\v 3 ያህዌ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አደረግሁ ታዲያ፣ ነፍሴ፣ «እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ብረሪ» እንዴት ትሏታላችሁ? ደግሞም ለምን እንዲህ ትሉኛላችሁ?
\v 4 ልበ ቅኖችን በጨለማ ለመግደል ክፉዎች ቀስታቸውን ገትረዋል፤ ፍላጻቸውንም በአውታሩ ላይ ደግነዋል፡፡
\s5
\v 5 ያህዌ ጻድቁንና ኃጢአተኛውን ይመለከታል ዐመፅን ማድረግ የሚወዱትን ግን ይጠላቸዋል፡፡
\v 6 እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤ የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስም የእነርሱ ዕጣ ፈንታ ነው፡፡
\v 7 ያህዌ ጻድቅ ስለ ሆነ የጽድቅን ሥራ ይወዳል፤ ቅኖችም ፊቱን ያያሉ፡፡
\s5
\c 12
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ደግ ሰው የለምና አንተው እርዳኝ ከሰው ዘር መካከል አንድ ታማኝ አይገኝም፡፡
\s5
\v 2 እያንዳንዱ ሰው ለባልንጀራው ባዶ ቃላት ይናገራል በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራል፡፡
\v 3 ሸንጋይ ከናፍርቶችንና በትምክህት የሚናገሩ አንደበቶችን ያህዌ ያጥፋ፡፡
\v 4 እነዚህም፣ «በአንደበታችን እንበረታለን የምንናገረውንስ ማን ማስተባበል ይችላል?» የሚሉ ናቸው፡፡
\s5
\v 5 «ስለ ድኾች መከራ፣ ስለ ችግረኞች ጩኸት ያህዌ አሁን እነሣለሁ፤ የናፈቁትንም ሰላም እሰጣቸዋለሁ» ይላል፡፡
\s5
\v 6 የያህዌ ቃሎች የነጹ ቃሎች ናቸው በእሳት ምድጃ ሰባት ጊዜ እንደ ነጠረ ብር የጠሩ ናቸው፡፡
\v 7 ያህዌ ሆይ፣ አንተ ትጠብቀናለህ ከዚህ ዐመፀኛ ትውልድ ለዘላለም ጻድቃንን ትጠብቃለህ፡፡
\v 8 በሰው ልጆች መካከል ክፋት በገነነበት ጊዜ ዐመፀኞች እንዳሻቸው በየቦታው ይዘራሉ፡፡
\s5
\c 13
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ እስከ መቼ ድረስ ለዘላለሙ ትረሳኛለህ? ፊትህን ከእኔ የምትሰውረውስ እስከመቼ ድረስ ነው?
\v 2 በስጋት የምኖረው ልቤስ ቀኑን ሙሉ የሚያዝነው እስከ መቼ ነው? ጠላቴ እኔ ላይ የሚያይለው እስከ መቼ ነው?
\s5
\v 3 ያህዌ አምላኬ ሆይ፣ ወደ እኔ ተመልከት መልስልኝም!
\v 4 የሞት እንቅልፍ እንዳይወስደኝ ዐይኖቼን አብራ፡፡ ጠላቴ፣ «አሸነፍሁት» እንዳይል ባላጋራዎቼም በውድቀቴ ደስ እንዳይላቸው ርዳኝ፡፡
\s5
\v 5 እኔ ግን ወሰን በሌለው ፍቅርህ እተማመናለሁ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል፡፡
\v 6 ቸርነቱ በዝቶልኛልና ለያህዌ እዘምራለሁ፡፡
\s5
\c 14
\p
\v 1 ሞኝ በልቡ፣ «እግዚአብሔር የለም» ይላል፡፡ ብልሹዎች ናቸው፤ አስጸያፊ ተግባርም ይፈጽማሉ፡፡ መልካም የሚያደርግ አንድም የለም፡፡
\s5
\v 2 የሚያስተውል፣ እርሱንም የሚፈልግ መኖሩን ለማየት ያህዌ ከሰማይ ወደ ምድር ተመለከተ፡፡
\v 3 ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤ ሁሉም ብልሹዎች ሆነዋል ከእነርሱ አንድ እንኳ መልካም የሚያደርግ የለም፡፡
\s5
\v 4 እነዚያ ዐመፃ የሚያደርጉ ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ፣ የያህዌን ስም የማይጠሩ ሰዎች ዕውቀት የላቸውምን?
\s5
\v 5 እግዚአብሔር በጻድቃን መካከል ይገኛልና እነርሱ በፍርሃት ተርበደበዱ!
\v 6 ምንም እንኳ ያህዌ መጠጊያው ቢሆንም እናንተ ግን ድኻውን ማዋረድ ትፈልጋላችሁ፡፡
\s5
\v 7 ያህዌ ሕዝቡን ከምርኮ ሲመለስ ለእስራኤል መዳን ከጽዮን ይመጣል ያኔ ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል፡፡
\s5
\c 15
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ በድንኳንህ ውስጥ የሚያድር ማን ነው? በተቀደሰው ኮረብታህስ የሚኖር ማን ነው?
\v 2 አካሄዱ ንጹሕ የሆነ፣ ጽድቅን የሚያደርግ ከልቡ እውነትን የሚናገር፤
\s5
\v 3 በአንደበቱ የማይሸነግል ሌሎች ሰዎችን የማይጐዳ፤ በጐረቤቱ ላይ አሉባልታ የማያሰራጭ
\s5
\v 4 ነውረኛውን የሚንቅ፣ ያህዌን የሚፈሩትን ግን የሚያከብር፡፡ ዋጋ ቢያስከፍለው እንኳ የገባውን ቃል የሚፈጽም
\v 5 ገንዘቡን በወለድ የማያበድር ንጹሕ ሰው ላይ ለመመስከር ጉቦ የማይበላ፤ እነዚህን የሚያደርግ ከቶውንም አይናወጥም፡፡
\s5
\c 16
\p
\v 1 በአንተ ተማምኛለሁና ያህዌ ሆይ ጠብቀኝ፡፡
\v 2 ያህዌን፣ «አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ ውጪ መልካም ነገር የለኝም» አልሁት፡፡
\v 3 በምድር የሚኖሩ ቅዱሳን የተከበሩ ናቸው፤ በእነርሱም ደስ ይለኛል፡፡
\s5
\v 4 ሌሎች አማልክትን የሚከተሉ መከራቸው ይበዛል እኔ ግን ለአማልክቶቻቸው የደም ቁርባን አላፈስም፤ ስማቸውንም በአፌ አልጠራም፡፡
\s5
\v 5 ያህዌ የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤ ፍጻሜዬም በአንተ እጅ ነው፡፡
\v 6 መለኪያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል በእርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ፡፡
\s5
\v 7 የሚመክረኝን ያህዌን እባርካለሁ፤ ሌሊት እንኳ ልቦናዬ ያስተምረኛል፡፡
\v 8 ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አስቀድማለሁ፤ እርሱ በቀኜ ስለሆነ አልናወጥም!
\s5
\v 9 ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፤ ክብሬም ሐሤት አደረገ፡፡ በእርግጥ ያለ ስጋት እኖራለሁ፡፡
\v 10 ምክንያቱም አንተ ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም ታማኝህ መበስበስ እንዲደርስበት አታደርግም፡፡
\s5
\v 11 የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣ በቀኝህም የዘላለም ፍስሐ አለ፡፡
\s5
\c 17
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት የማቀርበውን ጸሎት ስማ ጩኸቴንም አድምጥ፡፡ ከሐሰተኛ ከንፈር ያልወጣውን ጸሎቴን አድምጥ፡፡
\v 2 ጽድቄ ከአንተ ዘንድ ይምጣ፤ ዐይኖችህም ፍትሕን ይመልከቱ፡፡
\s5
\v 3 ልቤን ብትመረምር፣ በሌሊትም ብትጐበኘኝ፣ ብትፈትነኝም ከእኔ ዘንድ ክፋት አታገኝም፤ አንደበቴም አይስትም፡፡
\s5
\v 4 የሰው ልጆችን ተግባር በተመለከተ አንተ በተናገርኸው ቃል መሠረት ከዐመፀኞች መንገድ ራሴን ጠብቄአለሁ፡፡
\v 5 አረማመዱ በመንገድህ ጸንቶአል እግሮቼም አልተንሸራተቱም፡፡
\s5
\v 6 ያህዌ ሆይ፣ ስለምትመልስልኝ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ጸሎቴንም ስማ፡፡
\v 7 የሚተማመኑብህን በቀኝህ ከጠላቶቻቸው የምታድናቸው አንተ ታማኝትህን ድንቅ አድርገህ ግለጠው፡፡
\s5
\v 8 እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህ ጥላ ሥር ሰውረኝ፡፡
\v 9 ከሚያስጨንቁኝ፣ ከከበቡኝም አደገኛ ጠላቶቼ ጋርደኝ፡፡
\v 10 እነርሱ ማንንም አይምሩም፤ አንደበታቸው ትዕቢትን ይናገራል፡፡
\s5
\v 11 ጠላቶቼ አስጨነቁኝ፤ ከበባም አደረጉብኝ መሬት ላይ ሊዘርሩኝም አፈጠጡብኝ፡፡
\v 12 እነርሱ ለንጥቂያ እንደሚጓጓ፣ አድፍጦም እንደሚጠብቅ ደቦል አንበሳ ናቸው፡፡
\s5
\v 13 ያህዌ ሆይ፣ ተነሣና አጥቃቸው፤ በአፍጢማቸው ድፋቸው! በሰይፍህ ከክፉዎች አድነኝ፡፡
\v 14 ያህዌ ሆይ፣ እንዲህ ካሉ ሰዎች፣ ብልጽግናቸው በዚህ ሕይወት ብቻ ከሆነ ከዚህ ዓለም ሰዎች በቀኝህ አድነኝ፡፡ የአንተ የሆነ ሰዎችን ሆድ በመልካም ነገር ትሞላለህ እነርሱም ብዙ ልጆች ይኖሩዋቸዋል፤ ሀብታቸውንም ለልጆቻቸው ያወርሳሉ፡፡
\s5
\v 15 እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ ስነቃም ክብርህን ዐይቼ እረካለሁ፡፡
\s5
\c 18
\p
\v 1 ጉልበት የሆንኸኝ ያህዌ እወድሃለሁ፡፡
\s5
\v 2 ያህዌ ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፡፡ እርሱ አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፣ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው፡፡
\v 3 ምስጋና የሚገባውን ያህዌን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ፡፡
\s5
\v 4 የሞት ገመድ አነቀኝ፤ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ፡፡
\v 5 የሲኦል ማሰሪያ ተጠመጠመብኝ የሞት ወጥመድም ተጠመደብኝ፡፡
\s5
\v 6 በጨነቀኝ ጊዜ ያህዌን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም ወደ አምላኬ ጮኽሁ፤ ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም ከፊቱ ደረሰ፤ ወደ ጆሮውም ገባ፡፡
\s5
\v 7 ምድር ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፤ የተራሮችም መሠረት ተናጋ፤ ጌታ እግዚአብሔር ተቆጥቶአልና ተንቀጠቀጡ፡፡
\v 8 ከአፍንጫው ጢስ፣ ከአፉም የሚባላ እሳት ወጣ፤ የፍም ነበልባል ከእርሱ ፈለቀ፡፡
\s5
\v 9 ሰማያትን ከፍቶ ወረደ፤ ከእግሮቹም በታች ድቅድቅ ጨለማ ነበረ፡፡
\v 10 በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፍ መጠቀ፡፡
\s5
\v 11 ጨለማን እንደ ድንኳን፣ ዝናብ አዘል ጥቁር ደመናን በዙሪያው አደረገ፡፡
\v 12 በፊቱ ካለው መብረቅ የተነሣ የበረዶ ድንጋይና የእሳት ፍም ወጣ፡፡
\s5
\v 13 ያህዌ ከሰማያት አንጐደጐደ! የልዑልም ድምፅ አስተጋባ፡፡
\v 14 ቀስቱን አስፈንጥሮ ጠላቶቹን በተናቸው፤ መብረቅ አዥጐድጉዶ አሳደዳቸው፡፡
\s5
\v 15 ያህዌ ሆይ፣ ከቁጣህ የተነሣ፣ ከአፍንጫህም እስትንፋስ የተነሣ፣ የባሕር ወለል ታዬ የዓለምም መሠረት ተገለጠ፡፡
\s5
\v 16 ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሃም ስቦ አወጣኝ፡፡
\v 17 ከኃያላን ጠላቶቼ፣ ከሚጠሉኝ ከዐቅሜ በላይ ከሆኑ ባላንጣዎቼ ታደገኝ፡፡
\s5
\v 18 በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ ያህዌ ግን ድጋፍ ሆነኝ፡፡
\v 19 በጣም ሰፊ ወደ ሆነ ቦታ አወጣኝ፤ ወዶኛልና አዳነኝ፡፡
\s5
\v 20 ያህዌ እንደ ጽድቄ ከፍሎኛል፤ እጆቼ ንጹሕ ስለ ነበሩ ታድጐኛል፡፡
\v 21 የያህዌን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ በዐመፅ ተነሣሥቼ ከእርሱ ዘወር አላልሁም፡፡
\s5
\v 22 ሕጐቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤ ሥርዐቱንም ከፊቴ አላራቅሁም፡፡
\v 23 በእርሱ ፊት ንጹሕ ነበርሁ፤ ከኃጢአትም ራሴን ጠብቄአለሁ፡፡
\v 24 ያህዌ እንደ ጽድቄ መጠን፤ በዐይኖቹ ፊት ንጹሕ እንደ ነበሩት እጆቼ መጠን ከፍሎኛል፡፡
\s5
\v 25 አንተ ታማኝ ለሆኑት ታማኝ ነህ እውነተኞች ለሆኑት እውነተኛ ነህ
\v 26 ለንጹሖች ንጹሕ ነህ፡፡ ለጠማሞች ግን ጠማማ ትሆንባቸዋለህ፡፡
\s5
\v 27 አንተ ትሑታንን ታድናለህ ትዕቢተኛውን ዐይን ግን ታዋርዳለህ፡፡
\v 28 አንተ መብራቴን ታበራለህ፤ አምላኬ ያህዌ ጨለማዬን ብርሃን ታደርገዋለህ፡፡
\v 29 በአንተ ጉልበት በሰራዊት እረማመዳለሁ፤ በአምላኬም ኃይል ቅጥሩን እዘላለሁ፡፡
\s5
\v 30 የእግዚአብሔር መንገድ ፍጹም ነው፤ የያህዌ ቃል የነጠረ ነው። መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ እርሱ ጋሻ ነው።
\v 31 ከእግዚአብሔር በቀር ማን አምላክ አለ? ከአምላካችንስ በቀር ዐምባ ማን ነው?
\v 32 ኅይልን የሚያስታጥቀኝ፣ መንገዴንም የሚያቃና እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 33 እርሱ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያጠነክራል፣ በከፍታዎችም ላይ ያቆመኛል፡፡
\v 34 እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል የናስ ቀስቶች መሳብ እንዲችሉ ክንዶቼን ያበረታል፡፡
\s5
\v 35 የማዳን ጋሻህን ሰጠኸኝ፤ ቀኝ እጅህ ደግፎኛል፤ ሞገስህም ታላቅ አድርጐኛል፡፡
\v 36 እግሮቼ እንዳይንሸራተቱ ከበታቼ ያለውን ቦታ አሰፋህልኝ፡፡
\s5
\v 37 ጠላቶቼን አሳድጄ እይዛቸዋለሁ፤ እስኪጠፉ ድረስ ወደ ኃላ አልልም፡፡
\v 38 እንዳያንሰራሩ አድርጌ አደቀቅኋቸው ከእግሬም ሥር ወደቁ፡፡
\v 39 አንተ ለጦርነት ኃይልን አስታጠቅኸኝ፤ በእኔ ላይ የተነሡትንም ከበታቼ አደረግህልኝ፡፡
\s5
\v 40 ጠላቴቼ ወደ ኋላ እንዲሸሹ አደረግህ የሚጠሉኝንም አጠፋኋቸው፡፡
\v 41 ለእርዳታ ጮኹ፤ ግን ማንም አላዳናቸውም ወደ ያህዌ ጮኹ፤ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም፡፡
\v 42 ነፋስ ጠርጐ እንደሚወስደው ትቢያ አደቀቅኋቸው መንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ ረጋገጥኋቸው፡፡
\s5
\v 43 ከሕዝብ ክርክር ታደገኸኝ፤ መንግሥታት ላይ መሪ አደረግኸኝ፤ የማላውቀውም ሕዝብ ያገለግለኛል፡፡
\v 44 ዝናዬን እንደ ሰሙ ታዘዙልኝ፤ ባዕዳንም በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አደረጉ፡፡
\v 45 ባዕዳን በፍርሃት ተዋጡ እየተንቀጠቀጡም ከምሽጋቸው ወጥተው መጡ፡፡
\s5
\v 46 ያህዌ ሕያው ነው፤ ዐለት የሆነልኝ ይባረክ የድነቴ አምላክ ከፍ ከፍ ይበል፡፡
\v 47 እርሱ ጠላቶቼን ይበቀልልኛል፤ ሕዝቦችን ከእግሬ ሥር የሚያስገዛልኝም እርሱ ነው፡፡
\s5
\v 48 ከጠላቶቼም የሚታደገኝ እርሱ ነው! በእርግጥም አንተ ከተነሡብኝ በላይ ከፍ አደረግኸኝ! ከጨካኞችም አዳንኸኝ፡፡
\v 49 ያህዌ ሆይ፣ ስለዚህ ለአንተ ውዳሴ እሰጣለሁ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም እዘምራለሁ፡፡
\s5
\v 50 እግዚአብሔር ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል ለቀባው ለዳዊትና ለዘሮቹም ለዘላለም ታማኝነቱን ይገልጣል፡፡
\s5
\c 19
\p
\v 1 ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይ ጠፈርም የእጁን ሥራ ያውጃል።
\v 2 አንዱ ቀን ለሌላው ቀን ቃል ይናገራል፤ አንዱም ሌሊት ለሌላው ሌሊት ዕውቀትን ይገልጣል፡፡
\v 3 ንግግር የለም፤ ቃልም የለም፤ ድምፃቸውም አልተሰማም፡፡
\s5
\v 4 ያም ሆኖ ቃላቸው ወደ ምድር ሁሉ ወጣ፣ ንግግራቸውም ወደ ዓለም ዳርቻ ወጣ፡፡ በመካከላቸውም ለፀሐይ ድንኳኑን ተከለ
\v 5 ፀሐይ ከእልፍኙ እንደሚወጣ ሙሽራ ይወጣል ወደ ግቡም እንደሚሮጥ ብርቱ ሰው ደስ ይለዋል፡፡
\v 6 ፀሐይ ከአንዱ አድማስ ሰማይን አቋርጦ ወደ ሌላው አድማስ ይወጣል፤ ከሙቀቱም የሚሰወር የለም፡፡
\s5
\v 7 የያህዌ ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን መልሶ ያለመልማል፤ የያህዌ ምስክር የታመነ ነው፤ ዐላዋቂውን ጥበበኛ ያደርጋል።
\v 8 የያህዌ ሕግ ትክክል ነው፤ ልብን ደስ ያሰኛል፡፡ የያህዌ ትእዛዝ ንጹሕ ነው፤ ዐይንንም ያበራል፡፡
\s5
\v 9 ያህዌን መፍራት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፡፡ የያህዌ ፍርድ የታመነ ነው፤ ሁለንተናውም ጽድቅ ነው፡፡
\v 10 ከወርቅ ይልቅ የከበረ፤ እጅግ ከጠራ ወርቅም የበለጠ ነው፡፡ ከማር ይልቅ ይጣፍጣል፤ ከማር ወለላም ይበልጥ ይጥማል፡፡
\s5
\v 11 እንዲሁም አገልጋይህ በእርሱ ይመከራል፤ ሕግህን በመጠበቁም ወሮታ አለው፡፡
\v 12 ስሕተቱን ሁሉ ማን ማስተዋል ይችላል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ፡፡
\s5
\v 13 ባርያህን ከድፍረት ኃጢአት ጠብቅ ያኔ ፍጹም እሆናለሁ ከታላቅ በደልም እነጻለሁ፡፡
\v 14 ዐለቴና አዳኜ ያህዌ ሆይ፣ የአፌ ቃልና የልቤም ሐሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን፡፡
\s5
\c 20
\p
\v 1 በመከራ ቀን ያህዌ ይስማህ የያዕቆብም አምላክ ይጠብቅህ፡፡
\v 2 ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ
\s5
\v 3 መባህን ሁሉ ያስብልህ የሚቃጠል መሥዋዕትህን ይቀበልልህ፡፡
\v 4 የልብህን መሻት ይስጥህ ዕቅድህንም ሁሉ ያሳካልህ፡፡
\s5
\v 5 በአንተ ደስ ይለናል በአምላካችንም ስም ዐርማችን ከፍ ከፍ እናደርጋለን፡፡ ያህዌ የለመንኸውን ሁሉ ይፈጽምልህ፡፡
\v 6 ያህዌ የቀባውን እንደሚያድን አሁን ዐወቅሁ፤ ማዳን በሚችለው ቀኝ እጁ ከተቀደሰው ሰማይ ይመልስለታል፡፡
\s5
\v 7 አንዳንዶች በሰረገላ ሌሎች በፈረስ ይታመናሉ እኛ ግን የያህዌን ስም እንጠራለን፡፡
\v 8 እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ እኛ ግን ተነሣን፤ ቀጥ ብለንም ቆምን!
\s5
\v 9 ያህዌ ሆይ፣ ንጉሡን አድን ስንጠራህ እኛንም ሰማን፡፡
\s5
\c 21
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ንጉሥ በኃይልህ ደስ ይለዋል! በምትሰጠውም ድል እጅግ ሐሤት ያደርጋል፡፡
\v 2 የልቡን መሻት ሰጠኸው፤ የለመንህንም አልከለከልኸውም፡፡ ሴላ
\s5
\v 3 ብዙ በረከት ሰጠኸው፤ በራሱ ላይ የንጹሕ ወርቅ ዘውድ አደረግህለት፡፡
\v 4 ሕይወትን ለመነህ አንተም ረጅም ዘመንን ለዘላለም ሰጠኸው
\s5
\v 5 ከሰጠኸው ድል የተነሣ ክብሩ እጅግ በዛ ክብርንና ሞገስንም አጐናጸፍኸው፡፡
\v 6 ዘላለማዊ በረከት ሰጠኸው በፊትህ ባለው ፍስሐም ደስ አሰኘኸው፡፡
\s5
\v 7 ንጉሡ በያህዌ ተማምኖአልና ከልዑል ታማኝነት የተነሣ ከቶውንም አይናወጥም፡፡
\v 8 እጅህ ጠላቶችህን ትይዛቸዋለች ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ሁሉ ታገኛቸዋለች፡፡
\s5
\v 9 በቁጣህ ቀን እሳት በሚንቀለቀልበት ምድጃ ታቃጥላቸዋለህ፤ ያህዌ በመዓቱ ይፈጃቸዋል፤ እሳትም ይበላቸዋል፡፡
\v 10 ትውልዳቸውን ከምድር ላይ ታጠፋለህ ዘራቸውንም ከሰዎች መካከል ለይተህ ትደመስሳለህ፡፡
\s5
\v 11 በአንተ ላይ ክፋት ቢያስቡም፣ ሤራ ቢያውጠነጥኑም፣ አይሳካላቸውም፡፡
\v 12 በመጡበት ትመልሳቸዋለህና ቀስትህንም በእነርሱ ላይ ታነጣጥራለህ፡፡
\s5
\v 13 ያህዌ ሆይ፣ በብርታትህ ከፍ ከፍ በል እኛም ኃይልህን እንዘምራለን፤ እንወድሳለንም፡፡
\s5
\c 22
\p
\v 1 አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ለማዳን፣ ከመቃተቴም ቃል ለምን ራቅህ?
\v 2 አምላኬ ሆይ፣ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፣ አንተ ግን አልመለሰህልኝም በሌሊት እንኳ አላረፍሁም፡፡
\s5
\v 3 አንተ ቅዱስ ነህ በእስራኤል ምስጋና ውስጥ እንደ ንጉሥ ትቀመጣለህ፡፡
\v 4 አባቶቻችን በአንተ ተማመኑ፣ በአንተ ተማመኑ አንተም ታደግሃቸው፡፡
\v 5 ወደ አንተ ጮኹ፤ እነርሱም ዳኑ በአንተ ተማመኑ፤ እነርሱም አላፈሩም፡፡
\s5
\v 6 እኔ ግን ትል እንጂ፣ ሰው አይደለሁም ለሰዎች ማላገጫ፣ በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ፡፡
\v 7 የሚያዩኝ ሁሉ ይሣለቁብኛል ራሳቸውንም እየነቀነቁ ያፌዙብኛል፡፡
\v 8 «በያህዌ ተማምኖአል፤ ያህዌ ያድነው፤ በእርሱ ደስ ተሰኝቶበታልና እስቲ ይታደገው» ይላሉ፡፡
\s5
\v 9 አንተ ከእናቴ ማሕፀን አወጣኸኝ በእናቴም ጡት ሳለሁ በአንተ እንድታመን አደረግኸኝ፡፡
\v 10 ከማሕፀን ጀምሮ በአንተ ተጣልሁ በእናቴ ማሕፀን ከነበርኩበት ጊዜ ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ!
\s5
\v 11 መከራ እየተቃረበ ነው የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ፡፡
\v 12 ብዙ ኮርማዎች ከበቡኝ ኃይለኛ የባሳን ኮርማዎች ዙሪያዬን ቆመዋል፡፡
\v 13 እንደሚያገሣና እንደሚቦጫጭቅ አንበሳ አፋቸውን ከፈቱብኝ፡፡
\s5
\v 14 እንደ ውሃ ፈሰሰሁ አጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ ልቤ እንደ ሰም ሆነ በውስጤም ቀጠለ፡፡
\v 15 ጉልበቴ እንደ ሸክላ ደረቀ ምላሴም ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ፡፡ እንደ ሞተ ሰው ትቢያ ላይ አደረግኸኝ፡፡
\s5
\v 16 ውሾች ከበቡኝ የክፉዎች ስብስብ በዙሪያዬ ሰፈሩ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩ
\v 17 ዐጥንቶቼን ሁሉ አንድ አንድ መቁጠር እችላለሁ እነርሱም አፍጥጠው ይመለከቱኛል፡፡
\s5
\v 18 ልብሶቼን ተከፋፈሉ በእጄ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉ፡፡
\v 19 ያህዌ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ ብርታቴ ሆይ፣ እባክህ እኔን ለመርዳት ፍጠን!
\s5
\v 20 ነፍሴን ከሰይፍ ታደጋት ውድ ሕይወቴንም ከክፉ ውሾች አድናት፡፡
\v 21 ከአንበሳ አፍ አድነኝ፣ ከተዋጊ ጐሽ ቀንዶችም ታደገኝ፡፡
\s5
\v 22 ስምህን ለወንድሞቼ እናገራለሁ፤ በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ፡፡
\v 23 እናንት ያህዌን የምትፈሩ አመስግኑት፡፡ እናንት የያዕቆብ ዘሮች ሁሉ አክብሩት! እናንት የእስራኤል ልጆች ሁሉ እርሱን ፍሩት!
\s5
\v 24 ጭንቀት የደረሰበትን ሰው አልናቀም፤ መከራ ላይ ያለውን አልተጸየፈም፤ ነገር ግን የድረሱልኝ ጩኸቱን ሰማው፡፡
\v 25 ስለ ሠራኸው መልካም ሥራ፣ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ አመሰግንሃለሁ፤ በሚፈሩህ ሰዎችም ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ፡፡
\s5
\v 26 ችግረኞች ይበላሉ፤ ይጠግባሉም ያህዌን የሚፈልጉም ያመሰግኑታል፡፡ ልባችሁ ለዘላለም ሕያው ይሁን፡፡
\v 27 የምድር ሕዝቦች ሁሉ ያስታውሳሉ ወደ ያህዌም ይመለሳሉ፤ የምድር ወገኖች ሁሉ በፊትህ ወድቀው ይሰግዳሉ፡፡
\s5
\v 28 መንግሥት የያህዌ ነውና ሕዝቦችንም የሚገዛ እርሱ ነው፡፡
\v 29 የምድር ከበርቴዎች ሁሉ ይበላሉ፤ እርሱንም ያመልካሉ በሕይወት ማቆየት የማይችሉ ወደ አፈር ተመላሽ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በፊቱ ይንበረከካሉ፡፡
\s5
\v 30 የሚመጣው ትውልድ ያገለግለዋል ለቀጣዩ ትውልድም ስለ ጌታ ይነግረዋል
\v 31 የጽድቅ ሥራውን በማወጅ ገና ላልተወለደ ሕዝብ ጽድቁን፣ እርሱ ያደረገውንም ይነግራሉ፡፡
\s5
\c 23
\p
\v 1 ያህዌ እረኛዬ ነው፤ ምንም አላጣም፡፡
\v 2 በለመለመ መስክ ያሳድረኛል ፀጥ ባለ ውሃ ዘንድ ይመራኛል፡፡
\s5
\v 3 ነፍሴን ይመልሳታል፤ ያድሳታል፡፡ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ ይመራኛል፡፡
\s5
\v 4 በጨለማው የሞት ሸለቆ ውስጥ እንኳ ባልፍ አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንህ ጉዳት ይደርስብኛል ብዬ አልፈራም፡፡
\s5
\v 5 በጠላቶቼ ፊት ለፊት በፊቴ ገበታ አዘጋጀህልኝ ራሴን በዘይት ቀባህ ጽዋዬ ሞልቶ ተርፏል፡፡
\s5
\v 6 በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ደግነትና ፍቅር ዘወትር ከእኔ ጋር ይሆናሉ፤ በያህዌም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ፡፡
\s5
\c 24
\p
\v 1 ምድርና በእርሷ ያለው ሁሉ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖር ሁሉ የያህዌ ነው፡፡
\v 2 እርሱ ባሕር ላይ መሥርቶአታልና በውሆችም ላይ አጽንቶአታል፡፡
\s5
\v 3 ወደ ያህዌ ተራራ ማን ይወጣል? በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል?
\v 4 ንጹሕ እጅና ንጹሕ ልብ ያለው፣ ነፍሱን ለሐሰት ያላስገዛ በሐሰት የማይምል፣
\s5
\v 5 እርሱ ከያህዌ ዘንድ በረከትን፣ ከመድኃኒቱም አምላክ ጽድቅን ይቀበላል፡፡
\v 6 እርሱን የሚፈልግ ትውልድ የያዕቆብ አምላክን ፊት የሚፈልግ እንዲህ ያለ ነው፡፡ ሴላ
\s5
\v 7 እናንተ ደጆች ራሳችሁን ቀና አድርጉ እናንተ የዘላለም በሮች የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!
\v 8 ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? ብርቱና ኃያል የሆነው ያህዌ፣ በጦርነት አሸናፊ የሆነው ያህዌ ነው፡፡
\s5
\v 9 እናንተ ደጆች ራሳችሁን ቀና አድርጉ እናንተ የዘላለም በሮች የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!
\v 10 ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? የሰራዊት ጌታ ያህዌ እርሱ የክብር ንጉሥ ነው፡፡ ሴላ
\s5
\c 25
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁ!
\v 2 አምላኬ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ፡፡ እባክህ አታሳፍረኝ፤ አታዋርደኝ ጠላቶቼም በእኔ ላይ ደስ እንዲላቸው አታድርግ፡፡
\v 3 አንተን ተስፋ የሚያደርጉ ከቶ አያፍሩም፤ እንዲያው ያለ ምክንያት የሚያታልሉ ግን ያፍራሉ፡፡
\s5
\v 4 ያህዌ ሆይ፣ አካሄድህን አሳውቀኝ መንገድህንም አስተምረኝ፡፡
\v 5 በእውነትህ ምራኝ አስተምረኝም፤ አንተ የድነቴ አምላክ ነህና ቀኑን ሙሉ በአንተ ታመንሁ፡፡
\s5
\v 6 ያህዌ ሆይ፣ ከጥንት ጀምሮ የነበሩ ምሕረትህንና ፍቅርህን አስብ፡፡
\v 7 የልጅነቴን ኃጢአት፣ መተላለፌንም አታስብብኝ፤ ያህዌ ሆይ፣ እንደ ቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህም መጠን አስበኝ፡፡
\s5
\v 8 ያህዌ መልካም ቅን ነው፤ ስለዚህ ኃጢአተኞችን መንገድን ያስተምራቸዋል፡፡
\v 9 ትሑታንን በትክክለኛው መንገድ ይመራቸዋል መንገዱንም ያስተምራቸዋል
\s5
\v 10 ኪዳኑንና ሥርዐቱን ለሚጠብቁ የያህዌ መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው፡፡
\v 11 ያህዌ ሆይ፣ ኃጢአቴ እጅግ ብዙ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ
\s5
\v 12 ያህዌን የሚፈራ ሰው ማን ነው ጌታ በመረጠው መንገድ ያስተምረዋል፡፡
\v 13 ዘመኑን በተድላ ደስታ ያሳልፋል ዘሮቹም ምድርን ይወርሳሉ፡፡
\s5
\v 14 ያህዌ ለሚታዘዙት ሁሉ ወዳጃቸው ነው ለእነርሱ የገባውንም ኪዳን ያጸናል፡፡
\v 15 ዐይኖቼ ዘወትር ወደ ያህዌ ናቸው እግሮቼን ከወጥመድ የሚያላቅቃቸው እርሱ ነው፡፡
\v 16 እኔ ብቸኛና ምስኪን ነኝና ወደ እኔ ተመለስ ማረኝም፡፡
\s5
\v 17 የልቤ ሐዘን በዝቶአል ከጭንቀቴ አወጣኝ፡፡
\v 18 መከራዬንና ጭንቀቴን ተመልከት ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር በል፡፡
\v 19 ጠላቶቼ እንዴት እንደ በዙ እይ፤ እንዴት አምርረው እንደሚጠሉኝ ተመልከት፡፡
\s5
\v 20 ነፍሴን ጠብቃት፤ ታደገኝም በአንተ ተማምኛለሁና አልዋረድ፤ አልፈር፡፡
\v 21 አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና ታማኝነትና ቅንነት ይጠብቁኝ
\s5
\v 22 ያህዌ ሆይ፣ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነው፡፡
\s5
\c 26
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ያለ ነቀፋ ተመላልሻለሁና አንተው ፍረደኝ፤ ያለ ማወላውል በያህዌ ተማምኛለሁ፡፡
\v 2 ያህዌ ሆይ፣ ፈትነኝ መርምረኝም የልቤንና የውስጤን ንጽሕና ፈትን!
\v 3 የኪዳን ታማኝነትህ ዘወትር በፊቴ ነው በታማኝነትህም ተመላለስሁ፡፡
\s5
\v 4 ከአታላይ ሰዎች ጋር አልተባበርሁም ከማይታመኑ ሰዎችም ጋር አልተቀላቀልሁም፡፡
\v 5 የክፉዎችን ኅብረት ጠላሁ ከዐመፀኞችም ጋር አልተቀመጥሁም፡፡
\s5
\v 6 እጆቼን በየዋህነት እታጠባለሁ ያህዌ ሆይ፣ መሠዊያህንም እዞራለሁ
\v 7 የምስጋናህን መዝሙር እየዘመርሁ ድንቅ ሥራዎችህን ሁሉ አወራለሁ፡፡
\v 8 ያህዌ ሆይ፣ የምትኖርበትን ቤት፣ የክብርን ማደሪያ ቦታ ወደድሁ፡፡
\s5
\v 9 ነፍሴን ከኃጢአተኞች ጋር፣ ሕይወቴንም ደም ከተጠሙ ጋር አታጥፉ
\v 10 በእነርሱ እጅ የተንኰል ዕቅድ አለ ቀኝ እጃቸውም ጉቦ ያጋብሳል፡፡
\s5
\v 11 እኔ ግን በታማኝነት እጓዛለሁ አድነኝ፤ ምሕረትም አድርግልኝ፡፡
\v 12 እግሮቼ በተስተካከለ ምድር ላይ ቆመዋል በጉባኤ ፊት ያህዌን እባርካለሁ፡፡
\s5
\c 27
\p
\v 1 ያህዌ ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማን ነው? ያህዌ የሕይወቴ መታመኛዋ ነው የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?
\s5
\v 2 ክፉ አድራጊዎች ሥጋዬን ለመብላት በቀረቡኝ ጊዜ፣ ባላጋራዎቼና ጠላቶቼ ተሰነካክለው ወደቁ፡፡
\v 3 ሰራዊት ቢከብበኝ እንኳ፣ ልቤ አይፈራም ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ ልበ ሙሉ ነኝ፡፡
\s5
\v 4 ያህዌን አንዲት ነገር ለመንሁት፣ እርሷንም እሻለሁ፤ ያም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በያህዌ ቤት እንድኖር፣ የመቅደሱን ውበት እንዳይና መቅደሱ ውስጥ አሰላስል ዘንድ ነው፡፡
\s5
\v 5 በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ይሰውረኛናል በዐለትም ላይ ያቆመኛል፡፡
\v 6 ያኔ በዙሪያዬ ባሉ ጠላቶቼ ላይ ራሴ ከፍ ከፍ ይላል በድንኳኑም የደስታ መሥዋዕት እሠዋለሁ ለያህዌ እቀኛለሁ፤ እዘምርለታለሁም፡፡
\s5
\v 7 ያህዌ ሆይ፣ ወደ አንተ ስጮኽ ድምፄን ስማ ማረኝ መልስልኝም፡፡
\v 8 «ፊቴን ፈልጉ» ባልህ ጊዜ ልቤ፣ «የያህዌን ፊት እፈልጋለሁ» አለች፡፡
\s5
\v 9 ፊትህን ከእኔ አትሰውር ተቆጥተህም ባርያህን ገሸሽ አታድርገው! መቼም አንተ ረዳቴ ነህና የመድኃኒቴ አምላክ ሆይ፣ አትተወኝ፣ አትጣለኝም
\v 10 አባትና እናቴ ቢተውኝ እንኳ ያህዌ ይቀበለኛል፡፡
\s5
\v 11 ያህዌ ሆይ መንገድህን አስተምረኝ ስለ ጠላቶቼም በቀናች መንገድ ምራኝ፡፡
\v 12 ሐሰተኛ ምስክሮች ተነሥተውብኛልና ጠላቶቼ እንደ ፈለጉ እንዲያደርጉብኝ አትተወኝ፡፡ እነርሱ ዐመፃን ይረጫሉ!
\s5
\v 13 በሕያዋን ምድር የያህዌን መልካምነት እንደማይ ባላምን ኖሮ ምን እሆን ነበር?
\v 14 እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ አይዞህ በርታ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ
\s5
\c 28
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ዐለቴ ሆይ፣ ችላ አትበለኝ፡፡ አንተ ዝም ካልኸኝ ወደ መቃብር ከሚወርዱ ጋር እሆናለሁ፡፡
\v 2 እንድትረዳኝ ወደ አንተ በጮኽኩ ጊዜ እጆቼን ወደ ቅዱስ ማደሪያህ በዘረጋሁ ጊዜ የልመኛዬን ቃል ስማ፡፡
\s5
\v 3 ከዐመፀኞች ጋር፣ ክፋትን ከሚያደርጉ ጋር፣ በልባቸው ክፉ ሐሳብ እያለ ከባልንጀራቸው ጋር በሰላም ከሚናገሩ ጋር ጐትተህ አትውሰደኝ፡፡
\v 4 የእጃቸውን ስጣቸው፣ እንደ ዐመፃቸውም ክፈላቸው እንደ ክፉ ተግባራቸው መልስቸው፡፡
\v 5 ለያህዌ ሥራ ግድ ስለሌላቸው፣ ለእጆቹም ተግባር ስፍራ ስላልሰጡ እርሱ ያፈርሳቸዋል፤ መልሶም አይሠራቸውም፡፡
\s5
\v 6 የልመናዬን ቃል ሰምቶአልና ያህዌ ይባረክ፡፡
\v 7 ያህዌ ብርታቴና ጋሻዬ ነው ልቤ በእርሱ ይተማመናል፤ እርሱም ረዳኝ፡፡ ስለዚህ ልቤ ሐሤት አደረገ፤ በዝማሬም አመሰግነዋለሁ፡፡
\v 8 ያህዌ የሕዝቡ ብርታታቸው ነው ለቀባውም የመዳን ዐምባ ነው፡፡
\s5
\v 9 ሕዝብህን አድንን ርስትህንም ባርክ እረኛ ሁናቸው፤ ለዘላለሙም ተንከባከባቸው፡፡
\s5
\c 29
\p
\v 1 እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች ለያህዌ ምስጋና ስጡ ስለ ክብሩና ስለ ብርታቱ ለያህዌ ምስጋና ስጡ፡፡
\v 2 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለያህዌ ስጡ በቅድስናው ውበት ለያህዌ ስገዱ
\s5
\v 3 የያህዌ ድምፅ በውሆች ላይ ያስተጋባል የክብር አምላክ ያንጐዳጉዳል ያህዌ በብዙ ውሆች ላይ ድምፁን ያሰማል፡፡
\v 4 የያህዌ ድምፅ ኃያል ነው የያህዌ ድምፅ ባለ ግርማ ነው፡፡
\v 5 የያህዌ ድምፅ የሊባኖስን ዝግባ ይሰብራል
\s5
\v 6 ሊባኖን እንደ ጥጃ፣ ስርዮንን እንደ ኮርማ ያዘልላል፡፡
\v 7 የያህዌ ድምፅ የእሳት ነበልባል ይረጫል
\v 8 የያህዌ ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል የያህዌ ድምፅ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል፡፡
\s5
\v 9 የያህዌ ድምፅ ወርካዎችን ይወዘውዛል ጫካዎችን ይመነጥራል፡፡ ሁሉም በእርሱ ቤተ መቅደስ፣ «ክብር!» ይላል፡፡
\v 10 ያህዌ በጐርፍ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ተቀምጧል ያህዌ ለዘላለም ይነግሣል፡፡
\s5
\v 11 ያህዌ ለሕዝቡ ብርታት ይሰጣል ያህዌ ሕዝቡን በሰላም ይባርካል፡፡
\s5
\c 30
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ አንተ አንሥተኸኛልና ጠላቶቼም በእኔ ላይ ደስ እንዲላቸው አላደረግህምና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፡፡
\v 2 ያህዌ ሆይ፣ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ጮኽሁ አንተም ፈውሰኸኝ፡፡
\v 3 ያህዌ ሆይ፣ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት ወደ መቃብር ከመውረድም አዳንኸኝ፡፡
\s5
\v 4 እናንት የእርሱ ታማኝ ሕዝቦች ለያህዌ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ፤ ቅድስናውን ስታስታውሱ፣ ውዳሴ ስጡ፡፡
\v 5 ቁጣው ለአጭር ጊዜ ነው ሞገሱ ግን ለዕድሜ ልክ ነው፡፡ ሌሊት ሲለቀስ አድሮ ማለዳ ደስታ ይሆናል፡፡
\s5
\v 6 በልበ ሙሉነት «አልናወጥም!» አልሁ፡፡
\v 7 ያህዌ ሆይ በሞገስህ እንደ ተራራ ብርቱ አደረግኸኝ ፊትህን ስትሰውር ግን ውስጤ ታወከ፡፡
\v 8 ያህዌ፣ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ከጌታም ዘንድ ሞገስ ፈለግሁ፡፡
\s5
\v 9 እኔ ብሞት፣ ወደ መቃብርም ብወርድ ምን ጥቅም አለው? አፈር ያመሰግንሃልን? ታማኝነትህንስ ይናገራልን?
\v 10 ያህዌ ሆይ፣ ስማኝ ማረኝም፣ ያህዌ ረዳት ሁነኝ፡፡
\s5
\v 11 ዋይታዬን ወደ ሽብሸባ ለወጥህልኝ ማቄን አስወግደህ ደስታን አለበስከኝ፡፡
\v 12 እንግዲህ፣ ነፍሴ ታመስግንህ፤ ዝምም አትበል፡፡ አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፡፡
\s5
\c 31
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ አንተን ተማጽኛለሁና እፍረት ከቶ አይድረስብኝ፤ በጽድቅህም ታደገኝ፡፡
\v 2 ጌታ ሆይ፣ አድምጠኝ ፈጥነህም ታደገኝ የመማጸኛ ዐለት፣ የመዳኛም ምሽግ ሁነኝ፡፡
\s5
\v 3 አንተ ዐለቴና ዐምባዬ ነህ ስለ ስምህ ስትል ምራኝ መንገዱንም አሳየኝ፡፡
\v 4 አንተ መታመኛዬ ነህና በስውር ከተዘረጋብኝ ወጥመድ አውጣኝ፡፡
\s5
\v 5 መንፈሴን በእጅህ ዐደራ እሰጣለሁ የእውነት አምላክ ያህዌ ሆይ፣ ተቤዠኝ፡፡
\v 6 ከንቱ ጣዖታትን የሚያገለግሉትን ጠላሁ እኔ ግን በያህዌ እታመናለሁ፡፡
\v 7 መከራዬን አይተሃልና የነፍሴን ጭንቀት ዐውቀሃልና እኔ በኪዳን ታማኝነትህ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አድርጋለሁ፡፡
\s5
\v 8 በጠላቴ እጅ አሳልፈህ አልሰጠኸኝም እግሮቼን ሰፊ ቦታ ላይ አቆምሃቸው፡፡
\v 9 ያህዌ ሆይ፣ ጭንቀት ውስጥ ነኝና ማረኝ ዐይኖቼ በሐዘን ደክመዋል፤ ነፍስና ሥጋዬም ዝለዋል፡፡
\s5
\v 10 ሕይወቴ በጭንቀት ዕድሜዬም በመቃተት አለቀ፡፡ ከኃጢአቴ የተነሣ ጉልበቴ ከዳኝ ዐጥንቴም ደቀቀ፡፡
\v 11 ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ ለጐረቤቶቼ መዘባበቻ ለሚያውቁኝ ሰዎች መሳለቂያ ሆኛለሁ መንገድ ላይ የሚያገኙኝም ይሸሹኛል፡፡
\s5
\v 12 ማንም እንደማያስበው እንደ ሞተ ሰው ተረሳሁ እንደ ተሰበረ የሸክላ ዕቃም ተቆጠርሁ፡፡
\v 13 የብዙዎችን ሹክሹክታ ሰምቻለሁ በዙሪያዬም የሽብር ወሬ አለ በእኔ ላይ ባሤሩ ጊዜ ሕይወቴን ለማጥፋት ዶለቱ፡፡
\s5
\v 14 እኔ ግን ያህዌ ሆይ፣ በአንተ እተማመናለሁ «አንተ አምላኬ ነህ» አልሁ፡፡
\v 15 ዘመኔ ሁሉ በእጅህ ነው፡፡ ከጠላቶቼና ከሚያሳድዱኝ ሰዎች እጅ አድነኝ፡፡
\v 16 ፊትህን ባርያህ ላይ አብራ፡ በኪዳን ታማኝነትህ አድነኝ፡፡
\s5
\v 17 ያህዌ ሆይ፣ አንተን ጠርቻለሁና ለእፍረትና ለውርደት አትዳርገኝ፡፡ ክፉዎች ግን ይፈሩ፤ ይዋረዱ ሲኦል ገብተው ጸጥ ይበሉ፡፡
\v 18 ጻድቁ ላይ በእብሪት የሚናገሩ ትዕቢትና ንቀትን የተሞሉ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ፡፡
\s5
\v 19 ለሚፈሩህ የሰወርኸው፣ በአንተም ለሚታመኑ በሰው ልጆች ሁሉ ፊት የምታደርገው እንዴት ታላቅ ነው!
\v 20 ከሰዎች ሤራ በማደሪያህ ውስጥ ትሸሽጋቸዋለህ፡፡
\s5
\v 21 በተከበበች ከተማ ለእኔ ድንቅ ታማኝነቱን የገለጠ ያህዌ ይባረክ፡፡
\v 22 እኔ ግን ባለ ማስተዋል፣ «ከእንግዲህ ከዐይንህ ፊት ተወግጃለሁ» ብዬ ነበር፤ ሆኖም፣ አንተ እንድትረዳኝ ስጮኽ ሰማኸኝ፡፡
\s5
\v 23 እናንተ ታማኝ ተከታዮቹ ሁሉ ያህዌን ወደዱት ያህዌ ታማኞችን ይጠብቃል ለእብሪተኞች ግን የእጃቸውን ይሰጣቸዋል፡፡
\v 24 እግዚአብሔርን ተስፋ የምታደርጉ ሁሉ በርቱ ልባችሁም ይጽና፡፡
\s5
\c 32
\p
\v 1 መተላለፉ ይቅር የተባለለት ኃጢአቱም የተሸፈነለት ሰው ቡሩክ ነው፡፡
\v 2 ያህዌ በደሉን የማይቆጥርበት በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው ቡሩክ ነው፡፡
\s5
\v 3 ቀኑን ሙሉ በመቃተቴ ዝም ባልሁ ጊዜ፣ አጥንቶቼ ተበላሹ፡፡
\v 4 ቀኑን ሙሉ እጅህ ከብዳኛለች ብርታቴም የበጋ ትኩሳት እንደ መታው ነገር ከውስጤ ተሟጠጠ፡፡ ሴላ
\s5
\v 5 በዚያን ጊዜ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝሁ በደሌንም ከአንተ አልሰወርሁም ደግሞም፣ «መተላለፌን ለያህዌ እናዘዛለሁ» አልሁ አንተም የኃጢአቴን በደል ይቅር አልህ፡፡ ሴላ
\v 6 ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው በጭንቅ ጊዜ ወደ አንተ ይጸልይ ብርቱ ጐርፍ ሞልቶ ቢያጥለቀቅ እንኳ፣ ወደ እነዚህ ሰዎች አይቀርብም፡፡
\s5
\v 7 አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከመከራም ታወጣኛለህ፡፡ በድል ዝማሬ ትከበኛለህ፡፡ ሴላ
\v 8 አስተምርሃለሁ፤ በምትሄድበት መንገድ እመራሃለሁ እመክርሃለሁ ዐይኔንም አንተ ላይ አደርጋለሁ፡፡
\s5
\v 9 ወደምትፈልጉት ቦታ እንዲሄዱላችሁ በልጓምና በልባብ እንደሚገሩት ማስተዋል እንደሌለው ፈረስና በቅሎ አትሁኑ፡፡
\v 10 የክፉዎች ሐዘን ይበዛል በያህዌ የሚታመነውን ግን የእርሱ ኪዳን ታማኝነት ይከብበዋል፡፡
\s5
\v 11 ጻድቃን ሆይ፣ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ልበ ቅኖች ሆይ፣ እልል በሉ፡፡
\s5
\c 33
\p
\v 1 ጻድቃን ሆይ፣ በያህዌ ደስ ይበላችሁ ቅኖች ሊያመሰግኑት ይገባል፡፡
\v 2 ያህዌን በመሰንቆ አመስግት ዐሥር አውታር ባለው በገና ዘምሩለት፡፡
\v 3 አዲስ ዝማሬ አቅርቡለት ባማረ ቅኝት በገና ደርድሩ፤ እልልም በሉ፡፡
\s5
\v 4 የያህዌ ቃል እውነት ነው ሥራውም ሁሉ የታመነ ነው፡፡
\v 5 እርሱ ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል ምድር በያህዌ ኪዳን ታማኝት ተሞልታለች፡፡
\v 6 ያህዌ ሰማያትን በቃሉ የሰማይ ሰራዊትን በአፉ እስትንፋስ ፈጠረ፡፡
\s5
\v 7 የባሕርን ውሆች እንደ ክምር ቀላዩንም በመከማቻ ስፍራ አኖረ፡፡
\v 8 ምድር ሁሉ ያህዌን ትፍራው በዓለም ያሉ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ፡፡
\v 9 እርሱ ተናግሮአልና ሆኑ፤ እርሱ አዞአልና በስፍራቸው ጸኑ፡፡
\s5
\v 10 ያህዌ የሕዝቦችን ምክክር ያጨናግፋል ዕቅዳቸውንም ከንቱ ያደርጋል፡፡
\v 11 የያህዌ ዕቅድ ግን ለዘላለም ይኖራል የልቡም ሐሳቡም ለትውልድ ሁሉ ነው፡፡
\v 12 ያህዌ አምላኩ የሆነለት፣ ርስቱ እንዲሆን የመረጠውም ሕዝብ ቡሩክ ነው፡፡
\s5
\v 13 ያህዌ ከሰማይ ይመለከታል የሰው ልጆችንም ሁሉ ያያል፡፡
\v 14 ከማደሪያው ሆኖ፣ በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ይመለከታል፡፡
\v 15 የሁሉንም ልብ የሠራ እርሱ ነው የሚያደርጉትንም ሁሉ ይመለከታል፡፡
\s5
\v 16 ንጉሥ በሰራዊቱ ብዛት አይድንም፤ ጀግናም በኃይሉ ብርታት አያመልጥም፡፡
\v 17 በፈረስ ድል አደርጋለሁ ማለት ከንቱ ተስፋ ነው፤ በብርቱ ጉልበቱም ማንም አይድንም
\s5
\v 18 እነሆ፣ የያህዌ ዐይኖች በሚፈሩት ላይ ናቸው፤ በኪዳን ታማኝነቱ በሚታመኑት ላይ አትኩረዋል፡፡
\v 19 ይህም የሚሆነው ከሞት ሊያድናቸውና ከራብ ዘመንም ሊጠብቃቸው ነው፡፡
\s5
\v 20 ያህዌን በተስፋ እንጠብቃለን እርሱ ረድኤታችንና ጋሻችን ነው፡፡
\v 21 በቅዱስ ስሙ ተማምነናልና ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋል፡፡
\s5
\v 22 ያህዌ ሆይ፣ ተስፋችንን አንተ ላይ አድርገናልና ምሕረትህ በእኛ ላይ ይሁን፡፡
\s5
\c 34
\p
\v 1 ያህዌን ሁልጊዜ አመሰግናለሁ ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው፡፡
\s5
\v 2 ያህዌን አመሰግናለሁ! ትሑታን ይህን ሰምተው ደስ ይበላቸው፡፡
\v 3 ያህዌን ከእኔ ጋር አመስግኑት በአንድነት ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ፡፡
\s5
\v 4 ያህዌን ፈለግሁ እርሱም መለሰልኝ ከፍርሃቴም ሁሉ አዳነኝ፡፡
\v 5 ወደ እርሱ የሚመለከቱ ያበራሉ ፊታቸውም በፍጹም አያፍርም፡፡
\v 6 ይህ ችግረኛ ጮኸ እግዚአብሔርም ሰማው ከመከራውም ሁሉ አዳነው፡፡
\s5
\v 7 የያህዌ መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸዋልም፡፡
\v 8 ያህዌ መልካም መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ፡፡ በእርሱ የተማመነ ሰው ቡሩክ ነው፡፡
\v 9 እናንተ ቅዱሳን ያህዌን ፍሩ እርሱን የሚፈሩ አንዳች አያጡምና፡፡
\s5
\v 10 አንበሶች ሊያጡ ሊራቡም ይችላሉ ያህዌን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም፡፡
\v 11 ልጆቼ ሆይ፣ ኑ ስሙኝ ያህዌን መፍራት አስተምራችኋለሁ፡፡
\s5
\v 12 ሕይወትን የሚወድ፣ መልካም ነገርን ለማየት ረጅም ዕድሜ የሚፈልግ ማነው?
\v 13 እንግዲያስ አንደበትህን ከክፉ ከልክል ከንፈርህንም ከውሸት ጠብቅ፡፡
\v 14 ከክፉ ሽሽ፤ መልካሙንም አድርግ ሰላምን ፈልጋት ደግሞም ተከተላት፡፡
\s5
\v 15 የያህዌ ዐይኖች ጻድቃን ላይ ናቸው፡፡ ጆሮዎቹም ለጩኸታቸው ተከፍተዋል፡፡
\v 16 መታሰቢያቸውን ከምድር ላይ ለማጥፋት የያህዌ ፊት ክፉ በሚያደርጉ ላይ ነው።
\v 17 ጻድቃን ወደ ያህዌ ይጮኻሉ እርሱም ይሰማቸዋል፤ ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል፡፡
\s5
\v 18 ያህዌ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል፡፡
\v 19 የጻድቅ መከራው ብዙ ነው ያህዌ ግን ከሁሉም ያድነዋል፡፡
\v 20 ዐጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይሰበርም፡፡
\s5
\v 21 ኃጢአተኛን ክፋት ይገድለዋል ጻድቃንን የሚጠሉ ይፈርድባቸዋል፡፡
\v 22 ያህዌ የባርያዎቹን ነፍስ ይታደጋል እርሱንም መጠጊያ ያደረገ አይፈረድበትም፡፡
\s5
\c 35
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ የሚቃወሙኝን ተቃወማቸው፤ የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው፡፡
\v 2 ትልቁንና ትንሹን ጋሻ ያዝ እኔንም ለመርዳት ተነሥ፡፡
\v 3 በሚያሳድዱኝ ላይ ጦርና ሰይፍህን ምዘዝና ነፍሴን «እኔ አዳኝሽ ነኝ» በላት፡፡
\s5
\v 4 ሕይወቴን የሚፈልጓት ይፈሩ ይዋረዱም እኔን ለመጉዳት የሚያደቡ አፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ፤ ግራ ይጋቡ፡፡
\v 5 በነፋስ ፊት እንዳለ እብቅ ይሁኑ የያህዌም መልአክ ያሳድዳቸው፡፡
\v 6 መንገዳቸው ጨለማና ድጥ ይሁን የያህዌ መልአክ ያባርራቸው፡፡
\s5
\v 7 ያለ ምክንያት ወጥመድ ዘርግተውብኛል ያለ ምክንያት ሕይወቴን ለማጥፋት ጉድጓድ ቆፍረዋል፡፡
\v 8 ጥፋት በድንገት ይምጣባቸው የዘረጉት ወጥመድ ይያዛቸው ጉድጓድ ውስጥ ወድቀው ይጥፉ፡፡
\s5
\v 9 እኔ ግን በያህዌ ደስ ይለኛል በማዳኑም ሐሤት አደርጋለሁ፡፡
\v 10 ዐጥንቶቼ ሁሉ፣ «ያህዌ ሆይ፣ ድኻውን ከእርሱ ከሚበረቱ፣ ችግረናውንና ምስኪኑን ከቀማኞች እጅ የሚያድን እንደ አንተ ያለ ማን ነው?» እለዋለሁ፡፡
\s5
\v 11 ሐሰተኛ ምስክሮች ተነሥተውብኛል በሐሰትም ይከስሱኛል፡፡
\v 12 እኔን ብቸኛ አድርገው በመልካም ፈንታ ክፉ መለሱልኝ፡፡
\s5
\v 13 እኔ ግን እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፤ ለእነርሱ ጾምሁ፤ አንገቴን ደፋሁ፡፡
\v 14 ለወንድሙ እንደሚያለቅስ ሰው አዘንሁ ለእናቱ ልጅ እንደሚያዝን ሰው ሆንሁ፡፡
\s5
\v 15 እኔ በተሰናከልሁ ጊዜ ደስ ብሎአቸው ተሰበሰቡ ግፈኞች በድንገት ተሰበሰቡብኝ ያለ ዕረፍትም ቦጫጨቁኝ፡፡
\v 16 እንደ ምናምንቴዎች አፌዙብኝ ጥርሳቸውንም አፋጩብኝ፡፡
\s5
\v 17 ጌታ ሆይ፣ እስከ መቼ ዝም ብለህ ታያለህ? ነፍሴን በእነርሱ ከመጠቃት ሕይወቴንም ከአንበሶች አድናት፡፡
\v 18 በታላቅ ጉባኤ መካከል አመሰግንሃለሁ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበትም እወድስሃለሁ፡፡
\s5
\v 19 ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ እንዲላቸው፣ ተንኰላቸውንም እንዲፈጽሙብኝ አታድርግ፡፡
\v 20 የሰላም ቃል ከአፋቸው አይወጣም ነገር ግን በምድሪቱ በጸጥታ በሚኖሩት ላይ ተንኮል ይሸርባሉ፡፡
\s5
\v 21 አፋቸውን አስፍተው በመክፈት፣ «እሰይ! እሰይ! በዐይናችን አየነው» አሉ፡፡
\v 22 ያህዌ ሆይ፣ ይህን አይተሃልና ዝም አትበል ጌታ ሆይ፣ ለእኔም አትራቅ፡፡
\v 23 አምላኬ ጌታዬ፣ ለእኔ ለመሟገት ተነሥ ልትከራከርልኝም ተንቀሳቀስ፤
\s5
\v 24 ያህዌ ሆይ፣ በጽድቅህ ፍረድልኝ በእኔም ላይ ደስ አይበላቸው፡፡
\v 25 በልባቸው፣ «እሰይ፣ ያሰብነው ተሳካ» አይበሉ፤ «ዋጥ አደረግነውም» አይበሉ፡፡
\v 26 በጭንቀቴ ደስ የሚላቸው ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፡፡ በእኔ ላይ የሚያፌዙ፤ እፍረትና ውርደት ይልበሱ፡፡
\s5
\v 27 ፍትሕ ማግኘቴን የሚፈልጉ እልል ይበሉ ሐሤትም ያድርጉ፣ ዘወትርም፣ «የባርያው ሰላም ደስ የሚለው ያህዌ ይመስገን» ይበሉ፡፡
\v 28 ያኔ የአንተን ጽድቅ እናገራለሁ ቀኑን ሙሉ አመሰግንሃለሁ፡፡
\s5
\c 36
\p
\v 1 ክፉ ሰው በልቡ፣ ክፋትን ያስባል በዐይኖቹም ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም፡፡
\v 2 በደሉ ግልጽ ወጥቶ እንዳይጠላ እያሰበ ራሱን ይሸነግላል፡፡
\s5
\v 3 ንግግሩ ተንኰልንና ሐሰትን የተሞላ ነው፤ አስተዋይ መሆንንና መልካም ማድረግን አይፈልግም፡፡
\v 4 በመኝታው ላይ ክፋት ያውጠነጥናል ራሱን ወደ ክፉ መንገድ ይመራል ክፉውንም ነገር አያርቅም፡፡
\s5
\v 5 ያህዌ ሆይ፣ ታማኝነትህ እስከ ሰማይ እውነተኛነትህም እስከ ደመናት ይደርሳል፡፡
\v 6 ጽድቅህ እንደ እግዚአብሔር ተራራ ነው ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ነው፡፡ ያህዌ ሆይ፣ አንተ ሰውንም እንስሳንም ትጠብቃለህ፡፡
\s5
\v 7 እግዚአብሔር ሆይ፣ ታማኝነትህ እንዴት ክቡር ነው! የሰው ልጆች ሁሉ በክንፎችህ ጥላ ሥር መጠጊያ ያገኛሉ፡፡
\v 8 ከቤትህ ሲሳይ ተመግበው ይጠግባሉ፤ ከበረከትህም ወንዝ ይጠጣሉ፡፡
\v 9 በአንተ ዘንድ የሕይወት ምንጭ አለ በአንተ ብርሃን ብርሃን እናያለን፡፡
\s5
\v 10 ለሚያውቁህ ምሕረትህ፣ ልባቸውም ለቀና ጽድቅህ አይቋረጥባቸው፡፡
\v 11 የእብሪተኛ እግር አይቅረበኝ የክፉ ሰው እጅም አያሳድደኝ፡፡
\v 12 ክፉ አድራጊዎች እንዴት እንደ ወደቁ መነሣትም እንደማይችሉ ተመልከት፡፡
\s5
\c 37
\p
\v 1 በክፉዎች ምክንያት አትበሳጭ ኃጢአት በሚሠሩም አትቅና፤
\v 2 እንደ ሣር ቶሎ ይደርቃሉና እንደ ለመለመ ቅጠልም ይጠወልጋሉ፡፡
\s5
\v 3 በያህዌ ተማመን፤ መልካምንም አድርግ በምድሪቱ ተቀመጥ፤ ታምነህም ተሰማራ፡፡
\v 4 በያህዌ ደስ ይበልህ የልብህንም ፍላጐት ይሰጥሃል፡፡
\s5
\v 5 መንገድህን ለያህዌ አደራ ስጥ በእርሱ ታመን እርሱም ያከናውንልሃል፡፡
\v 6 ጽድቅህን እንደ ብርሃን ያንተንም ንጽሕና እንደ ቀትር ፀሐይ ያበራዋል፡፡
\s5
\v 7 በያህዌ ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግሥትም ተጠባበቀው፡፡ ነገር በተሳካለት፣ ክፋትንም በሚሸርብ ሰው አትቅና
\s5
\v 8 አትቆጣ፤ ተስፋም አትቁረጥ መከራን ከማብዛቱ ውጪ ምንም ስለማይጠቅምህ አትከፋ፡፡
\v 9 ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉ ያህዌን የሚጠባበቁ ግን ምድሪቱን ይወርሳሉ፡፡
\v 10 ብዙም ሳይቆይ ክፉ ሰው ይጠፋል ብትፈልግም ቦታውን አታገኘውም፡፡
\s5
\v 11 ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ በታላቅ ሰላምም ደስ ይላቸዋል፡፡
\v 12 ክፉዎች ጻድቃን ላይ ያሤራሉ ጥርሳቸውንም ያፋጩባቸዋል፡፡
\v 13 መጥፊያ ቀናቸው እንደ ደረሰ ስለሚያውቅ ጌታ ይስቅባቸዋል፡፡
\s5
\v 14 ድኾችንና ችግረኞችን ለመጣል ልበ ቅኖችንም ለመግደል ክፉዎች ሰይፋቸውን መዘዙ፤ ቀስታቸውንም ገተሩ፡፡
\v 15 ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል ቀስታቸውም ይሰበራል፡፡
\s5
\v 16 ከክፉ ሰው ብዙ ሀብት ይልቅ፣ የጻድቅ ጥቂት ሀብት ይበልጣል፡፡
\v 17 የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና ያህዌ ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል፡፡
\s5
\v 18 ያህዌ ያለ ነቀፋ የሚመላለሱትን ዕለት ዕለት ይጠብቃቸዋል፡፡ ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል፡፡
\v 19 በክፉ ቀን አያፍሩም በራብ ዘመንም የሚበሉትን አያጡም፡፡
\s5
\v 20 ክፉዎች ግን ይጠፋሉ የያህዌ ጠላቶች እንደ መስክ ውበት ይሆናሉ፡፡ እንደ ጢስም በንነው ይጠፋሉ፡፡
\v 21 ኃጢአተኛ ይበደራል፣ ግን መልሶ አይከፍልም ጻድቅ ግን በልግስና ይሰጣል፡፡
\s5
\v 22 እግዚአብሔር የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ እርሱ የረገማቸው ግን ይጠፋሉ፡፡
\v 23 የሰውን አካሄድ የሚያጸና ያህዌ ነው በመንገዱም ደስ ይለዋል፡፡
\v 24 ያህዌ በእጁ ደግፎ ስለሚይዘው ቢሰናከል እንኳ አይወድቅም፡፡
\s5
\v 25 ጐልማሳ ነበርሁ፤ አሁን አርጅቻለሁ ጻድቅ ሲጣል፣ ዘሩም እንጀራ ስለምን አላየሁም፡፡
\v 26 ጻድቅ ሁልጊዜ በልግሥና ይሰጣል፣ ደግሞም ያበድራል ልጆቹም የተባረኩ ይሆናሉ፡፡
\v 27 ከክፉ ራቅ መልሙንም አድርግ ለዘላለምም በሰላም ትኖራለህ፡፡
\s5
\v 28 ያህዌ ፍትሕ ይወዳልና ታማኞቹንም በፍጹም አይጥልም፤ ለዘላለምም ይጠብቃቸዋል፡፡ የኃጢአተኛው ዘር ግን ይጠፋል፡፡
\v 29 ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ በእርሷም ለዘላለም ይኖራሉ፡፡
\v 30 የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል አንደበቱም ፍትሕን ያወራል፡፡
\s5
\v 31 የአምላኩ ሕግ ልቡ ውስጥ ነው አካሄዱም አይሰናከልም፡፡
\v 32 ኃጢአተኛው ጻድቅን ይመለከተዋል ሊገድለውም ይፈልጋል፡፡
\v 33 እግዚአብሔር ግን በእጁ አይጥለውም ፍርድ ፊት ሲቀርቡም አይረታም፡፡
\s5
\v 34 ያህዌን ደጅ ጥና፤ መንገዱንም ጠብቅ እርሱም ምድርን እንድትወርስ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፡፡ ክፉዎች ሲጠፋ ታያለህ፡፡
\s5
\v 35 ክፉና ጨካኙን ሰው ምቹ መሬት ላይ እንዳለ ዛፍ ለምልሞ አየሁት
\v 36 ተመልሼ ስመጣ ግን በቦታው አልበረም፤ ፈለግሁ ላገኘው ግን አልቻልሁም፡፡
\s5
\v 37 ጻድቅን ሰው ተመልከት ቅን የሆነውንም ሰው እይ የሰላም ሰው ተስፋ አለውና፡፡
\v 38 ኃጠአተኞች ግን ፈጽሞ ይደመስሳሉ ዘራቸውም ይወገዳል፡፡
\s5
\v 39 የጻድቃን ድነት ከያህዌ ዘንድ ነው በመከራም ጊዜ ይጠብቃቸዋል፡፡
\v 40 ያህዌ ይረዳቸዋል፤ ደግሞም ይታደጋቸዋል፡፡ ከክፉዎች እጅ ነጥቆ ያወጣቸዋል እርሱን መጠጊያ አድርገዋልና ያድናቸዋል፡፡
\s5
\c 38
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ በቁጣህ አትገሥጸኝ በመዓትህም አትቅጣኝ፡፡
\v 2 ፍላጻዎችህ ወግተውኛልና እጅህ ተጭናኛለች፡፡
\s5
\v 3 ከቁጣህ የተነሣ መላው አካሌ ታመመ ከኃጢአቴ የተነሣም ዐጥንቶቼ ጤና የላቸውም፡፡
\v 4 በደሌ ውጦኛል እንደ ከባድ ሸክምም ተጭኖኛል፡፡
\s5
\v 5 በሞኝነት ካደረግሁት የተነሣ ቁስሌ መገለ፤ ሸተተም፡፡
\v 6 ጐበጥሁ፤ በየቀኑም እያጐነበስኩ ሄድሁ ቀኑን ሙሉ በትካዜ ዋልሁ፡፡
\s5
\v 7 ውስጤ እንደ እሳት ይቃጠላል ሥጋዬም ጤና የለውም፡፡
\v 8 እንደ ዲዳ ሆንሁ፤ ፈጽሞም ደቀቅሁ ከልቤ ምሬት የተነሣ እቃትታለሁ፡፡
\s5
\v 9 ጌታ ሆይ፣ የጥልቅ ልቤን ናፍቆት አንተ ታውቃለህ መቃተቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም፡፡
\v 10 ልቤ በኃይል ይመታል፤ ጉልበት ከድቶኛል የዐይኔም ብርሃን ፈዝዞአል፡፡
\s5
\v 11 ካለሁበት ሁኔታ የተነሣ፣ ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ሸሹኝ ጐረቤቶቼም ርቀው ቆሙ፡፡
\v 12 ሕይወቴን ማጥፋት የሚወዱ ወጥመድ ዘረጉብኝ ሊጐዱኝ የሚፈልጉም በዛቻ ተናገሩኝ፤ በእኔም ላይ ቀኑን ሙሉ ያሤራሉ፡፡
\s5
\v 13 እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቆሮ ምንም መናገር እንደማይችል ዲዳ ሰው ሆንሁ፡፡
\v 14 ጆሮው እንደማይሰማ አንደበቱም መልስ መስጠት እንደማይችል ሰው ሆንሁ፡፡
\s5
\v 15 ያህዌ ሆይ፣ በፍጹም ልቤ አንተን እጠብቃለሁ ጌታ ሆይ፣ አንተ መልስ ትሰጠኛለህ፡፡
\v 16 ይህን የምለው ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ እንዳይላቸው ነው፤ እግሬ ቢንሸራተት ክፉ ነገር ያደርጉብኛል፡፡
\s5
\v 17 ልወድቅ ተቃርቤአለሁ ሕመሜም ፋታ አልሰጠኝም፡፡
\v 18 በደሌን እናዘዛለሁ ኃጢአቴም አስጨንቆኛል፡፡
\s5
\v 19 ጠላቶቼ እጅግ ብዙ ናቸው ያለ ምክንያት የሚጠሉንም በዝተዋል፡፡
\v 20 በመልካም ፈንታ ክፉ መለሱልኝ መልሙን እየተከተልሁ ቢሆንም፣ እነርሱ ግን እኔ ላይ የሐሰት ክስ ደረደሩ፡፡
\s5
\v 21 ያህዌ ሆይ፣ አትተወኝ አምላኬ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ
\v 22 ጌታ መድኃኒቴ እኔን ለመርዳት ፍጠን፡፡
\s5
\c 39
\p
\v 1 እኔ፣ «በአንደበቴ እንዳልበድል ለምናገረው እጠነቀቃለሁ፣ በክፉዎችም ፊት እስካለሁ ድረስ፣ በአፌ ልጓም አደርጋለሁ» አልሁ፡፡
\s5
\v 2 አንድ ቃል እንኳ ሳልናገር ዝም አልሁ ለመልካም ነገር እንኳ አፌን ዘጋሁ፤ ያም ሆኖ ጭንቀቴ ባሰ፡፡
\v 3 ልቤ በውስጤ ጋለ ስለ እነዚህ ነገሮች ሳስብ እንደ እሳት ነደደ፡፡ ከዚያም መናገር ጀመርሁ፡፡
\s5
\v 4 «ያህዌ ሆይ፣ የሕይወቴ መጨረሻ መቼ እንደ ሆነና የዕድሜዬን ልክ አሳውቀኝ አላፊ ጠፊ መሆኔን አሳየኝ፡፡
\v 5 እነሆ፣ ዘመኔን በስንዝር ለክተህ አኖርህ ዕድሜዬም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው፡፡ በእርግጥ የሰው ሁሉ ሕይወት ጥላ ነው፡፡ ሴላ
\s5
\v 6 በእርግጥ ሰው ሁሉ እንደ ጥላ ይመላለሳል፡፡ ለማን እንደሚሆን ሳያውቅ ሀብት ንብረት ያከማቻል፡፡
\v 7 ጌታ ሆይ፣ አሁንስ ማንን ልጠብቅ? ተስፋዬ አንተ ብቻ ነህ፡፡
\s5
\v 8 ከኃጢአቴ አድነኝ የሞኞች መዘባበቻ አታድርገኝ፡፡
\v 9 ይህን ያደረግህ አንተ ነህና ዝም እላለሁ አፌንም አልከፍትም፡፡
\s5
\v 10 ክንድህን አንሣልኝ ከእጅህ ምት የተነሣ ዝዬአለሁ፡፡
\v 11 ሰውን በኃጢአቱ ትገሥጸዋለህ፤ ትቀጣዋለህም የሚወደውንም ነገር እንደ ብል ታጠፋበታለህ፡፡ በእርግጥ ሰው ሁሉ ተን ነው፡፡ ሴላ
\s5
\v 12 ያህዌ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ ለቅሶየንም ቸል አትበል፡፡ በአንተ ፊት እንደ መጻተኛ ነኝና እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝ፡፡
\v 13 ከመሞቴ በፊት ዳግመኛ ደስ እንዲለኝ ዐይንህን ከላዬ አንሣ፡፡
\s5
\c 40
\p
\v 1 በትዕግሥት ያህዌን ደጅ ጠናሁት እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማኝ፡፡
\v 2 ከአደገኛ ጉድጓድ፣ ከሚያዘቅጥም ጭቃ አወጣኝ፤ እግሮቼን፣ በዐለት ላይ አቆመ አካሄዴንም አጸና፡፡
\s5
\v 3 ለአምላካችን ምስጋና አዲስ መዝሙር በአፌ አኖረ፡፡ ብዙዎች ዐይተው ያከብሩታል፤ በያህዌም ይታመናሉ፡፡
\v 4 ያህዌን መታመኛው ያደረገ ወደ ትዕቢተኛው የማይመለከት የሐሰት አማልክት ወደሚከተሉት የሚያይ ቡሩክ ነው፡፡
\s5
\v 5 ያህዌ አምላኬ ሆይ፣ ያደረግኸው ድንቅ ነገር ብዙ ነው ለእኛ ያለህም ሐሳብ ከቁጥር በላይ ነው፤ ላወራው ልናገረው ብል ስፍር ቁጥር አይኖረውም፡፡
\v 6 መሥዋዕትንና መባን አልፈለግህም ጆሮዎቼን ግን ከፈትህ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትንና የኃጢአት መሥዋዕትን አልጠየቅህም፡፡
\s5
\v 7 እኔም እንዲህ አልሁ፣ «እነሆ፣ መጥቻለሁ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ ተጽፎአል፤
\v 8 አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ ሕግህም ልቤ ውስጥ ነው፡፡
\v 9 በታላቅ ጉባኤ ውስጥ ጽድቅህን ዐወጅሁ ያህዌ ሆይ፣ ይህን ከማድረግ ወደ ኋላ አለማለቴንም አንተ ታውቃለህ፡፡
\s5
\v 10 ጽድቅህን በልቤ ውስጥ አልሸሸግሁም፤ ታማኝነትህንና ማዳንህን ተናገርሁ ምሕረትህንና እውነትህን ከታላቅ ጉባኤ አልደበቅሁም፡፡
\v 11 ያህዌ ሆይ ምሕረትህን አትንፈገኝ ቸርነትህና ታማኝነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ፡፡
\s5
\v 12 ስፍር ቁጥር የሌለው ችግር ከብቦኛል የኃጢአቴ ብዛት ስለ ያዘኝ ማየት ተስኖኛል፤ ከራሴ ጠጉር ይልቅ በዝቶአል፤ ልቤም ከድቶኛል፡፡
\v 13 ያህዌ ሆይ፣ እኔን ለማዳን ፈቃድህ ይሁን እኔን ለመርዳትም ፍጠን፡፡
\s5
\v 14 ነፍሴን ለመንጠቅ የሚፈልጉ ይፈሩ፤ ይዋረዱም፡፡ ጉዳቴን የሚሹ ተዋርደው በመጡበት ይመለሱ፡፡
\v 15 በእኔ ላይ፣ «እሰይ! እሰይ!» የሚሉ በራሳቸው እፍረት ይደንግጡ
\s5
\v 16 አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፤ ማዳንህን የሚወዱ ዘወትር፣ «ያህዌ ከፍ ከፍ ይበል» ይበሉ፡፡
\v 17 እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ ጌታ ግን ያስብልኛል፡፡ አንተ ረዳቴ ነህ እኔን ለማዳን ፍጠን አምላኬ ሆይ አትዘግይ፡፡
\s5
\c 41
\p
\v 1 ለድኾች የሚያስብ ቡሩክ ነው እርሱንም በመከራ ቀን ያህዌ ያድነዋል፡፡
\v 2 ያህዌ ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል በምድርም ላይ ይባርከዋል ለጠላቶቹ ምኞትም አሳልፎ አይሰጠውም፡፡
\v 3 ታሞ በተኛበት አልጋ ያህዌ ይንከባከበዋል በበሽታውም ጊዜ መኝታውን ያነጥፍለታል፡፡
\s5
\v 4 እኔም፣ «ያህዌ ሆይ፣ ማረኝ! በአንተ ላይ ኃጢአት አድርጌአለሁና ፈውሰኝ» አልሁ፡፡
\v 5 «የሚሞተው መቼ ነው፤ ስሙ የሚደመሰሰውስ መቼ ነው?» እያሉ ጠላቶቼ እኔ ላይ ክፉ ይናገራሉ፡፡
\v 6 ሊጠይቀኝ ቢመጣ እንኳ በልቡ ስድብ እያመቀ ከአንገት በላይ ይናገራል ወጥቶም ወሬ ይነዛል፡፡
\s5
\v 7 ጠላቶቼ ሁሉ ተባብረው እኔ ላይ ያሾኮሽካሉ የክፋ ነገርም በላዬ ያውጠነጥናሉ
\v 8 «ክፉ ደዌ ይዞታል፤ አልጋ ላይ ወድቋል ከእንግዲህ ከተኛበት አይነሣም» ይላሉ።
\v 9 እንጀራዬን ተካፍሎ የበላ የተማመንሁበት የቅርብ ወዳጄ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ፡፡
\s5
\v 10 አንተ ግን ያህዌ ሆይ ማረኝ፤ የእጃቸውን እንድሰጣቸውም አስነሣኝ፡፡
\v 11 ጠላቴ በእኔ ላይ ድል አላገኘምና እንደ ወደድከኝ በዚህ ዐወቅሁ፡፡
\v 12 ስለ ቅንነቴ እኔን ትረዳኛለህ በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ፡፡
\s5
\v 13 የእስራኤል አምላክ ያህዌ ከዘላለም እስከ ዘለላለም ይመስገን፡፡ አሜን አሜን፡፡
\s5
\c 42
\p
\v 1 ዋላ የምንጭ ውሃ እንደሚናፍቅ አምላኬ ሆይ፣ እኔም እግዚአብሔርን ተጠማሁ፡፡
\v 2 መቼ ደርሼ ነው የአምላክን ፊት የማየው?
\s5
\v 3 ጠላቶቼ ዘወትር፣ «አምላክህ የት አለ?» ስለሚሉኝ እንባዬ ቀንና ሌሊት ምግቤ ሆነ፡፡
\v 4 ነፍሴ በውስጤ እየፈሰሰች እነዚህን ነገሮች አስታውሳለሁ፣ ታላቅ ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ቤት እየመራሁ በአእላፍ ሕዝብ መካከል በእልልታና በምስጋና መዝሙር እንዴት ከሕዝቡ ጋር እሄድ እንደ ነበር ትዝ አለኝ፡፡
\s5
\v 5 ነፍሴ ሆይ፣ ለምን ታዝኛለሽ? በውስጤስ ለምን ትታወኪያለሽ? የመድኃኒቴን አምላክ ዳግመኛ እንዳመሰግነው እግዚአብሔርን ተስፋሽ አድርጊ፡፡
\v 6 አምላኬ ሆይ፣ ነፍሴ በውስጤ አዝናለች ስለዚህ በዮርዳኖስ ምድር፣ ከአርሞንኤም ተራራ ጫፍ በሚዛር ተራራ አስብሃለሁ፡፡
\s5
\v 7 በፏፏቴህ ድምፅ ጥልቁ ጥልቁን ይጠራል ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በእኔ ላይ አለፈ፡፡
\v 8 ያም ሆኖ፣ ያህዌ ምሕረቱን በቀን ያዛል በሌሊትም ዝማሬው በእኔ ዘንድ አለ ይህም ለሕይወቴ አምላክ የማቀርበው ጸሎት ነው፡፡
\s5
\v 9 እግዚአብሔር ዐለቴን፣ «ለምን ረሳኸኝ? ጠላቴ ከደረሰብኝ ጭንቀት የተነሣ ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?» እለዋለሁ፡፡
\v 10 ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ፣ «አምክህ የት አለ?» እያሉ የሚያደርሱብን ፌዝ ዐጥንቶቼ ውስጥ እንደ ሰይፍ ሆነ፡፡
\s5
\v 11 ነፍሴ ሆይ፣ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? የመድኃኒቴን አምላክ ዳግመኛ እንዳመሰግነው እግዚአብሔርን ተስፋሽ አድርጊ፡፡
\s5
\c 43
\p
\v 1 አምላክ ሆይ፣ ፍረድልኝ ከጽድቅ ከራቀ ሕዝብ ጋር ተሟገትልኝ፡፡
\v 2 አምላክ ሆይ፣ አንተ ብርታቴ ነህ ለምን ተውኸኝ? ጠላት እያስጨነቀኝ ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?
\s5
\v 3 ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እኔንም ይምሩኝ፡፡ ወደ ቅዱስ ኮረብታህና ወደ ማደሪያህ ያድርሱኝ፡፡
\v 4 እኔም ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ እሄዳለሁ ፍጹም ደስታዬ ወደ ሆነው አምላኬ አቀናለሁ፡፡ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣ በበገና አመሰግንሃለሁ፡፡
\s5
\v 5 ነፍሴ ሆይ፣ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? የመድኃኒቴን አምላክ ዳግመኛ እንዳመሰግነው እግዚአብሔርን ተስፋሽ አድርጊ፡፡
\s5
\c 44
\p
\v 1 አምላክ ሆይ፣ በጆሮአችን ሰምተናል በቀድሞ ዘመን እነርሱ በነበሩበት ዘመን ያደረግኸውን አባቶቻችን ነግረውናል፡፡
\v 2 ሕዝቦችን በእጅህ አሳድዶህ አስወጣህ የእኛን ሕዝብ ግን ተከልህ ሕዝቦችን አደቀቅህ የእኛ ሕዝብ ግን በምድሩ እንዲኖር አደረግህ፡፡
\s5
\v 3 ምድሪቱን የወረሳት በሰይፋቸው አልነበረም፣ ያዳናቸውም የገዛ ክንዳቸው አልነበረም አንተ ወደድሃቸውና ቀኝ እጅህ፣ ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አደረገ፡፡
\v 4 እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ንጉሤ ነህ ያዕቆብ ድል እንዲያገኝ የወሰንህ አንተ ነህ፡፡
\s5
\v 5 በአንተ ርዳታ ጠላቶቻችንን ድል እንነሣለን በስምህም ተቃዋሚዎቻችንን እንረግጣለን፡፡
\v 6 በቀስቴ አልተማመንምና ሰይፌም አያድነኝም፡፡
\s5
\v 7 አንተ ግን ከጠላቶቻችን አዳንኸን የሚጠሉንንም አሳፈርሃቸው፡፡
\v 8 ዘወትር በእግዚአብሔር እንመካለን ለዘላለምም ስምህን እንወድሳለን፡፡ ሴላ
\s5
\v 9 አሁን ግን ትተኸናል ለውርደትም ዳርገኸናል ከሰራዊታችንም ጋር አትወጣም፡፡
\v 10 ከጠላት ፊት እንድንሸሽ አደረግህ ባላንጣዎቻችንም ዘረፉን፡፡
\v 11 እንደሚታረዱ በጐች አደረግኸን በሕዝቦችም መካከል በተንኸን፡፡
\s5
\v 12 ሕዝብህን በርካሽ ዋጋ ሸጥኸው ከሽያጩም ያተረፍኸው የለም፡፡
\v 13 ለጐረቤቶቻችን ማፈሪያ በዙሪያችን ላሉትም መሣቂያና መዘባበቻ አደረግኸን፡፡
\v 14 በሕዝቦች ዘንድ ስድብ፣ በሰዎችም መካከል ራስ የሚነቀነቅብን አደረግኸን፡፡
\s5
\v 15 ውርደቴ ዘወትር በፊቴ ነው ፊቴም እፍረትን ተከናንቦአል፡፡
\v 16 ይህም ከዘላፊውና ከተሳዳቢው ድምፅ የተነሣ ከጠላትና ከተበቃይ የተነሣ ነው፡፡
\v 17 ይህ ሁሉ ቢደርስብንም፣ አንተን ግን አልረሳንም ለኪዳንህ ታማኝ መሆንንም አልተውንም፡፡
\s5
\v 18 ልባችን ከአንተ አልተመለሰም ርምጃችንም ከመንገድህ ወደ ኋላ አላለም፡፡
\v 19 አንተ ግን ተኩላዎች በሚውሉበት ቦታ ሰባብረህ ጣልኸን፤ በሞት ጥላም ሸፈንኸን፡፡
\v 20 የአምካችንን ስም ረስተን፣ እጆቻችንን ለባዕድ አማልክት ዘርግተን ቢሆን ኖሮ፣
\v 21 እግዚአብሔር ይህን ማወቅ ይሣነዋልን? እርሱ የሰውን ልብ ምስጢር የሚረዳ ነውና፡፡
\v 22 ያም ሆኖ፣ ቀኑን ሙሉ ስለ አንተ እንገደላለን እንደሚታረዱ በጐችም ተቆጠርን፡፡
\s5
\v 23 ጌታ ሆይ ንቃ፣ ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፣ ለዘላለምም አትተወን፡፡
\v 24 ፊትህን ለምን ከእኛ ትሰውራለህ? መከራና ጭንቀታችን ለምን ችላ ትላለህ?
\s5
\v 25 እስከ ምድር ትቢያ ድረስ ወርደናል አካላችን ከምድር ጋር ተጣብቆአል፡፡
\v 26 እኛን ለመርዳት ተነሥ ስለ ኪዳን ታማኝነትህ ስትል ተቤዠን፡፡
\s5
\c 45
\p
\v 1 ልቤ መልካም ሐሳብ አፈለቀ ለንጉሡ የተቀኘሁትን ቅኔ አሰማለሁ አንደበቴ እንደ መልካም ጸሐፊ ብዕር ነው፡፡
\v 2 አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ ከከንፈሮችህ ጸጋ ይፈስሳል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ባርኮሃል፡፡
\s5
\v 3 ኃያል ሆይ፣ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ ግርማ ሞገስንም ተላበስ
\v 4 ስለ እውነት ስለ ፍትሕ ግርማን ተጐናጽፈህ ድል ለማድረግ ገሥግሥ ቀን እጅህ ድንቅ ነገር ታሳይ፡፡
\s5
\v 5 ፍላጻዎችን የሾሉ ናቸው ሕዝቦች ከእግርህ በታች ይወድቃሉ፡፡ ፍላጻዎችህ የንጉሡ ጠላቶችን ልብ ይወጋል፡፡
\v 6 አምላክ ሆይ፣ ዙፋንህ የዘላለም ዙፋን ነው በትረ መንግሥትህም የፍትሕ በትረ መንግሥት ነው፡፡
\v 7 ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃንም ጠላህ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ፡፡
\s5
\v 8 ልብስህ ሁሉ ከከርቤ፣ ከእሬትና ከብርጉድ በተቀመመ ሽቱ ያውዳል፤ በዝሆን ጥርስ ከተዋቡ ቤተ መንግሥቶች የሚወጣ የበገናና የመሰንቆ ድምፅ ደስ ያሰኝሃል፡፡
\v 9 በቤተ መንግሥትህ ከሚገኙ ወይዛዝርት መካከል፤ የነገሥታት ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በንጹሕ ወርቅ ያሸበረቀ ጌጤኛ ልብስ ተጐናጽፋ በቀኝህ በኩል ትቆማለች፡፡
\s5
\v 10 ልጄ ሆይ፣ አድምጪ አስተውይ፣ ጆሮሽንም አዘንብይ ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ፡፡
\v 11 ንጉሥ በውበትሽ ተማርኮአል እርሱ ጌታሽ ነውና አክብሪው፡፡
\s5
\v 12 የጢሮስ ሴት ልጅ ስጦታ ይዛ ትመጣለች፤ ሀብታሞች ደጅ ይጠኑሻል፡፡
\v 13 በቤተ መንግሥት ያለችው ልዕልት አጊጣለች ልብሷም በወርቅ አሸብርቋል፡፡
\s5
\v 14 ጌጠኛ ልብሷን ለብሳ ወደ ንጉሡ ትገባለች፤ ደናግል ጓደኞቿም አጅበዋት ወደ አንተ ይመጣሉ፡፡
\v 15 በደስታና በሐሤትም አብረው ወደ ንጉሡ ቤት ይገባሉ፡፡
\s5
\v 16 ወንዶች ልጆችህ በአባቶችህ እግር ይተካሉ በምድር ሁሉ ላይ ገዦች አድርገህ ትሾማቸዋለህ፡፡
\v 17 ስምህን በትውልድ ሁሉ ዘንድ ለመታሰቢያ አደርጋለሁ ስለዚህ ሕዝቦች ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወድሱሃል፡፡
\s5
\c 46
\p
\v 1 እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኃይላችን፣ በመከራም ቀን ረዳታችን ነው፡፡
\v 2 ስለዚህ ምድር ብትናወጥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ፣ አንፈራም፡፡
\v 3 ውሆች ቢያስገመግሙ፣ ዐረፋ ቢደፍቁም፣ ከውሃው ሙላት የተነሣ ተራሮች ቢንቀጠቀጡም አንደነግጥም፡፡ ሴላ
\s5
\v 4 የእግዚአብሔርን ከተማ የልዑልንም የተቀደሰ ማደሪያ ደስ የሚያሰኙ ወራጅ ወንዞች አሉ፡፡
\v 5 እግዚአብሔር በመካከሏ ነውና አትናወጥም ጠዋት በማለዳ እግዚአብሔር ይረዳታል፡፡
\s5
\v 6 ሕዝቦች በዐመፅ ተነሡ፤ መንግሥታት ወደቁ ድምፁን ከፍ አድርጐ አሰማ ምድርም ቀለጠች፡፡
\v 7 የሰራዊት ጌታ ያህዌ ከእኛ ጋር ነው የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው፡፡ ሴላ
\s5
\v 8 ኑ የእግዚአብሔርን ሥራ በምድር ላይ የደረሰውን ጥፋት ተመልከቱ፡፡
\v 9 ከምድር ዳር እስከ ዳርቻ ጦርነትን ያስወግዳል ቀስትን ይሰብራል፤ ጦርንም ያነክታል ጋሻዎችንም በእሳት ያቃጥላል፡፡
\s5
\v 10 ጸጥ በሉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ፡፡
\v 11 የሰራዊት አምላክ ያህዌ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው፡፡ ሴላ
\s5
\c 47
\p
\v 1 ሕዝቦች ሁሉ እጆቻችሁን አጨብጭቡ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፡፡
\v 2 በምድር ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ የሆነው ልዑል ያህዌ እጅግ አስፈሪ ነው፡፡
\s5
\v 3 ሕዝቦችን ከእኛ በታች አደረገ፣ መንግሥታትንም ከእግራችን ሥር አስገዛልን፡፡
\v 4 ለሚወደው ለያዕቆብ ክብር የሆነችውን ርስታችንን እርሱ መረጠልን፡፡
\v 5 እግዚአብሔር በእልልታ፣ ያህዌም በመለከት ድምፅ ዐረገ
\s5
\v 6 ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ ዘምሩ ለንጉሣችን ዘምሩ
\v 7 እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና ስለዚህ በማስተዋል ዘምሩለት፡፡
\s5
\v 8 እግዚአብሔር በሕዝቦች ሁሉ ነግሦአል እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል፡፡
\v 9 ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር የሕዝቦች መኳንንት ተሰበሰቡ የምድር ነገሥታት የእግዚአብሔር ናቸውና እርሱ እጅግ ከፍ ያለ ነው፡፡
\s5
\c 48
\p
\v 1 ያህዌ ታላቅ ነው፣ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰ ተራራው ላይ ከፍ ያለ ምስጋና ሊቀርብለት ይገባል፡፡
\v 2 የምድር ሁሉ ደስታ የሆነው በሰሜን በኩል በርቀት የሚታየው በከፍታ ላይ አምሮ የደመቀው የጽዮን ተራራ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነው፡፡
\v 3 እግዚአብሔር በቤተ መንግሥት ውስጥ ሆኖ ብርቱ ምሽጓ መሆኑን አስመስክሮአል፡፡
\s5
\v 4 እነሆ፣ ነገሥታት ተባብረው መጡ በአንድነትም ገሠገሡ፡፡
\v 5 ዐይተው ተደነቁ ደንግጠውም ፈረጠጡ፡፡
\v 6 በዚያ ፍርሃትና ድንጋጤ ያዛቸው ምጥ እንደያዛት ሴት ብርክ ያዛቸው፡፡
\s5
\v 7 የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከብ እንደሚሰባብር አንተ አንበረከክሃቸው
\v 8 በጆሮአችን እንደ ሰማን በሰራዊት አምላክ ከተማ በአምላካችን ያህዌ ከተማ በዐይናችን አየን፡፡
\s5
\v 9 አምላክ ሆይ፣ በቤተ መቅደስ ውስጥ ሆነን ታማኝነትህን እናስባለን፡፡
\v 10 እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደ ስምህ ምስጋናህም እስከ ምድር ዳርቻ ነው፤ ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት፡፡
\s5
\v 11 ስለ ጽድቅህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበላት የይሁዳም ልጅ ሐሤት ታድርግ፡፡
\s5
\v 12 በጽዮን ተራራ፣ በዙሪያዋም ተመላለሱ፣ ማማዎቿን ቁጠሩ፤
\v 13 ለሚቀጥለው ትውልድ ትናገሩ ዘንድ ጠንካራ ቅጥሮቿን አስተውሉ ምሽጐችዋንም ተመልከቱ፡፡
\s5
\v 14 ይህ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላካችን ነው፤ እስከ መጨረሻው መሪያዎችንም እርሱ ነው፡፡
\s5
\c 49
\p
\v 1 ሕዝቦች ሁሉ ይህን ስሙ በዓለም የምትኖሩ ሁሉ ይህን አድምጡ፡፡
\v 2 ዝቅተኞችና ከፍተኞች ሀብታሞችና ድኾች ይህን በአንድነት አድምጡ፡፡
\s5
\v 3 አፌ ጥበብን ይናገራል የልቤ ሐሳብም ማስተዋልን ይሰጣል፡፡
\v 4 ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ በበገናም የምሳሌዎቹን ትርጒም እገልጣለሁ፡፡
\v 5 ክፉ ቀን ሲመጣና አታላዮች ሲከብቡኝ ለምን እፈራለሁ?
\s5
\v 6 በሀብታቸው የሚመኩትንና በብልጽግናቸው የሚተማመኑትን ለምን እፈራለሁ?
\v 7 ማንም ወንድሙን መቤዠት ለእርሱም ቤዛ የሚሆነውን ዋጋ ለእግዚአብሔር መክፈል አይችልም፡፡
\v 8 የነፍስ ቤዛ ውድ ነውና በቂ ዋጋ ሊገኝለት አይችልም፡፡
\s5
\v 9 እንዳይሞትና ወደ መቃብር እንዳይወርድ ማንም ለዘላለም መኖር አይችልም፡፡
\v 10 ሰዎች ሁሉ ይሞታሉ፤ ጠቢባን እንኳ ከሞኞችና ከሞኞች እኩል በአንድት ይጠፋሉ ሀብታቸውንም ለሌላው ጥለው ይሄዳሉ፡፡
\s5
\v 11 እነርሱ የሚያስቡት ቤተ ሰባቸው ለዘላለም እንደሚኖር፣ መኖሪያ ስፍራቸውም ለትውልድ ዘመን እንደማይጠፋ በመሆኑ መሬቶቻቸውን በስማቸው ይሰይማሉ፡፡
\s5
\v 12 ግን ሰው በሀብቱ እንደ ተከበረ አይዘልቅም አሁን ታይተው በኃላ እንደሚጠፉ እንስሳት ይመስላል፡፡
\v 13 ይህ የምኞት ዕድል ፈንታ የእነርሱንም አባባል የሚከተሉ ሰዎች መጨረሻ ግብ ነው፡፡
\s5
\v 14 እንደ በጐች ለሞት የተመደቡ ናቸው እረኛቸውም ሞት ነው በማለዳ ቅኖች ይገዟቸዋል፤ መኖሪያ ቦታ አጥቶ አካላቸው ሲኦል ውስጥ ይፈራርሳል፡፡
\v 15 እግዚአብሔር ግን ሕይወቴን ከሲኦል ኃይል ይቤዣል፤ እርሱም ይቀበለኛል፡፡ ሴላ
\s5
\v 16 ሰው ባለጠጋ ቢሆን፣ የቤቱም ክብር ቢበዛለት አትፍራ፡፡
\v 17 በሚሞትበት ጊዜ ምንም ይዞ አይሄድም ክብሩም አብሮት አይወርድም፡፡
\s5
\v 18 ሰው በሕይወቱ ዘመን ቢደሰትም፣ ሁሉም ነገር ስለ ተሳካለት ቢመሰገንም፣
\v 19 በሞት ተለይቶ ከእንግዲህ ብርሃን ወደሚያይበት ወደ አባቶች ትውልድ ይሄዳል፡፡
\v 20 ሁሉም ነገር እያለው ማስተዋል የጐደለው ሰው ታይተው የሚጠፉ እንስሳትን ይመስላል፡፡
\s5
\c 50
\p
\v 1 ኃያሉ አምላክ ያህዌ ተናገረ ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ ምድርን ተናገረ፡፡
\v 2 ፍጹም ውብ ከሆነችው ከጽዮን እግዚአብሔር አበራ፡፡
\s5
\v 3 አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም የሚባላ እሳት በፊቱ ነው ኃይለኛ ዐውሎ ነፋስም በዙሪያው ነው፡፡
\v 4 ሕዝቡ ላይ ይፈርድ ዘንድ በላይ ያሉ ሰማያትንና ምድርን፣ «በመሥዋዕት ከእኔ ጋር ኪዳን የገቡትን
\v 5 ቅዱሳኔን ሁሉ ወደ እኔ ሰብስቡ» ብሎ ይጣራል፡፡
\s5
\v 6 ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፡፡ እግዚአብሔርን ራሱ ፈራጅ ነው፡፡ ሴላ
\s5
\v 7 «ሕዝቤ ሆይ፣ ስማኝ ልንገርህ እስራኤል ሆይ፣ በአንተ ላይ ልመስክር፤ አምላክህ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡
\v 8 ስለ መሥዋዕትህ አልነቅፍህም የሚቃጠል መሥዋዕትህ ሁልጊዜ በፊቴ ነው፡፡
\s5
\v 9 ከበረትህ ኮርማዎችን፣ ከጉሮኖህም አውራ ፍየሎችን አልወስድም
\v 10 የዱር አራዊት ሁሉ፣ በሺ ተራሮች ያለው እንስሳ ሁሉ የእኔ ነውና፡፡
\v 11 በየተራሮች ያሉ ወፎችን ሁሉ ዐውቃለሁ፡፡ በመስክ የሚገኙ እንስሶች ሁሉ የእኔ ናቸው፡፡
\s5
\v 12 ብራብ እንኳ ለአንተ አልናገርም ዓለምና በውስጧ ያለው ሁሉ የእኔ ነውና፡፡
\v 13 የኮርማዎችን ሥጋ እበላለሁን? ወይስ የፍየሎችን ደም እጠጣለሁን?
\s5
\v 14 የምስጋና መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርብ፤ ስእለትህንም ለልዑል አምላክ ክፈል፡፡
\v 15 በመከራ ቀን ጥራኝ እኔ እታደግሃለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ፡፡
\s5
\v 16 ዐመፀኛውን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል ሕጌን ለማነብነብ፣ ኪዳኔንም በአፍህ ለመናገር ምን መብት አለህ?
\v 17 ትምህርቴን ጠልተሃል፤ ቃሌንም ወደ ኃላህ ጥለሃል፡፡
\s5
\v 18 ሌባውን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ጋር ሮጥህ፣ ዕድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ፡፡
\v 19 አፍህን ለክፋት፣ አንደበትህንም ሽንገላ ለመናገር አዋልህ፡፡
\v 20 ተቀምጠህ ወንድምህን አማኸው የእናትህንም ልጅ ስም አጠፋህ፡፡
\s5
\v 21 ይህን ሁሉ ስታደርግ ዝም አልሁህ ስለዚህ እኔም እንዳንተው የሆንሁ መሰለህ፡፡ አሁን ግን ፊት ለፊት ነገርህን ገልጩ እገሥጽሃለሁ፡፡
\v 22 እናንት እግዚአብሔርን የምትረሱ ይህን አስተውሉ፤ አለበለዚያ ብትንትናችሁን አወጣለሁ! የሚያስጥላችሁም የለም!
\s5
\v 23 የምስጋና መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤ መንገዱን ቀና ለሚያደርግ የእግዚአብሔር ማዳን አሳየዋለሁ፡፡
\s5
\c 51
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ርኅራኄም ብዛት መተላለፌን ደምስስ፡፡
\v 2 በደሌን ፈጽሞ እጠብልኝ ከኃጢአቴም አንጻኝ፡፡
\s5
\v 3 መተላለፌን ዐውቃለሁና ኃጢአቴም ዘወትር በፊቴ ነው፡፡
\v 4 አንተን፣ በእርግጥ አንተን ብቻ በደልሁ ስትናገር ትክክል ነህ፤ ስትፈርድም ትክክል ነህ፡፡
\s5
\v 5 ስወለድ ጀምሮ በደለኛ ነህ ገና እናቴም ስትወልደኝ ኃጢአተኛ ነኝ፡፡
\v 6 እነሆ፣ አንተ ልቤ ውስጥ እውነትን ትሻለህ ስለዚህ ጥልቅ ጥበብን በውስጤ አስተምረኝ፡፡
\s5
\v 7 በሂሶጵ እርጨኝ እኔም እነጻለሁ፡፡ እጠበኝ፤ ከበረዶም ይልቅ እነጻለሁ፡፡
\v 8 ያደቀቅሃቸው አጥንቶቼ ደስ እንዲላቸው ደስታንና ሐሤትን አሰማኝ፡፡
\v 9 ፊትህን ከኃጢአቴ መልስ፣ በደሌን ሁሉ ደምስስልኝ፡፡
\s5
\v 10 አምላኬ ሆይ፣ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ
\v 11 ከፊትህ አትጣለኝ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ አትውሰድብኝ፡፡
\s5
\v 12 የማዳንህን ደስታ መልስልኝ በእሺታ መንፈስም ደግፈኝ ያዘኝ፡፡
\v 13 በዚያ ጊዜ፣ ለሕግ ተላላፊዎች መንገድህን አስተምራለሁ፡፡ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ፡፡
\s5
\v 14 የድነቴ አምላክ ሆይ፣ ደም አፍሳሽነቴን ይቅር በል አንደበቴም በደስታ ስለ ጽድቅህ በእልልታ ይዘምራል፡፡
\v 15 ጌታ ሆይ፣ ከንፈሮቼን ክፈት አፌም ምስጋናህን ያውጃል፡፡
\v 16 መሥዋዕትን ብትወድ ኖሮ፣ እሰጥህ ነበር፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም ደስ አያሰኝህም፡፡
\s5
\v 17 የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው አንተ፣ የተሰበረውን የተዋረደውን መንፈስ አትንቅም፡፡
\v 18 በበጐነትህ ለጽዮን መልካም አድርግ የኢየሩሳሌምንም ቅጥሮች ሥራ፡፡
\v 19 በዚያ ጊዜ የጽድቅ መሥዋዕት፣ የሚቃጠል መሥዋዕትና ፈጽሞ የሚቃጠል መሥዋዕት ደስ ያሰኝሃል፡፡ እኛም በመሠዊያህ ላይ እንደ ገና ኮርማዎችን እናቀርባለን፡፡
\s5
\c 52
\p
\v 1 ኃያል ሆይ፣ ሁከት በመፍጠር ለምን ትኩራለህ? የእግዚአብሔር ኪዳን ታማኝነት ዕለት ዕለት ነው፡፡
\v 2 አንደበትህ እንደ ሰላ ምላጭ ጥፋትን ያውጠነጥናል፡፡
\s5
\v 3 ከመልካም ይልቅ ክፋትን፣ እውነትን ከመናገር ይልቅ ሐሰትን ወደድህ፡፡
\s5
\v 4 አንተ አታላይ አንደበት ሆይ፣ ሌሎችን የሚያጠፋ ቃል ወደድህ፡፡
\v 5 ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ያጠፋሃል ይነጥቅሃል፤ ከድንኳንህም መንጥቆ ያወጣሃል፤ ከሕያዋን ምድር ይነቅልሃል፡፡
\s5
\v 6 ጻድቃን ይህን ዐይተው ይፈራሉ እንዲህ እያሉም ይሥቁበታል፤
\v 7 «ተመልከቱ፣ እግዚአብሔርን መጠጊያ ያላደረገ፣ ነገር ግን በሀብቱ ብዛት የተመካ በክፋቱም የበረታ ያ ሰው እነሆ!»
\s5
\v 8 እኔ ግን በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለመለመ የወይራ ዛፍ ነኝ፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ በእግዚአብሔር ምሕረት እታመናለሁ።
\v 9 ስላደረግኸው ነገር ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፤ ስምህ መልካም ነውና ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ፤ በቅዱሳንም መካከል አመሰግንሃለሁ።
\s5
\c 53
\p
\v 1 ሞኝ በልቡ፣ «እግዚአብሔር የለም» ይላል ብልሹዎች ናቸው፤ ጸያፍ ነገርም አድርገዋል መልካም የሚያደርግ አንድ እንኳ የለም፡፡
\v 2 አስተዋዮችና እርሱን የሚፈልጉ ሰዎች ለማግኘት፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ፡፡
\v 3 ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር ብለዋል፤ በአንድነትም ብልሹዎች ሆነዋል፡፡ መልካም የሚያደርግ አንድ እንኳ የለም፡፡
\s5
\v 4 ክፉ አድራጊዎች ከቶ አያስተውሉምን እንጀራ እንደሚበላ ሰው ሕዝቤን የሚበሉ፣ እግዚአብሔርንም ጠርተው የማያውቁት ሰዎች አይማሩምን?
\v 5 ምንም የሚያስፈራ ነገር ሳይኖር እጅግ ፈሩ፤ የዘመቱብህን ሰዎች ዐጥንት እግዚአብሔር በተነ፤ እግዚአብሔር ስለ ናቃቸው እንዲህ ያሉ ሰዎች ያፍራሉ፡፡
\s5
\v 6 ምነው ለእስራኤል የሚሆን መዳን ከጽዮን በመጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከምርኮ በመለሰ ጊዜ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፤ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል!
\s5
\c 54
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ በስምህ አድነኝ በኃይልህም ፍረድልኝ፡፡
\v 2 እግዚአብሔር ሆይ፣ ጸሎቴን ስማልኝ የአፌንም ቃል አድምጥ፡፡
\v 3 ባዕዳን ተነሥተውብኛልና ጨካኞችም ነፍሴን ይፈልጓታል እግዚአብሔርንም ከምንም አልቆጠሩትም፡፡ ሴላ
\s5
\v 4 እነሆ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው ጌታም ደግፎ ይይዘኛል፡፡
\v 5 ክፋታቸውን በጠላቶቼ ላይ መልስባቸው በቃልህ ታማኝ ነህና አጥፋቸው፡፡
\s5
\v 6 በበጐ ፈቃድ መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ መልም ነውና ያህዌ ሆይ፣ ስምህን አመሰግናለሁ፡፡
\v 7 ከመከራ ሁሉ ታድጐኛልና ዐይኔም የጠላቶቼን ውድቀት ለማየት በቅቶአል፡፡
\s5
\c 55
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ ልመናዬንም ቸል አትበል፡፡
\v 2 ችግሬ ዕረፍት ነስቶኛልና ወደ እኔ ተመልከት መልስልኝም፡፡
\v 3 ከጠላቶቼ ዛቻ የተነሣ፣ ፈርቼአለሁ፤ በክፉዎችም ጭቈና ደቅቄአለሁ፡፡ መከራ አምጥተውብኛል፤ በቁጣም ያሳድዱኛል፡፡
\s5
\v 4 ልቤ በውስጤ ተሸበረብኝ የሞት ድንጋጤም መጣብኝ፡፡
\v 5 ፍርሃትና እንቅጥቅጥ መጡብኝ ሽብርም በረታብኝ፡፡
\s5
\v 6 እኔም እንዲህ አልሁ፣ «ምነው የርግብ ክንፍ በኖረኝ! በርሬ ሄጄ ዐርፍ ነበር፡፡
\v 7 እነሆ፣ ኮብልዬ በራቅሁ ነበር በምድረ በዳ በሰነበትሁ ነበር፡፡ ሴላ
\s5
\v 8 ከዐውሎ ነፋስና ከውሽንፍር ሸሽቼ ወደ መሸሽጊያ ፈጥኜ በደረስሁ ነበር፡፡»
\v 9 ግፍና ሁከት በከተማዪቱ ዐይቻለሁና ጌታ ሆይ ግራ አጋባቸው፤ ቋንቋቸውንም ደበላልቅ!
\s5
\v 10 ቀንና ሌሊት ቅጥሮቿን ይዞራሉ ተንኰልና መከራ በውስጧ አሉ፡፡
\v 11 ዐመፃ በመካከልዋ ነው፤ ግፍና አታላይነት ከጐዳናዋ አይጠፋም፡፡
\s5
\v 12 የሰደበኝ ጠላት አይደለም ያማ ቢሆን በታገሥኩ ነበር፤ የሚታበይብኝ፣ ራሱንም ቀና ቀና ያደረገብኝ ባላንጣ አይደለም፤ ያማ ቢሆን፣ ከእርሱ በተሸሸግሁ ነበር፡፡
\v 13 ነገር ግን ያን ያደረግህ አንተ እኩያየ፣ ባልንጀራዬና የቅርብ ወዳጄ ነህ፡፡
\v 14 ደስ የሚል ኅብረት በአንድነት ነበረን በሕዝቡ መካከል በእግዚአብሔር ቤት አብረን ተመላልሰን ነበር፡፡
\s5
\v 15 በድንገት ሞት ይምጣባቸው ክፋት በመካከላቸው ናትና በሕይወታቸው እያሉ ወደ ሲኦል ይወረዱ፡፡
\s5
\v 16 እኔ ግን እግዚአብሔርን እጣራለሁ ያህዌም ያድነኛል፡፡
\v 17 በማታ፣ በጧትና በቀትር አቃሥታለሁ እቃትታለሁም እርሱም ድምፄን ይሰማል፡፡
\v 18 ከእኔ ጋር የሚዋጉት ብዙ ናቸውና እርሱ፣ ከተከፈተብኝ ጦርነት በሰላም ይታደገኛል፡፡
\s5
\v 19 ስለማይለወጡና አምኬንም ስለማይፈሩ ከዘላለም እስከ ዘላለም ዙፋኑ ላይ ያለው እግዚአብሔር ሰምቶ ያዋርዳቸዋል፡፡ ሴላ
\s5
\v 20 ጓደኛዬ የምለው ሰው እጁን በወዳጆቹ ላይ ሰነዘረ፤ ቃል ኪዳኑንም አፈረሰ፡፡
\v 21 አፉ ከቅቤ ይልቅ የለዘበ ነው በልቡ ግን ጦርነት አለ፤ ቃሉ ከዘይት ይልቅ የለሰለሰ ነው ሆኖም የተመዘዘ ሰይፍ ነው፡፡
\s5
\v 22 የከበድህን ነገር በያህዌ ላይ ጣል እርሱ ደግፎ ይይዝሃል፤ የጻድቁን መናወጥ ከቶ አይፈቅድም፡፡
\v 23 አንተ ግን እግዚአብሔር ሆይ፣ ዐመፀኞችን ወደ ጥፋት ጉድጓድ ታወርዳቸዋለህ ደም የተጠሙና አታላዮች የዕድሜያቸውን ግማሽ እንኳ አይኖሩም፡፡ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ፡፡
\s5
\c 56
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ ሰዎች ስለሚያጠቁኝና ጠላቶቼም ቀኑን ሙሉ ስለሚያሳድዱኝ ማረኝ፡፡
\v 2 ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ በላዬ ቆሙ በእብሪት የሚዋጉኝ ብዙ ናቸውና፡፡
\s5
\v 3 እኔ ግን ፍርሃት ሲይዘኝ እምነቴን አንተ ላይ አደርጋለሁ
\v 4 ቃሉን በማመሰግው አምላክ በእግዚአብሔር ታምኛሁና አልፈራም ከቶ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
\s5
\v 5 ቀኑን ሙሉ ቃሌን ያጣምማሉ ሐሳባቸው ሁሉ እኔን መጉዳት ነው፡፡
\v 6 ይዶልታሉ፤ ያደባሉ ሕይወቴ ላይ እንደሚያደቡት ሁሉ ርምጃዬንም ይከታተላሉ፡፡
\s5
\v 7 አምላክ ሆይ፣ በምንም መንገድ እንዲያመልጡ አታድርጋቸው፤ በቁጣህ ሕዝቦችን አዋርዳቸው፡፡
\v 8 የመንከራተት ቀኖቼን ቆጥረሃል እንባዎቼን በመያዣህ አኑረሃል፡፡ ሁሉስ በመጽሐፍህ ያለ አይደለምን?
\s5
\v 9 ወደ አንተ በተጣራሁ ቀን ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፡፡ በዚህም እግዚአብሔር ከእኔ ጋር መሆኑን በእርግጥ ዐወቅሁ፡፡
\v 10 ቃሉን በማመሰግነው አምላክ ቃሉን በማመመሰግነው ያህዌ
\v 11 በአምላክ ታምኛለሁና አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
\s5
\v 12 አምላኬ ሆይ፣ የተሳልሁትን እፈጽማለሁ ለአንተም የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፡፡
\v 13 ነፍሴን ከሞት፣ እግሬን ከመሰናከል አድነሃልና በሕያዋን ብርሃን፣ በእግዚአብሔር ፊት እመላለሳለሁ፡፡
\s5
\c 57
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ ማረኝ አቤቱ ማረኝ የመከራው ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁና፡፡ ጥፋት እስኪያልፍ ድረስ በክንፎችህ እጠለላለሁ፡፡
\s5
\v 2 ወደ ልዑል እግዚአብሔር የሚያስፈልገኝን ሁሉ ወደሚሰጠኝ አምላክ እጮኻለሁ፡፡
\v 3 ከሰማይ ልኮ ያድነኛል የሚያስጨንቁኝንም ያዋርዳቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ፍቅሩንና ታማኝነቱን ይልካል፡፡
\s5
\v 4 ነፍሴ በአንበሶች ተከባለች፣ ሊውጡኝ በተዘጋጁ መካከል ወድቄአለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ ምሳቸውም የተሳለ ሰይፍ ነው፡፡
\v 5 እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ይስፋፋ
\s5
\v 6 ለእግሬ ወጥመድ ዘረጉ፣ ነፍሴንም አጐበጡአት፤ መንገዴ ላይ ጉድጓድ ቆፈሩ፤ ነገር ግን ራሳቸው ገቡበት፡፡ ሴላ
\s5
\v 7 ልቤ ጽኑ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ ልቤ ጽኑ ነው እቀኛለሁ፤ እዘምራለሁ፡፡
\v 8 ነፍሴ ሆይ፣ ንቂ በገናና መሰንቆም ተነሡ እኔም በማለዳ እነሣለሁ፡፡
\s5
\v 9 ጌታ ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ በመንግሥታት መካከል ምስጋና እዘምራለሁ፡፡
\v 10 ዘላለማዊ ፍቅርህ ከሰማያት በላይ ነው ታማኝነትህም እስከ ደመናት ይደርሳል፡፡
\v 11 እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ በል ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ይስፋፋ፡፡
\s5
\c 58
\p
\v 1 እናንተ ገዢዎች እውነትን ትናገራላችሁ? እናንተ ሰዎች ቅን ፍርድ ትፈርዳላችሁ?
\v 2 የለም፤ በልባችሁ ክፋት ታውጠነጥናላችሁ በእጃችሁም በምድር ሁሉ ላይ በደል ትፈጽማላችሁ፡፡
\s5
\v 3 ክፉዎች በእናታቸው ማሕፀን እያሉ እንኳ ከመንገድ የወጡ ናቸው ሲወለዱ ጀምሮ የተሳሳቱና ውሸታሞች ናቸው፡፡
\v 4 መርዛቸው እንደ እባብ መርዝ ነው
\v 5 የአስማተኛውን ቃል አልሰማ እንዳለች እፉኝት ጆሮአቸውን ደፍነዋል፡፡
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ሆይ፣ ጥርሳቸውን አፋቸው ውስጥ ስበር የአንበሶችንም መንጋጋ አውላልቅ፡፡
\v 7 ፈስሶ እንደሚያልቅ ውሃ ይጥፉ የቀስታቸው ፍላጻ ዱልዱም ይሁን፡፡
\v 8 እየሄደ ሟምቶ እንደሚጠፋ ቀንድ አውጣ፣ ፀሐይ እንደማያይም ጭንጋፍ ይሁኑ፡፡
\s5
\v 9 የሚነደው እሾኽ እሳት ገና ድስታችሁን ሳያሞቀው እርጥቡንም ደረቁንም እኩል በዐውሎ ነፋስ ጠራርጐ ይወስዳቸዋል፡፡
\v 10 ጻድቃን የእግዚአብሔርን በቀል ሲያዩ ደስ ይላቸዋል እግሩንም በግፈኞች ደም ይታጠባል፡፡
\v 11 በዚህ ጊዜ ሰዎች፣ «በእርግጥ ለጻድቃን ዋጋ አላቸው፤ በእውነትም በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ» ይላሉ፡፡
\s5
\c 59
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ ከጠላቶቼ አድነኝ በእኔ ላይ ከሚነሡ ሰዎችም ጠብቀኝ፡፡
\v 2 ከክፉ አድራጊዎች ታደገኝ፣ ደም ከተጠሙ ሰዎችም አድነኝ፡፡
\s5
\v 3 ሕይወቴን ለማጥፋት አድብተዋልና ያህዌ ሆይ፣ ጨካኞች ያለ በደሌ፣ ያለ ኃጢአቴ በላዬ ተሰብስበው ዶለቱብኝ፡፡
\v 4 ምንም በደል ባይኖርብኝም ተዘጋጅተው መጡብኝ፤ አንተ ግን ሁኔታዬን ተመልከት እኔን ለመርዳትም ተነሥ፡፡
\s5
\v 5 የሰራዊት አምላክ የሆንህ ያህዌ አንተ የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝቦችን ለመቅጣት ተነሥ፣ ዐመፀኞችንም ያለ ምሕረት ቅጣቸው፡፡ ሴላ
\s5
\v 6 እንደ ውሻ እያላዘኑ በምሽት ተመልሰው ይመጣሉ በከተማዪቱም ይራወጣሉ፡፡
\v 7 ከአፋቸው የሚወጣውን ተመልከት ሰይፍ ከንፈራቸው ላይ አለ ደግሞም፣ «ማን ሊሰማን ይችላል?» ይላሉ፡፡
\s5
\v 8 አንተ ያህዌ ግን ትሥቅባቸዋለህ ሕዝቦችን ሁሉ በንቀት ታያቸዋለህ፡፡
\v 9 እግዚአብሔር ብርታቴ ሆይ አንተን እጠብቃለሁ፤ አምላኬ ሆይ አንተ መጠጊያዬ ነህና፡፡
\s5
\v 10 እግዚአብሔር በምሕረቱ ይገናኘኛል አምላኬ የጠላቶቼን ውድቀት ያሳየኛል፡፡
\v 11 እግዚአብሔር ጋሻችን ሆይ፣ ሕዝቤ እንዳይረሱ አትግደላቸው፤ በኃይልህ በትናቸው ዝቅ ዝቅም አድርጋቸው፡፡
\s5
\v 12 ከአፋቸው ስለሚወጣው ኃጢአት ከከንፈራቸውም ስለሚሰነዘረው ቃል በትዕቢታቸው ይያዙ፡፡ ከአፋቸው ስለ ወጣው መርገምና ውሸት
\v 13 በቁጣ አጥፋቸው፤ ፈጽመህም አስወግዳቸው፡፡ እግዚአብሔር በያዕቆብና በምድር ዳርቻ ሁሉ ገዢ መሆኑን ይወቁ፡፡
\s5
\v 14 እንደ ውሻ እያላዘኑ፣ በምሽት ተመልሰው ይመጣሉ፤ በከተማዪቱም ዙሪያ ይራወጣሉ፡፡
\v 15 ምግብ ፍለጋ ይራወጣሉ፤ ካልጠገቡም ያላዝናሉ፡፡
\s5
\v 16 እኔ ግን ስለ ኃይልህ እዘምራለሁ በማለዳም ስለ ዘላለማዊ ፍቅርህ እዘምራለሁ፡፡ አንተ መጠጊያዬ፣ በመከራዬም ቀን ዐምባዬ ነህና፡፡
\v 17 ብርታቴ ሆይ፣ በዝማሬ አመሰግንሃለሁ፤ እግዚአብሔር መጠጊያዬ የምትወደኝም አምላኬ ነህና፡፡
\s5
\c 60
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ ጣልኸኝ፣ ሰባበርኸን፤ ተቆጣኸንም፤ አሁን ግን መልስህ አብጀኝ፡፡
\s5
\v 2 ምድሪቱን አናወጥኃት፣ ፍርክስክስ አደረግኃት፤ ተንገዳግዳለችና ስብራቷን ጠግን፡፡
\v 3 ሕዝብህን መከራውን አሳየኸው የሚያንገዳግድ ወይን ጠጅ እንድንጠጣም ሰጠኸን፡፡
\s5
\v 4 ከጠላት ቀስት እንዲያመልጡ ለሚፈሩህ ምልክት አደረግህላቸው፡፡ ሴላ
\v 5 የምትወደው ሕዝብህ ከጉዳት እንዲድን በቀኝህ ታደገን፤ መልስም ስጠን፡፡
\s5
\v 6 እግዚአብሔር በመቅደሱ ሆኖ እንዲህ አለ፣ «ሲኬምን እሸነሽናለሁ፤ የሱኮትንም ሸለቆ አከፋፍላለሁ፡፡
\v 7 ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራስ ቁሬ፣ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው፡፡
\s5
\v 8 ሞዓብ መታጠቢ ገንዳዬ ነው፤ በኤዶም ላይ ጫማየን እወረውራለሁ ፍልስጥኤማውያን ላይ በድል እልል እላለሁ፡፡
\v 9 ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ያመጣኛል? ማንስ ወደ ኤዶም ይመራኛል?
\s5
\v 10 ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ፥ የጣልከን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አብረህ አልወጣህም
\v 11 በጠላቶቻችን ላይ ድልን ስጠን የሰው ድጋፍ ከንቱ ነውና።
\v 12 በእግዚአብሔር እርዳታ ድል እንቀዳጃለን እርሱ ጠላቶቻችንን ከእግሩ በታች ይረግጣቸዋል።
\s5
\c 61
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ ጩኸቴን ስማ ጸሎቴንም አድምጥ፡፡
\v 2 ልቤ በዛለ ጊዜ ከምድር ዳርቻዎች ወደ አንተ እጣራለሁ ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ፡፡
\v 3 አንተ መጠጊያዬ ከጠላትም የምከለልብህ ፅኑ ግንብ ሆነኸኛልና፡፡
\s5
\v 4 በማደሪያህ ለዘላለም ልኑር በክንፎችህም ጥላ ልከለል፡፡ ሴላ
\v 5 እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ስእለቴን ሰምተሃል ስምህን የሚያከብሩ ሰዎችን ርስት ለእኔ ሰጠህ፡፡
\s5
\v 6 የንጉሡን ዕድሜ አርዝመው ዘመኑንም እስከ ብዙ ትውልዶች ድረስ ጨምርለት፡፡
\v 7 ለዘላለም በእግዚአብሔር ፊት ይንገሥ፡፡
\s5
\v 8 ስእለቴን በየቀኑ እንድፈጽም ለስምህ ለዘላለም የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ፡፡
\s5
\c 62
\p
\v 1 ድነቴ የሚመጣው ከእርሱ ስለሆነ እግዚአብሔርን ብቻ በጸጥታ እጠብቃለሁ፡፡
\v 2 ዐለቴና መድኃኒቴ እርሱ ብቻ ነው መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም፡፡
\s5
\v 3 ሰውን የምታጠቁት እስከ መቼ ነው? ይህን የዘመመ ግድግዳ የተንጋደደ ዐጥር ሁላችሁ ገፍታችሁ ልትጥሉት ትፈልጋላችሁ?
\v 4 እነርሱ የሚፈልጉት እርሱን ከክብሩ ለማዋረድ ስለሆነ በእርሱ ላይ ሐሰት መናገር ይወዳሉ፤ በአፋቸው ይመርቁታል፤ በልባቸው ግን ይረግሙታል፡፡ ሴላ
\s5
\v 5 እግዚአብሔርን ብቻ በጸጥታ እጠብቃለሁ
\v 6 ዐለቴና መድኃኒቴ እርሱ ብቻ ነው፡፡ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም፡፡
\s5
\v 7 ድነቴና ክብሬ ከእግዚአብሔር ነው እርሱ መጠጊያ ዐምባዬና መሸሸጊያ ነው፡፡
\v 8 ሰዎች ሆይ፣ ሁልጊዜ በእርሱ ታመኑ በፊቱም ልባችሁን አፍስሱ እግዚአብሔር ለእኛ መጠጊያችን ነውና፡፡ ሴላ
\s5
\v 9 ከዝቅተኛ ወገን መወለድ ከንቱ ነው፣ ከከፍተኛ ወገን መወለድም ሐሰት ነው ሚዛን ላይ ከፍ ብለው ቢታዩም ሁሉም በአንድነት ከነፋስ የቀለሉ ናቸው፡፡
\v 10 በዝርፊያ አትተማመኑ በቅሚያ በተገኘ ሀብትም ተስፋ አታድርጉ በዚህ አትበለጽጉምና ልባችሁ እነርሱ ላይ አታድርጉ፡፡
\s5
\v 11 እግዚአብሔር አንዴ ተናገረ እኔም ይህን ሁለቴ ሰማሁ፡፡ ኃይል የእግዚአብሔር ነው፡፡
\v 12 ጌታ ሆይ፣ የኪዳን ታማኝነት የአንተ ነው አንተ ለእያንዳንዱ፣ እንደ ሥራው ትከፍለዋለህ፡፡
\s5
\c 63
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ አምላኬ ነህ! ከልቤ አንተን እሻለሁ ውሃ በሌለበት ደረቅና ጭው ያለ ምድረ በዳ ነፍሴ አንተን ተጠማች ሥጋዬም አንተን ናፈቀች፡፡
\v 2 ስለዚህ መቅደስህ ውስጥ አየሁህ ኃይልህንና ክብርህንም ተመለከትሁ፡፡
\s5
\v 3 ታማኝነትህ ከሕይወት ይበልጣልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል፡፡
\v 4 እንግዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ በስምህም እጆቼን አነሣሁ፡፡
\s5
\v 5 ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንደሚጠግብ ነፍሴ በአንተ ትረካለች፤ ስለዚህ ደስ እያለኝ የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ
\v 6 በመኝታዬ ሆኜ አስታውስሃለሁ፤ ሌሊቱን ሁሉ የአንተን ነገር አስባለሁ፡፡
\s5
\v 7 አንተ ረዳቴ ነህና በክንፎችህ ጥላ ውስጥ ሐሤት አደርጋለሁ፡፡
\v 8 ነፍሴ አንተን የሙጥኝ ብላለች ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች፡፡
\s5
\v 9 ነፍሴን ማጥፋት የሚፈልጉ ግን ወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ፤
\v 10 በሰይፍ ይገደላሉ ለቀበሮችም ምግብ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 11 ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል በእግዚአብሔ ስም የሚምሉ ሁሉ ይከብራ የሐሰተኞች አንደበትም ትዘጋለች፡፡
\s5
\c 64
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ ድምፄን ስማ የብሶቴን ቃል አድምጥ፤ ከሚያስፈራ የጠላት ዛቻ ሕይወቴን አድናት
\v 2 ከክፉ አድራጊዎች ዐድማ ሰውረኝ ከዐመፀኞችም ሤራ አድነኝ፡፡
\s5
\v 3 እነርሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ስለዋል መርዘኛ ቃላቸውንም እንደ ፍላጻ ያነጣጥራሉ
\v 4 ካሸመቁበት ቦታ ሆነው ንጹሑን ሰው ይነደፋታል ድንገት ይነድፉታል፤ አይፈሩምም፡፡
\s5
\v 5 ክፉ ዕቅድ ለማውጣት እርስ በርስ ይመካከራሉ፤ ወጥመድ ለመዘርጋትም በምስጢር ይነጋገራሉ፤ «ማንስ ሊያድን ይችላል?» ይባባላሉ፡፡
\v 6 እነርሱ ክፉ ዕቅድ አወጡ፤ በሐሳባቸውም፣ «በጥንቃቄ ዕቅድ አውጥተናል» ይላሉ፡፡ የሰው ሐሳብና ልብ በጣም ጥልቅ ነው፡፡
\s5
\v 7 እግዚአብሔር ግን በፍላጻው ይነድፋቸዋል እነርሱም በድንገት ይቆስላሉ፡፡
\v 8 በገዛ ምላሳቸው ያሰናክላቸዋል ጥፋትንም ያመጣባቸዋል የሚያዩአቸው ሁሉ በመገረም ራሳቸውን ይነቀንቃሉ፡፡
\v 9 የሰው ልጆች ሁሉ ይፈራሉ የእግዚብሔር ያደረገውንም በይፋ ይናገራሉ፡፡
\s5
\v 10 ጻድቅ በያህዌ ደስ ይለዋል፤ እርሱንም መጠጊያው ያደርጋል ልበ ቅኖችም ሁሉ በእርሱ ይመካሉ፡፡
\s5
\c 65
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፤ ለአንተ የተሳልነውንም እንፈጽማለን፡፡
\v 2 ሥጋ ለባሽ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል፡፡
\v 3 ኃጢአት በርትቶብን በነበረ ጊዜ አንተ መተላለፋችንን ይቅር አልህ፡፡
\s5
\v 4 አንተ የመረጥኸው፣ በአደባባይህም እንዲኖር ወደ አንተ ያቀረብኸው ሰው ቡሩክ ነው፡፡ ከተቀደሰው መቅደስህ፣ ከቤትህም በረከት እንጠግባለን፡፡
\s5
\v 5 የምድር ዳርቻዎችና ከባሕሩ ማዶ ርቀው ያሉ ሁሉ ተስፋ አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ፣ በጽድቅህ ድንቅ አሠራር መልስልን፡፡
\s5
\v 6 በኃይልህ ተራሮችን አጽንተሃል ብርታትንም ታጥቀሃል፡፡
\v 7 አንተ የባሕሮችን ማስገምገም የማዕበላቸውንም ጩኸት የሕዝቦችንም ውካታ ጸጥ ታሰኛለህ፡፡
\s5
\v 8 ርቀው በምድር ዳርቻዎች ያሉ ካደረግኸው ድንቅ ሥራህ የተነሣ ይደነግጣሉ፡፡ ምሥራቅና ምዕራብ በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋቸዋለህ፡፡
\v 9 ዝናብ በማዝነብ ምድርን ትጐበኛለህ፤ ፍሬያማ በማድረግም ታበለጽጋታለህ፡፡ ለሰው ልጆች እህልን ይሰጡ ዘንድ የእግዚአብሔር ወንዞች ውሃን የተሞሉ ናቸው፡፡ አንተ እንዲህ እንዲሆን ወስነሃል፡፡
\s5
\v 10 ትልሟን ታረሰርሳለህ ወጣ ገባውን ታስተካክላለህ ዐፈሩን በካፊያ ታለሰልሳለህ ቡቃያዋንም ትባርካለህ፡፡
\v 11 ለዓመቱ በጐነትህን ታቀዳጀዋለህ፤ ሰረገላህም በረከትን ሞልቶ ይፈስሳል፡፡
\v 12 የምድረ በዳው ግጦሽ ቦታ እጅግ ለመለመ ኮረብቶችም ደስታን ለበሱ፡፡
\s5
\v 13 መሰማሪያዎች መንጋ በመንጋ ሆኑ ሸለቆዎች በሰብል ተሞሉ እልል እያሉም ዘመሩ፡፡
\s5
\c 66
\p
\v 1 ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ
\v 2 ለስሙ ክብር ዘምሩ ምስጋናውን አድምቁ፡፡
\s5
\v 3 እግዚአብሔርን፣ «ሥራህ እንዴት ድንቅ ነው! ከኃይልህ ታላቅነት የተነሣ ጠላቶችህ ይገዙልሃል፡፡
\v 4 ምድር ሁሉ ያመልክሃል በዝማሬም ያመሰግኑሃል ለስምህም ይዘምራሉ» ባሉት፡፡ ሴላ
\s5
\v 5 ኑ የእግዚአብሔርን ሥራ እዩ ለሰው ልጆ ያደረገውስ አስፈሪ ነው፡፡
\v 6 ባሕሩን ደረቅ ምድር አደረገው ወንዙን በእግር ተሻገሩ እኛም እርሱ ባደረገው ነገር ደስ ብሎናል፡፡
\v 7 በኃይሉ ለዘላለም ይነግሣል ዐይኖቹ ሕዝቦችን ይመለከታሉ፡፡ እንግዲህ ዐመፀኞች ቀና ቀና አይበሉ፡፡ ሴላ
\s5
\v 8 ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔርን ባርኩ የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ፡፡
\v 9 በሕያዋን መካከል አኑሮናል እግራችን እንዲንሸራተት አልፈቀደም፡፡
\s5
\v 10 እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ፈተንኸን ብር እንደሚፈተን እኛን ፈተንኸን
\v 11 ወደ ወጥመድ አገባኸን በጀርባችንም ከባድ ሸክም ጫንህብን፡፡
\v 12 ሰዎች ራሳችን ላይ እንዲፈነጩ አደረግህ በእሳትና በውሃ መካከል አለፍን የኃላ ኃላ ግን ወደ ሰፊ ስፍራ አመጣኸን፡፡
\s5
\v 13 የሚቃጠል መሥዋዕት ይዤ ወደ ቤትህ እመጣለሁ ስእለቴንም ለአንተ እከፍላለሁ፡፡
\v 14 ይህም መከራ በደረሰብኝ ጊዜ ከአፌ የወጣ፣ በከንፈሮቼም የተናገርሁት ስእለት ነው፡፡
\v 15 የሰቡ እንስሶችን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ፣ እንዲሁም መዓዛው ደስ የሚያሰኝ የአውራ በግ መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ፡፡
\s5
\v 16 እናንት እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ ኑና ስሙ፣ ለነፍሴ ያደረገላትን እነግራችኃለሁ፡፡
\v 17 በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፤ በአንደበቴ አመሰገንሁት፡፡
\v 18 በውስጤ ኃጢአት ይዤ ቢሆን ኖሮ ጌታ አይሰማኝም ነበር፡፡
\s5
\v 19 አሁን ግን እግዚአብሔር በእርግጥ ሰምቶኛል ጸሎቴንም አድምጦአል፡፡
\v 20 ጸሎቴን ያልናቀ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡
\s5
\c 67
\p
\v 1 እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም ፊቱንም በላያችን ያብራ፡፡ ሴላ
\v 2 መንገድህ በምድር ላይ ማዳንህም በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይታወቅ ዘንድ፡፡
\s5
\v 3 እግዚአብሔር ሆይ፣ ሕዝቦች ያመስግኑህ ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ፡፡
\v 4 አንተ ለሕዝቦች ቅን ስለምትፈርድላቸው የምድር ሕዝቦችን ስለምትመራ ሕዝቦች ሁሉ ደስ ይበላቸው በእልልታም ይዘምሩ፡፡ ሴላ
\s5
\v 5 እግዚአብሔር ሆይ፣ ሕዝቦች ያመስግኑህ ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ፡፡
\v 6 ምድር ፍሬዋን ሰጠች አምላካችን እግዚአብሔር ባርኮናል፡፡
\s5
\v 7 እግዚአብሔር ባርኮናል የምድር ዳርቻዎች ሁሉ እርሱን ያከብሩታል፡፡
\s5
\c 68
\p
\v 1 እግዚአብሔር ይነሣ የሚጠሉትም ከፊቱ ይበተኑ፡፡
\v 2 ጢስ እንደሚበንን፣ እንዲሁ አብንናቸው፤ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ እንዲሁ ክፉች ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ፡፡
\v 3 ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ ደስታንና ሐሤትን ይሞሉ፡፡
\s5
\v 4 ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለስሙም የምስጋና መዝሙር አቅርቡ በደመናት ላይ የሚሄደውን ከፍ አድርጉት፡፡ ስሙ ያህዌ ነው! በፊቱም ሐሤት አድርጉ፡፡
\v 5 በተቀደሰ ማደሪያው ያለው አምላክ አባት ለሌላቸው አባት ነው፡፡ ለመበለቶችም ዳኛ ነው፡፡
\v 6 እግዚአብሔር ብቸኞች በቤተ ሰብ መካከል ያኖራቸዋል፤ እስረኞችን ነጻ አውጥቶ ያስፈነድቃቸዋል፤ ክፉዎች ግን በምድረ በዳ ይኖራሉ፡፡
\s5
\v 7 እግዚአብሔር ሆይ፣ በሕዝብህ ፊት ባለፍህ ጊዜ በምድረ በዳ በተጓዝህ ጊዜ፣
\v 8 በሲና አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ምድር ተንቀጠቀጠች ሰማያትም ዶፍ አወረዱ፡፡
\s5
\v 9 እግዚአብሔር ሆይ፣ በቂ ዝናብ አዘነብህ ደርቆ የነበረውን ርስትህን አረሰረስህ፡፡
\v 10 ሕዝብህ መኖሪያው አደረጋት፤ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ከመልካምነትህ ለድኾች ሰጠህ፡፡
\s5
\v 11 እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ቃሉን ሰጠ ቃሉን የሚያውጁትም ብዙ ሰራዊት ናቸው፡፡
\v 12-13 የሰራዊት ነገሥታት ፈጥነው ወደ ኋላ ሸሹ፤ በሰፈር የቀሩ ሴቶችም ምርኮ ተከፋፈሉ በበጐች በረት መካከል ብትገኙ እንኳ በቅጠልያ ወርቅ እንደ ተለበጡ ላባዎች ናችሁ፡፡
\s5
\v 14 ሁሉን ቻዩ በዚያ የነበሩትን ነገሥታት በበተነ ጊዜ፣ ከሰልሞን ተራራ እንደሚወርድ በረዶ አደረጋቸው፡፡
\v 15 አንተ ብርቱ የባሰን ተራራ ሆይ፤ እናንት ባለ ብዙ ጫፍ ተራሮች ሆይ፣ እግዚአብሔር ሊኖርበት የመረጠውን ተራራ፣ በእርግጥ እግዚአብሔር ለዘላለም
\v 16 የሚኖርበትን ተራራ ለምን በምቀኝነት ትመለከቱታላችሁ?
\s5
\v 17 የእግዚአብሔር ሰረገላዎች እልፍ አእላፍ ነቸው ሺህ ጊዜም ሺህ ናቸው ጌታ በተቀደሰው ቦታ በሲና በመካከላቸው ነው፡፡
\v 18 ወደ ላይ ዐረግህ፣ ምርኮን አጋበስህ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ በዚያ ትኖር ዘንድ ከአንተ ጋር ከተዋጉት እንኳ ሳይቀር፣ ከሰዎች ስጦታን ተቀበልህ፡፡
\s5
\v 19 በየዕለቱ ሸክማችንን የሚሸከምልን መድኃኒታችን የሆነው እግዚአብሔር ይባረክ፡፡ ሴላ
\v 20 አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው ከሞት ሊታደገን የሚቻለው ጌታ ያህዌ ነው፡፡
\v 21 እግዚአብሔር የጠላቶችን ራስ በኃጢአታቸውም የሚጸኑትን ሰዎች ጠጉራም ዐናት ይፈነክታል፡፡
\s5
\v 22 ጌታ እንዲህ አለ፤ «ጠላቶቼን ከባሳን መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ ከባሕርም ጥልቅ አውጥቼ አመጣቸዋለሁ፤
\v 23 እግርህ በጠላትህ ደም እንዲጠልቅ የውሻህም ምላሽ ከጠላትህ ድርሻውን እንዲያገኝ ነው፡፡»
\s5
\v 24 አምላክ ሆይ፣ የክብር አካሄድህን፣ አምላኬና ንጉሤ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያደርገውን የክብር አካሄድ አዩ፡፡
\v 25 የሚጫወቱ ከኋላ ሆነው ሲሄዱ መዘምራን ከፊት፤ መሣሪያ መካከላቸው ከበሮ የሚመቱ ደናግል ነበሩ፡፡
\s5
\v 26 እግዚአብሔርን በጉባኤ አመስግኑት በእውነት የእስራኤል ዘር የሆናችሁ ያህዌን አመስግኑት፡፡
\v 27 በመጀመሪያ በቁጥር ታናሽ የሆነው የብንያም ነገድ ታየ ቀጥሎም የይሁዳ መሪዎችና ሰራዊቶቻቸው ታዩ፤ በመጨረሻም የዛብሎንና የንፍታሌም መሪዎች ተከተሉ፡፡
\s5
\v 28 እግዚአብሔር ሆይ፣ በቀድሞ ዘመን እንደዳረግኸው ኃይልህን ግለጥ
\v 29 ነገሥታት ስጦታቸውን ከሚያመጡልህ በኢየሩሳሌም ካለው ቤተ መቅደስህ ኃይልህን ግለጥ፡፡
\s5
\v 30 በሸምበቆ መካከል ያሉትን አራዊት ገሥጽ ኮርማዎችና ጥጆች የመሳሰሉትን መንግሥታት ገሥጸቸው፡፡ አዋርዳቸው ስጦታዎች እንዲመጡልህም አድርጋቸው ጦርነትን የሚወዱ ሕዝቦችንም በትናችው፡፡
\v 31 መሳፍንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች፡፡
\s5
\v 32 እናንት የምድር መንግሥታት ለያህዌ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ፡፡ ሴላ
\v 33 ከጥንት ጀምሮ ከነበሩት ሰማያት በላይ ለሚራመደው በኃያል ድምፁ ለሚያስገመግመው ዘምሩ፡፡
\s5
\v 34 ግርማው በእስራኤል ላይ ኃይሉም በሰማያት ላይ ስለሆነ የእግዚአብሔርን ኃይል ዐውጁ፡፡
\v 35 እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ በመቅደስህ ድንቅ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ ለሕዝቡ ኃይልና ብርታት ይሰጣል፡፡ እግዚአብሔር ይባረክ!
\s5
\c 69
\p
\v 1 የውሃ ሙላት እስከ አንገቴ ደርሶአልና አምላክ ሆይ አድነኝ፡፡
\v 2 መቆሚያ ስላጣሁ በጥልቁ ረግረግ ውሃ ለመስጠም ተቃርቤአለሁ፡፡
\s5
\v 3 ብዙ ከመጮኼ የተነሣ ዛልሁ ጉሮሮየም ደረቀ፤ አምላኬን በመጠባበቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ፡፡
\v 4 ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ከራስ ጠጉሬ ይልቅ በዝተዋል፤ ብዙ ጠላቶቼ እኔን ማጥፋት ይፈልጋሉ ያልሰረቅሁን ነገር መልሰህ አምጣ ተባልሁ፡፡
\s5
\v 5 እግዚአብሔር ሆይ አንተ ሞኝነቴን ታውቃለህ ኃጢአቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም፡፡
\v 6 የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ አንተን ተስፋ የሚያደርጉ በእኔ ምክንያት አይፈሩ፡፡ የእስራኤል አምላክ ሆይ፣ አንተን አጥብቀው የሚሹህ በእኔ ምክንያት አይዋረዱ፡፡
\s5
\v 7 ስለ አንተ ስድብን ታግሼአለሁ እፍረትም ፊቴን ሸፍኖአል፡፡
\v 8 ለወንድሞቼ እንደ እንግዳ ለእናቴም ልጆች እንደ ባዕድ ሆንሁባቸው፡፡
\v 9 የቤትህ ቅናት በላችኝ ለአንተ የተሰነዘረው ስድብ እኔ ላይ ዐረፈ፡፡
\s5
\v 10 በምጾምበት ጊዜ በጣም አለቀስሁ እነርሱም ሰደቡኝ፡፡
\v 11 ማቅ በለበስሁ ጊዜ መተረቻ አደረጉኝ፡፡
\v 12 በከተማው ቅጥር ለሚቀመጡ የመነጋገሪያ ርእስ ለሰካራሞችም መዝፈኛ ሆንሁ፡፡
\s5
\v 13 ያህዌ ሆይ፣ እኔ ግን በወደድኸው ሰዓት ወደ አንተ እጸልያለሁ፡፡ በታላቅ ምሕረትህ፣ በማዳንህም ርግጠኝነት መልስልኝ፡፡
\v 14 ከረግረግ አውጣኝ እንድሰጥምም አትተወኝ፡፡ ከጥልቁ ውሃ ከእነዚያ ከሚጠሉኝም ታደገኝ፡፡
\v 15 ጐርፍ አያጥለቅልቀኝ ጥልቁ ውሃም አይዋጠኝ ጉድጓዱም ተደርምሶ አይዘጋብኝ፡፡
\s5
\v 16 ያህዌ ሆይ፣ የኪዳንህ ታማኝነት በጐ ናትና ስማኝ እንደ ምሕረትህም ብዛት መልስልኝ
\v 17 ከባርያህ ፊትህን አትሰውር ተጨንቄአለሁና ፈጥነህ መልስልኝ፡፡
\s5
\v 18 ወደ እኔ ቀርበህ አድነኝ ስለ ጠላቶቼም ተቤዠኝ፡፡
\v 19 የደረሰብኝን ስድብ፣ እፍረትና ውርደት ታውቃለህ ጠላቶቼንም አንድ በአንድ ታውቃቸዋለህ፡፡
\s5
\v 20 ስድብ ልቤን ሰብሮታልና ተስፋ ቆረጥሁ፡፡ የሚያዝንልኝ ፈለግሁ ማንም አልነበረም የሚያጽናናኝም ፈለግሁ ማንንም አላገኘሁም፡፡
\v 21 ምግቤን ከሐሞት ጋር ቀላቀሉ ለጥማቴም ሆምጣጤ ሰጡኝ፡፡
\s5
\v 22 በፊታቸው የቀረበው ማእድ ወጥመድ ይሁንባቸው ደኅና ነን ሲሉ አሽክላ ይሁንባቸው፡፡
\v 23 ማየት እንዳይችሉ ዐይናቸው ይጨልም ጀርባቸውም ዘወትር ይጉበጥ፡፡
\s5
\v 24 መዓትህን በላያቸው አፍስስ፤ የቁጣህም መቅሠፍት ድንገት ይድረስባቸው፡፡
\v 25 መኖሪያቸው ወና ይሁን! በድንኳኖቻቸውም የሚኖር አይገኝ፡፡
\s5
\v 26 አንተ የመታኸውን አሳደዋልና ያቆሰልሃቸውንም ሥቃይ አባብሰዋል፡፡
\v 27 በበደላቸው ላይ በደልን ጨምርባቸው ወደ ጽድቅህ ድል አይግቡ፡፡
\s5
\v 28 ከሕይወት መጽሐፍ ይደምሰሱ ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ፡፡
\v 29 እኔ ግን ምስኪንና ሐዘነተኛ ነኝና አምላክ ሆይ፣ ማዳንህ ደግፎ ይያዘኝ፡፡
\s5
\v 30 የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አመሰግናለሁ በውዳሴም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ፡፡
\v 31 ከበሬ ይልቅ፣ ቀንድና ጥፍር ካበቀለ እንቦሳ ይበልጥ ይህ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል፡፡
\s5
\v 32 ገሮች ይህን ባዩ ጊዜ ደስ ይላቸዋል እናንተ እግዚአብሔርን የምትሹ በርቱ፡፡
\v 33 ያህዌ ችግረኞችን ይሰማልና በእስራት ያለውንም ሕዝቡን አይንቅም፡፡
\s5
\v 34 ሰማይና ምድር፣ ባሕሮችና በውስጡ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ያመስግኑት፡፡
\v 35 እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና የይሁዳንም ከተሞች መልሶ ይሠራቸዋልና ሕዝቡም በዚያ ይሰፍራል ይወርሷታልም፡፡
\v 36 የባርያዎቹም ዘሮች ይወርሷታል ስሙንም የሚወዱ በዚያ ይኖራሉ፡፡
\s5
\c 70
\p
\v 1 አምላክ ሆይ አድነኝ፤ ያህዌ ሆይ፣ ፈጥነህም እርዳኝ፡፡
\v 2 ሕይወቴን ማጥፋት የሚፈልጉ ይፈሩ ይዋረዱም፤
\v 3 በእኔ ስቃይ ደስ የሚላቸው ተሸማቅቀው ወደ ኋላ ይመለሱ፡፡
\s5
\v 4 ነገር ግን አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፤ ማዳንህን የሚወዱ ሁሉ ሁልጊዜ፣ «እግዚአብሔር ታላቅ ነው» ይበሉ፡፡
\v 5 እኔ ምስኪንና ችግረኛ ነኝ፤ አምላክ ሆይ ፈጥነህ ድረስልኝ፤ አንተ ረዳቴ ታዳጊዬም ነህና ያህዌ ሆይ አትዘግይ፡፡
\s5
\c 71
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አደረግሁ ፈጽሞ አልፈር፡፡
\v 2 በጽድቅህ ታደገኝ አስጥለኝም ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድነኝም፡፡
\v 3 በምሄድበት ቦታ ሁሉ አንተ መጠጊያ ዐምባ ሁነኝ፡፡ አንተ ዐለቴ፣ ምሽጌ ነህና እኔን ለማዳን ትእዛዝ ከአንተ ይውጣ፡፡
\s5
\v 4 አምላኬ ሆይ፣ ከዐመፀኛ ርኅራኄ ከሌለው ከጨካኝ እጅ ታደገኝ፡፡
\v 5 ጌታ ያህዌ ሆይ፣ አንተ ተስፋዬ ነህና ከልጅነቴ ጀምሮ በአንተ ታምኛለሁና፡፡
\s5
\v 6 ከተወለድሁ ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ ከእናቴ ማሕፀን ያወጣኸኝም አንተ ነህ ምስጋናዬ ዘወትር ለአንተ ነው፡፡
\v 7 አንተ ብርቱ መጠጊያየ ስለሆንህልኝ ሕይወቴ ለብዙዎች ምሳሌ ሆነ፡፡
\s5
\v 8 አፌ በምስጋናህ ተሞልቶአል ስለ ክብርህም ቀኑን ሙሉ እናገራለሁ፡፡
\v 9 በእርጅና ዘመኔ አትጣለኝ ጉልበቴም በደከመ ጊዜ አትተወኝ፡፡
\s5
\v 10 ጠላቶቼ ተነጋግረውብኛልና ሕይወቴን ማጥፋት የሚፈልጉም በእኔ በአንድነት አሢረዋል፡፡
\v 11 እነርሱም፣ «እግዚአብሔር ትቶታል፣ የሚያስጥለው የለምና ተከታትላችሁ ያዙት» አሉ፡፡
\s5
\v 12 አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ፣ አምላኬ ሆይ፣ እኔን ለማዳን ፍጠን፡፡
\v 13 ተቃዋሚዎቼ ይፈሩ፤ ይጥፉም ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ይፈሩ ይዋረዱም፡፡
\s5
\v 14 እኔ ግን ዘወትር አንተን ተስፋ አደርጋለሁ በምስጋና ላይ ምስጋና አቀርብልሃለሁ፡፡
\v 15 ምንም እንኳ ማስተዋል ቢያዳግተኝ አንደበቴ ዘወትር ስለ ጽድቅህና ስለ ማዳንህ ይናገራል፡፡
\v 16 መጥቼ የጌታ ያህዌን ብርቱ ሥራ ዐውጃለሁ የአንተን ጽድቅ ብቻ እናገራለሁ፡፡
\s5
\v 17 እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ከልጅነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ እኔም እስከ ዛሬ ድረስ ድንቅ ሥራህን እናገራለሁ፡፡
\v 18 አምላክ ሆይ፣ ሳረጅና ስሸብትም አትተወኝ እኔም ኃያልነትህን ለመጪው ትውልድ ብርታህንም ኃላ ለሚነሣ ሕዝብ እናገራለሁ፡፡
\s5
\v 19 አምላክ ሆይ፣ ጽድቅህ እስከ ሰማያት ከፍ ያለ ነው አንተ ታላላቅ ነገሮችን አድርገሃል አምላክ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
\v 20 ብዙ ችግርና መከራ ብታሳየኝም ሕይወቴን እንደ ገና ታድሳለህ፡፡ ከምድር ጥልቅም እንደ ገና ታወጣኛለህ
\s5
\v 21 ክብሬን ትጨምራለህ ተመልሰህም ታጽናናኛለህ፡፡
\v 22 አምላኬ ሆይ፣ ስለ ታማኝነትህ በበገና አመሰግንሃለሁ፤ የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፣ በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ፡፡
\s5
\v 23 ለአንተ የምስጋና መዝሙር ሳቀርብ፣ ከንፈሮቼ በደስታ ይሞላሉ አንተ ያዳንሃት ነፍሴም እልል ትላለች፡፡
\v 24 አንደበቴ ቀኑን ሙሉ ስለ ጽድቅህ ያወራል፤ የእኔን መጐዳት የሚፈልጉ አፍረዋልና ተዋርደዋልምና፡፡
\s5
\c 72
\p
\v 1 እግዚአብአብሔር ሆይ፣ ለንጉሡ ትክክለኛ ፍርድን ለንጉሡም ልጅ ጽድቅህን ስጠው፡፡
\v 2 እርሱም ሕዝብህን በጽድቅ፣ ይዳኛል ለተቸገሩትም በትክክል ይፈርዳል፡፡
\v 3 ተራሮች ሰላምን፣ ኮረብቶችም የጽድቅን ፍሬ ያመጣሉ፡፡
\s5
\v 4 ለተቸገረው ሕዝብ ይሟገታል የችግረኞችን ልጆች ያድናል ጨቋኙንም ያደቀዋል፡፡
\v 5 ፀሐይ እስካለች ድረስ፣ ጨረቃም እስከምትኖርበት ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ፣ አንተን ያከብራሉ፡፡
\s5
\v 6 በታጨደ መስክ ላይ እንደሚዘንብ ዝናብ ይውረድ እንደ ካፊያም ምድርን ያረስርስ፡፡
\v 7 በዘመኑ ጽድቅ ይስፈን ጨረቃም ብርሃንዋ በምትሰጥበት ዘመን ሁሉ ብርልጽግና ይብዛለት፡፡
\s5
\v 8 ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር ከታላቁም ወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ይሁን፡፡
\v 9 በምድረ በዳ የሚኖሩ በፊቱ ይስገዱ ጠላቶቹም ወደ መሬት ወድቀው ትቢያ ይላሱ፡፡
\v 10 የተርሴስ ነገሥታትና ደሴቶች ስጦታ ያምጡለት የሳባና የዐረብ ነገሥታት እጅ መንሻ ያቅርቡለት፡፡
\s5
\v 11 ነገሥታት ሁሉ ይስገዱለት ሕዝቦችም ሁሉ ያገልግሉት፡፡
\v 12 ወደ እርሱ የሚጮኸውን ችግረኛ ሌላ ረዳት የሌለውን ድኻ ይረዳልና፡፡
\s5
\v 13 ለድኻና ለችግረኛ ይራራል ምስኪኖችንም ከሞት ያድናል፡፡
\v 14 ሕይወታቸውን ከጭቆናና ከግፍ ያድናል ደማቸውም በፊቱ የከበረ ነው፡፡
\s5
\v 15 ዕድሜው ይርዘም፤ ከዐረብ ወርቅ ይምጣለት፤ ዘወትር ይጸልዩለት የእግዚአብሔር በረከት አይለየው፡፡
\v 16 በምድሪቱ እህል ይትረፍረፍ በተራሮች አናት ያለው ሰብል ይወዛወዝ፡፡ ፍሬው እንደ ሊባኖስ ይንዠርገግ፤ በከተማ ያለውም ሕዝብ እንደ ሜዳ ሣር ይብዛ፡፡
\s5
\v 17 ስሙ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር ዝናውም ፀሐይ በሚወጣበት ዘመን ሁሉ ይሰማ፤ ሕዝቦች በእርሱ ይባረኩ ሰዎች ሁሉ ቡሩክ ነህ ይበሉት፡፡
\s5
\v 18 ብቻውን ድንቅ የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ ያህዌ ይባረክ፡፡
\v 19 ክቡር ስሙ ለዘላለም ይባረክ ምድር ሁሉ በክብሩ ትሞላ፡፡ አሜን፤ አሜን
\v 20 የእሴይ ልጅ የዳዊት ጸሎት እዚህ ላይ ተፈጸመ።
\s5
\c 73
\p
\v 1 ልባቸው ንጹሕ ለሆነ ለእስራኤል እግዚአብሔር ቸር ነው፡፡
\v 2 እኔ ግን እግሬ ሊሰናከል፣ አዳልጦኝም ልወድቅ ጥቂት ቀረኝ፡፡
\v 3 ክፉዎች ሲሳካላቸው ዐይቼ ቅናት አድሮብኝ ነበር፡፡
\s5
\v 4 እስኪሞቱ ድረስ ሕመም አያውቃቸውም ሰውነታቸውም ጤነኛና ጠንካራ ነው፡፡
\v 5 እንደ ሌሎች ሰዎች አይጨነቁም በሌሎች ላይ የሚደርሰው ስቃይ እነርሱ ላይ አይደርስም፡፡
\s5
\v 6 ትዕቢት የአንገት ጌጣቸው ነው ግፍን እንደ ልብስ ለብሰውታል፡፡
\v 7 የሰባ ዐይናቸውም ይጉረጠርጣል፣ ልባቸው ክፉ ሐሳብ ያፈልቃል፡፡
\s5
\v 8 በፌዝና በክፋት ይናገራሉ በእብሪት ተነሣሥተው ሌሎች ላይ ይዝታሉ፡፡
\v 9 አፋቸውን በሰማይ ያላቅቃሉ አንደበታቸውም ምድርን ያካልላል፡፡
\s5
\v 10 ስለዚህ ሕዝቡ ወደ እነርሱ ይመለሳል ውሃቸውንም በገፍ ይጠጣሉ፡፡
\v 11 «እግዚአብሔር እንዴት ሊያውቅ ይችላል በልዑልስ ዘንድ ዕውቀት አለ?» ይላሉ፡፡
\v 12 እንግዲህ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው ሁልጊዜ እንደ ተዝናኑ ናቸው በሀብት ላይ ሀብት ይጨምራሉ፡፡
\s5
\v 13 ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት እኔን በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሮአል!
\v 14 ቀኑን ሙሉ ተሰቃየሁ በየማለዳውም ተቀጣሁ፡፡
\v 15 እኔ እንደዚህ እናገራለሁ ብል ኖሮ የልጆችህን ትውልድ በከዳሁ ነበር፡፡
\s5
\v 16 እነዚህን ነገሮች ለመረዳት ብሞክርም በጣም ከባድ ሆነብኝ፡፡
\v 17 ወደ መቅደስህ እስክገባ ድረስ ምንም ማወቅ አልቻልሁም በኋላ ግን በክፉዎች ላይ ምን እንደሚደርስባቸው ተረዳሁ፡፡
\s5
\v 18 በእርግጥ በሚያዳልጥ ስፍራ አኑረሃቸዋል ወድቀው እንዲጠፉም አድርገሃል፡፡
\v 19 እንዴት ፈጥነው በቅጽበት ጠፉ! በከባድ ድንጋጤ ፈጽመው ወደሙ፡፡
\v 20 ሰው ከሕልሙ ሲነቃ እንደሚሆነው፣ ጌታ ሆይ፣ አንተም በምትነሣበት ጊዜ፣ እነርሱ በማለዳ እንደሚረሳ ሕልም ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 21 ልቤ በጣም ተማረረች፣ እኔም እጅግ ቆሰልሁ፡፡
\v 22 ስሜት የሌለው አላዋቂ ሆንሁ በፊትህም እንደ እንስሳ ሆንሁ፡፡
\s5
\v 23 ይህም ሆኖ ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ አንተም ቀኝ እጄን ይዘኸኛል፡፡
\v 24 በምክርህ ትመራኛለህ በመጨረሻም በክብር ትቀበለኛለህ፡፡
\s5
\v 25 በሰማይ ከአንተ በቀር ማን አለኝ? በምድርም ከአንተ ሌላ የምፈልገው የለኝም፡፡
\v 26 ሥጋዬና ልቤ ደከሙ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም የልቤ ብርታትና አለኝታ ነው፡፡
\s5
\v 27 እነሆ፣ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉ ለአንተ ያልታመኑትንም ታጠፋቸዋለህ፡፡
\v 28 ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፣ ጌታ ያህዌን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ ሥራህንም ሁሉ እናገራለሁ፡፡
\s5
\c 74
\p
\v 1 አምላክ ሆይ፣ ለዘላለም የጣልኸን ለምንድነው? በመሰማሪያህ በጐችህስ ላይ ቁጣህ የነደደው ለምንድነው?
\v 2 ከጥንት ጀምሮ የመረጥኸውን ሕዝብ ርስትህ እንዲሆን የዋጀኸውን ነገድ፣ መኖርያህ ያደረግሃትን የጽዮን ተራራን አስብ፡፡
\s5
\v 3 ጠላት ለዘለቄታው ባድማ ያደረገውን መቅደስህ ውስጥ ያወደመውን ሁሉ ተመልከት፡፡
\v 4 ጠላቶችህ አንተ በመረጥኸው ቦታ መካከል ደነፉ፤ የጦርነት ዓርማቸውንም ምልክት አድርገው በዚያ አቆሙ፡፡
\v 5 እነርሱ ጥቅጥቅ ባለው ደን ውስጥ እንጨቶችን በመጥረቢያ የሚቆርጥ ሰው ይመስላሉ፡፡
\v 6 በእደ ጥበብ ያጌጠውን ሥራ ሁሉ፣ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰባብረው አደቀቁት፡፡
\s5
\v 7 መቅደስህን አፍርሰው በእሳት አቃጠሉት የስምህን ማደሪ አረከሱ፡፡
\v 8 በልባቸውም፣ «ገና ሁሉንም እናጠፋቸዋለን!» አሉ፡፡ በምድሪቱ ያሉ የተቀደሱ ቦታዎችን ሁሉ አቃጠሉ፡፡
\s5
\v 9 የምናየው ምልክት የለም ከእንግዲህ ወዲህ ነቢያትም አይኖሩም፤ ይህ እስከ መቼ እንደሚቀጥል ከእኛ መካከል የሚያውቅ የለም
\v 10 አምላክ ሆይ፤ ጠላት የሚሳደበው እስከ መቼ ነው? ባላንጣስ ለዘላለም በስምህ ያላግጣልን?
\v 11 እጅህን፣ ቀኝ እጅህን የምትመልሰው ለምንድነው? ቀኝ እጅህን ከብብትህ አውጥተህ አጥፋቸው፡፡
\s5
\v 12 እግዚአብሔር ሆይ፣ ከጥንት ጀምሮ አንተ ንጉሤ ነህ ማዳንህንም በምድር ላይ አደረግህ፡፡
\v 13 በኃይልህ ባሕሩን ከፈልህ የባሕሩንም አውሬ ራስ ውሃ ውስጥ ቀጠቀጥህ፡፡
\s5
\v 14 የሌዋታንን ራሶች አደቀቅህ ሥጋውንም በምድረ በዳ ለሚኖሩ ምግብ አድርገህ ሰጠሃቸው፡፡
\v 15 ምንጮችንና ፈሳሾችን አፈለቅህ ወራጅ ወንዞችን አደረቅህ
\s5
\v 16 ቀኑ የአንተ ነው፣ ሌሊቱም የአንተ ነው፤ ፀሐይንና ጨረቃንም በቦታቸው አደረግህ፡፡
\v 17 የምድር ዳርቻዎችን ሁሉ የወሰንህ አንተ ነህ ክረምትና በጋ እንዲፈራረቁ አደረግህ፡፡
\s5
\v 18 ያህዌ ሆይ፣ ጠላቶችህ በአንተ ላይ መሳለቃቸውን ጅል ሰዎችም ስምህን መዳፈራቸውን ተመልከት፡፡
\v 19 የርግብህን ነፍስ ለዱር አራዊት አሳልፈህ አትስጥ፤ የተጨቆኑ ሕዝብህንም ለዘላለም አትርሳ፡፡
\s5
\v 20 የምድር ጨለማ ቦታዎች በዐመፅ ተሞልተዋልና ኪዳንህን አስብ፡፡
\v 21 የተጨቆኑት አፍረው አይመለሱ ችግረኞችና ጭቁኖች ስምህን ያመስግኑ፡፡
\s5
\v 22 አምላክ ሆይ፣ ተነሥ ለክብርህ ተሟገት ከንቱ ሰው ቀኑን ሙሉ አንተ ላይ ማላገጡን ተመልከት፡፡
\v 23 የባላጋራዎችህን ድንፋታ ዘወትር የሚሰነዝሩትን ስድብ አትርሳ፡፡
\s5
\c 75
\p
\v 1 አምላክ ሆይ፣ እናመሰግንሃለን ሐልዎትህን ስለ ገለጥህ ምስጋና ለአንተ እንሰጣለን፤ ሰዎች ድንቅ ሥራህን ይናገራሉ፡፡
\v 2 አንተም እንዲህ አልህ፣ «ለይቼ በወሰንሁት ሰዓት በቅን የምፈርድ እኔ ነኝ፡፡
\v 3 ምድር ብትናወጥ በውስጧ የሚኖሩትም ቢንቀጠቀጡ እኔ የምድርን መሠረት አጸናለሁ፡፡ ሴላ፡፡
\s5
\v 4 ትዕቢተኞችን፣ አትታበዩ ክፉዎችን ‹አታምፁ› እላቸዋለሁ፤
\v 5 ቀንድህን ወደ ሰማይ አታንሣ፤ ዐንገትህንም መዝዘህ አትናገር፡፡»
\v 6 ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፣ ወይም ከምድረ በዳ አይመጣም፡፡
\s5
\v 7 ነገር ግን አንዱን ዝቅ፣ ሌላውን ከፍ በማድረግ በትክክል የሚፈርድ እግዚአብሔር ነው፡፡
\v 8 ያህዌ በእጁ የቁጣው ወይን ጠጅ የሞላበት ጽዋ ይዞአል ሲያፈስሰው ክፉዎች ሁሉ ጨልጠው ይጠጡታል፡፡
\s5
\v 9 እኔ ግን ዘወትር ሥራህን እናገራለሁ፤ ለያዕቆብ አምላክም ዝማሬ አቀርባለሁ፡፡
\v 10 እርሱ «የክፉዎችን ሁሉ ቀንድ እሰብራለሁ፤ የጻድቃን ቀንድ ግን ከፍ ከፍ አደርጋለሁ» ይላል፡፡
\s5
\c 76
\p
\v 1 እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው፡፡
\v 2 ድንኳኑ በሳሌም መኖሪያውም በጽዮን ነው፡፡
\v 3 በዚያም የቀስቱን ፍላጻዎች ጋሻውን፣ ጦሩንና ሌሎች የጦር መሣሪያዎችን ሰበረ፡፡ ሴላ
\s5
\v 4 ጠላቶችህን ካጠፋህበት ተራሮች ስትወርድ ደምቀህ አበራህ፤ ክብርህንም ገለጥህ፡፡
\v 5 ጀግኖች ተኝተው እያሉ የማረኩትን ተቀሙ ጦረኞችም ሁሉ ዐቅመ ቢስ ሆኑ፡፡
\s5
\v 6 የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሱና ፈረሰኛው ጭልጥ ብለው ተኝተዋል፡፡
\v 7 መፈራት ያለብህ አንተ ብቻ ነህ፤ በተቆጣህ ጊዜ ፊትህ መቆም የሚችል ማነው?
\s5
\v 8 አንተ ከሰማይ ፍርድህን አሰማህ ምድርም ፈርታ ጸጥ አለች
\v 9 አንተ በምድር የተጨቆኑትን ለማዳን ለፍርድ ስትነሣ ዓለም ጸጥ አለ፡፡
\s5
\v 10 በእርግጥ የሰው ልጅ ላይ የሚወርደው ቁጣ ፍርድህ አንተን ያመሰግንሃል ከቁጣ የተረፉትንም ትገታቸዋለህ፡፡
\s5
\v 11 ለአምላካችሁ ለያህዌ ተሳሉ፣ ስእለቱንም አግቡ በእርሱ ዙሪያ ያሉ ሁሉ መፈራት ለሚገባው እጅ መንሻ ያምጡ፡፡
\v 12 እርሱ የገዦችን መንፈስ ይሰብራል በምድር ነገሥታትም ዘንድ የተፈራ ይሆናል፡፡
\s5
\c 77
\p
\v 1 ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ ይሰማኝ ዘንድ ድምፄን ከፍ አድርጌ እግዚአብሔርን እጠራለሁ፡፡
\s5
\v 2 በመከራዬ ቀን ጌታን ፈለግሁት በሌሊትም ያለ ዕረፍት እጆቼን ዘረጋሁ፤ ነፍሴ አልጽናና አለች፡፡
\v 3 አምላኬ ሆይ፣ አንተን ባሰብሁ ቁጥር ቃተትሁ ባወጣሁ ባወረድሁ መጠን መንፈሴ ዛለች፡፡
\s5
\v 4 ዐይኖቼ እንዳይከደኑ አደረግህ መናገር እስኪሳነኝ ድረስ ታወክሁ፡፡
\v 5 የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ የድሮውን ዘመን አወጠነጠንሁ፡፡
\s5
\v 6 በሌሊት ዝማሬዬን አስታወስሁ በጥልቅ በማሰብ እየሆነ ያለውን መረዳት ሞከርሁ፡፡
\v 7 እግዚአብሔር ለዘላለም ጥሎኛልን? ከእንግዲህስ ቸርነት አያደርግልኝምን?
\s5
\v 8 የኪዳን ታማኝነቱስ እስከ ወዲያኛው ተሻረን? የተስፋ ቃሉንስ ዘነጋ?
\v 9 እግዚአብሔር ቸርነቱን ረሳ? ወይስ ከቁጣው የተነሣ መራራቱን ትቶአልን? ሴላ
\s5
\v 10 እኔም፣ «የልዑል ቀኝ እጅ እንደ ተለወጠ ማሰቤ ይህ የእኔ ደካማነት ነው» አልሁ፡፡
\s5
\v 11 ያህዌ ሆይ፣ ሥራዎችህን ሁሉ አስታውሳለሁ ድሮ ያደረግኸውን ድንቅ ሥራ አስባለሁ፡፡
\v 12 ሥራዎችህን ሁሉ አሰላሰላለሁ ድንቅ ሥራህን ሁሉ አውጠነጥናለሁ፡፡
\s5
\v 13 አምላክ ሆይ፣ መንገድህ ቅዱስ ነው እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?
\v 14 እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ድንቆችን የምታደርግ አምላክ ነህ በሕዝቦች መካከል ኃይልህን ገለጥህ፡፡
\v 15 በታላቅ ኃይልህ ለሕዝብህ ለያዕቆብና ለዮሴፍ ልጆች ድል ሰጠሃቸው፡፡ ሴላ
\s5
\v 16 አምላክ ሆይ፣ ውሆች አዩህ ውሆች አንተን አይተው ፈሩ፤ ጥልቆችም ተነዋወጡ፡፡
\v 17 ደመኖች ውሃ አንጠባጠቡ፡፡ ሰማያት አንጐዳጐዱ ፍላጾችህም ዙሪያውን አንጸባረቁ፡፡
\s5
\v 18 የድምፅህ ነጐድጓድ ዐውሎ ነፋስ ውስጥ አስተጋባ የመብረቅ ብልጭታ ዓለምን አበራ ምድር ራደች ተንቀጠቀጠች፡፡
\v 19 መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው መሄጃህም በታላቅ ውሃ ውስጥ ነው ዱካህንም ማንም አላየም፡፡
\v 20 በሙሴና በአሮን እጅ ሕዝብህን እንደ በግ መንጋ መራኸው፡፡
\s5
\c 78
\p
\v 1 ሕዝቤ ሆይ፣ ትምህርቴን ሰሙ የአፌንም ቃል አድምጡ፡፡
\v 2 አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ ከጥንት ጀምሮ የተሰወረውን ምስጢር እገልጣለሁ፡፡
\s5
\v 3 ይህም የሰማነውና ያወቅነው አባቶቻችንም የነገሩን ነው፡፡
\v 4 እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም ስለ እግዚአብሔር ኃይል ስላከናወናቸውም ታላላቅ ሥራዎችና ስላደረጋቸው ድንቅ ነገሮች ለተከታዩ ትውልድ እንገራለን፡፡
\s5
\v 5 ለያዕቆብ ሥርዐትን መሠረተ ለእስራኤልም ሕግን ደነገገ፡፡ ይህንንም ለሚቀጥለው ትውልድ እንዲያስተምሩ አባቶቻችንን አዘዘ፡፡
\v 6 ይህም የሚመጣው ትውልድ ሥርዐቱን እንዲያውቅ እነርሱም በተራቸው ለልጆቻቸው ገና ለሚወለዱትም እንዲነግሩ ነው፡፡
\s5
\v 7 እነርሱም በእግዚአብሔር ይታመኑ የእግዚአብሔርን ሥራ አይረሱም ትእዛዞቹንም ይጠብቃሉ፡፡
\v 8 እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው እልኸኛና ዐመፀኛ አይሆኑም፤ እነርሱ እግዚአብሔርን በማመን አልጸኑም ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆነው አልኖሩም፡፡
\s5
\v 9 የኤፍሬም ሰዎች የታጠቁ ቀስተኖች ቢሆኑም በጦርነት ቀን ወደ ኃላ ተመለሱ፡፡
\v 10 የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁም፣ በሕጉ መሠረት መኖርም አልፈለጉም፡፡
\v 11 ሥራዎቹን ረሱ ያሳያቸውንም ድንቆች ዘነጉ፡፡
\s5
\v 12 በግብፅ ምድር፣ በዞዓር ምድር በአባቶቻቸው ፊት ያደረጋቸውን ድንቆች ዘነጋ፡፡
\v 13 ባሕሩን ከፍሎ አሻገራቸው ውሃውንም እንደ ግድግዳ አቆመው፡፡
\v 14 ቀን በደመና፣ ሌሊቱንም ሁሉ በእሳት ብርሃን መራቸው፡፡
\s5
\v 15 በምድረ በዳ ዐለቱን ሰነጠቀ እንደ ባሕር የበዛ ውሃ ሰጣቸው፡፡
\v 16 ከዐለቱ ምንጭ አፈለቀ ውሃውም እንደ ወንዝ እንዲፈስ አደረገ
\s5
\v 17 እነርሱ ግን ኃጢአት ማድረጋቸውን ቀጠሉ፤ በምድረ በዳ በልዑል ላይ ዐመፁ፡፡
\v 18 የተመኙትን ምግብ በመጠየቅ፣ ሆን ብለው እግዚአብሔርን ተፈታተኑት፡፡
\s5
\v 19 እንዲህ በማለትም በእግዚአብሔር ላይ ተናገሩ፣ «ለመሆኑ፣ እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድ ማዘጋጀት ይችላልን?»
\v 20 ዐለቱን ሲመታው ውሃ ተንዶለዶለ ጅረቶችም ጐረፉ፡፡ ታዲያ፣ እርሱ እንጀራንም መስጠት ይችላል? ለሕዝቡስ ሥጋ ማቅረብ ይችላል?
\s5
\v 21 ያህዌ ይህን ሲሰማ እጅግ ተቆጣ በያዕቆብ ላይ እሳት ነደደ በእስራኤልም ላይ ቁጣው ተቀጣጠሉ፡፡
\v 22 በእግዚአብሔር አላመኑም በእርሱም ማዳን አልተማመኑም፡፡
\s5
\v 23 ሆኖም እርሱ ከላይ ያሉትን ሰማያትን አዘዘ የሰማይንም በሮች ከፈተ
\v 24 ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ መና አዘነበላቸው የሰማይንም ምግብ ሰጣቸው፡፡
\v 25 ሰዎች የመላእክትን እንጀራ በሉ፡፡ ጠግበው እስከሚተርፍ ድረስ ምግብ ላከላቸው፡፡
\s5
\v 26 የምሥራቅን ነፋስ ከሰማይ አስነሣ የደቡብንም ነፍስ በኃይሉ አመጣ፡፡
\v 27 ሥጋን እንደ ዐፈር ብዙ ውፎችንም እንደ ባሕር አሸዋ አዘነበላቸው፡፡
\v 28 ሰፈራቸው መሓል በድንኳኖቻቸውም ዙሪያ አወረደ፡፡
\s5
\v 29 ስለዚህ እስኪጠግቡ ድረስ በሉ አጥብቀው የተመኙትን ሰጣቸው፡፡
\v 30 ነገር ግን ገና ምኞታቸውን ሳያረኩ፣ ምግቡ ገና አፋቸው ውስጥ እያለ፣
\s5
\v 31 የእግዚአብሔር ቁጣ እነርሱ ላይ ተነሣ የእስራኤልን ኃያላን ሰዎች ገደለ ምርጥ ወጣቶችንም በአጭር ቀጨ፡፡
\v 32 ይህም ሆኖ፣ ኃጢአት ማድረጋቸውን ቀጠሉ፤ ድንቅ ሥራዎቹንም አላመኑም፡፡
\s5
\v 33 ስለዚህ ዘመናቸውን አሳጠረ ዕድሜያቸውም በሽብር እንዲያልቅ አደረገ፡፡
\v 34 እርሱ በገደላቸው ጊዜ ፈለጉት ከልባቸው በመሻትም ወደ እርሱ ተመለሱ፡፡
\s5
\v 35 እግዚአብሔር ዐለታቸው፣ ልዑል አምላክ ታዳጊያቸው እንደ ሆነ አስቡ፡፡
\v 36 ነገር ግን በአፋቸው ሸነገሉት በአንደበታቸውም ዋሹት፡፡
\v 37 ልባቸው በእርሱ የጸና አልነበረም ለኪዳኑም ታማኞች አልነበሩም፡፡
\s5
\v 38 እርሱ ግን መሐሪ ስለሆነ ኃጢአታቸውን ይቅር አለ፤ እነርሱንም አላጠፋም ቁጣውን ብዙ ጊዜ ገታ መዐቱንም አላወረደም፡፡
\s5
\v 39 ካለፈ በኋላ እንደማይመለስ ነፋስ ሥጋ ለባሾች መሆናቸውን አሰበ፡፡
\v 40 በምድረ በዳ ስንት ጊዜ ዐመፁበት በበረሐስ ምን ያህል አሳዘኑት!
\v 41 ደግመው ደጋግመው እግዚአብሔርን ተፈታተኑት የእስራኤልንም ቅዱስ አስቆጡት፡፡
\s5
\v 42 ኃይሉን አላሰቡም፣ እነርሱን ከጠላቶቻቸው እጅ ያዳነበትን፣ ቀንና ታላቁን ኃይሉን አላስታወሱም፡፡
\v 43 በግብፅ አገር፣ በዞዓር ሜዳ ያደረጋቸውን ታላላቅ ድንቆችና ምልክቶች ዘነጉ፡፡
\s5
\v 44 ከወንዞቻቸው ወሃ መጠጣት እንዳይችሉ የግብፃውያንን ወንዞች ወደ ደም ለወጠ፡፡
\v 45 ተናዳፊ የዝንብ ሰራዊት ሰደደባቸው፣ ጓጉንቸርም ላከባቸው፤ ምድራቸውንም አጠፋ፡፡
\v 46 ሰብላቸውን ለኩብኩባ፣ ምርታቸውንም ለአንበጣ ሰጠ፡፡
\s5
\v 47 የወይን ተክላቸውን በበረዶ የበለስ ዛፎቻቸውንም በውርጭ አጠፋ፡፡
\v 48 ከብቶቻቸውን በበረዶ በጐቻቸውንም በመብረቅ ገደለ፡፡
\v 49 ጽኑ ቁጣውን በላያቸው ሰደደ መዓቱን፣ የቅናቱንም ቁጣና መቅሠፍት ላከባቸው አጥፊ የመላእክት ሰራዊትም ሰደደባቸው፡፡
\s5
\v 50 ለቁጣው መንገድ አዘጋጀ፤ ከሞትም አላዳናቸውም፡፡ ነገር ግን ሕይወታቸውን ለመቅሠፍት አሳልፎ ሰጠ፡፡
\v 51 የዐፍላ ጉልበታቸው መጀመሪያ የሆኑትን በካም ድንኳኖች፣ በኩሮቻቸውንም ሁሉ በግብፅ ምድር ፈጀ፡፡
\s5
\v 52 ሕዝቡን ግን እንደ በግ አሰማራቸው በምድረ በዳ እንደ መንጋ መራቸው
\v 53 በሰላም ስለ መራቸው አልፈሩም ጠላቶቻቸውን ግን ባሕር ዋጣቸው፡፡
\s5
\v 54 ከዚያም ወደ ተቀደሰች ምድሩ፣ ቀኝ እጁም ወዳስገኘው ወደዚህ ተራራ አመጣቸው፡፡
\v 55 ሕዝቦችን ከፊታቸው አባረረ ምድራቸውንም ርስት አድርጐ አከፋፈላቸው፡፡ የእስራኤል ነገዶችን በጠላቶቻቸው ድንኳን አኖረ፡፡
\s5
\v 56 እነርሱ ግን አምላክን ተፈታተኑት በልዑልም ላይ ዐመፁ፤ ትእዛዞቹንም አልጠበቁም፡፡
\v 57 እንደ አባቶቻቸው ዐመፀኞችና ከዳተኞች ሆኑ፡፡ እንደማያስተማምን ጠማማ ቀስት ተወላገዱ፡፡
\s5
\v 58 በኮረብታ ማምለኪያዎቻቸው አስቆጡት በጣዖቶቻቸውም አስቀኑት፡፡
\v 59 እግዚአብሔር በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ፡፡
\s5
\v 60 በሰዎች መካከል የኖረባትን ድንኳን፣ በሴሎ የነበረች ማደሪያውን ተዋት፡፡
\v 61 የኃይሉን ምልክት አስማረካት፣ ክብሩንም ለጠላቶች እጅ አሳልፎ ሰጠ፡፡
\s5
\v 62 ሕዝቡን ለሰይፍ ዳረገ በርስቱም ላይ እጅግ ተቆጣ፡፡
\v 63 ጐልማሶቻቸውን እሳት በላቸው ለልጃገረዶቻቸውም የሰርግ ዘፈን አልተዘፈነላቸውም፡፡
\s5
\v 64 ካህናቶቻቸው በሰይፍ ተገደሉ መበለቶቻቸው ማልቀስ ተሳናቸው፡፡
\v 65 ጌታም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ድፍረት እንደሚሰማው ጀግና ሆነ፡፡
\v 66 ጠላቶቹን መትቶ ወደ ኋላ መለሳቸው የዘላለም ውርደትንም አከናነባቸው፡፡
\s5
\v 67 የዮሴፍን ድንኳን ተዋት፣ የኤፍሬምንም ነገድ አልመረጠም፡፡
\v 68 ነገር ግን የይሁዳን ነገድና የወደዳትን የጽዮን ተራራ መረጠ፡፡
\v 69 መቅደሱን እንደ ሰማያት፣ እርሱ ለዘላለም እንደ መሠረታት ምድር ሠራት፡፡
\s5
\v 70 ባርያውን ዳዊትን መረጠ ከበጐች ጉረኖ ወሰደው፤
\v 71 ለሕዝቡ ለያዕቆብ፣ ለርስቱም ለእስራኤል እረኛ ሊደርገው የሚያጠቡ በጐችን ከመከተል አመጣው፡፡
\v 72 ዳዊትም በፍጹም ቅንነት ጠበቃቸው፤ በእጁ ብልኃትም መራቸው፡፡
\s5
\c 79
\p
\v 1 አምላክ ሆይ፣ ባዕድ ሕዝቦች ርስትህን ወረሩ! የተቀደሰ መቅደስህን አረከሱ ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር አደረጓት፡፡
\v 2 የባሪያዎችህን ሬሳ ለሰማይ ወፎች፣ የታማኞችህን ሥጋ ለምድር አራዊት ምግብ እንዲሆን ሰጡ፡፡
\v 3 ደማቸውን በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውሃ አፈሰሱ የሚቀብራቸውም አልተገኘም፡፡
\s5
\v 4 እኛም ለጐረቤቶቻችን መዘባበቻ በዙሪያችን ላሉትም መሣቂያ መሣለቂያ ሆንን፡፡
\v 5 ያህዌ ሆይ፣ ይህ እስከ መቼ ነው? የምትቆጣው ለዘላለም ነውን? ቅናትህ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራልን?
\s5
\v 6 አንተን በማያውቁ ሕዝቦች ላይ፣ ስምህን በማይጠሩ መንግሥታት ላይ መዓትህን አፍስስ፤
\v 7 ያዕቆብን ውጠውታልና መኖሪያ ቦታውንም ባድማ አድርገዋል፡፡
\s5
\v 8 የአባቶቻችንን ኃጢአት እኛ ላይ አትቁጠርብን እጅግ ተዋርደናልና ምሕረትህ ፈጥና ወደ እኛ ትምጣ፡፡
\v 9 መድኃኒታችን እግዚአብሔር ሆይ፣ ስለ ስምህ ክብር ርዳን፤ ይቅርም በለን፡፡
\s5
\v 10 ሕዝቦች፣ «አምካቸው የት አለ?» ለምን ይበሉ? ስለ ፈሰሰው የባሪያዎችህ ደም፣ ዐይናችን እያየ ሕዝቦችን ተበቀል፡፡
\v 11 የእስረኞች ሰቆቃ ወደ አንተ ይድረስ በኃይልህ ብርታት ሞት የተፈረደባቸውን አድን፡፡
\s5
\v 12 ጌታ ሆይ፣ ጐረቤቶቻችን አንተ ላይ ስለ ሰነዘሩት ስድብ ሰባት ዕጥፍ ተበቀላቸው፡፡
\v 13 እኛ ሕዝብህ፣ የመሰማሪያ በጐችህ ለዘላለም ምስጋና እናቀርብልሃለን፡፡ ለትውልድ ሁሉ ምስጋናህን እንናገራለን፡፡
\s5
\c 80
\p
\v 1 ዮሴፍን እንደ በግ መንጋ የምትመራ፣ የእስራኤል እረኛ ሆይ፣ ስማን፡፡ በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፣ ብርሃንህ ይብራልን!
\v 2 በኤፍሬም፣ በብንያምና በምናሴ ፊት ኃይልህን ግለጥ፤ መጥተህም አድነን፡፡
\v 3 አምላክ ሆይ፣ መልሰን ፊትህን አብራልን እኛም እንድናለን፡፡
\s5
\v 4 የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ በሕዝብህ ጸሎት ላይ የምትቆጣው እስከ መቼ ነው?
\v 5 የእንባ እንጀራ አበላሃቸው ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው፡፡
\v 6 የጐረቤቶቻችን መከራከሪያ አደረግኸን ጠላቶቻችንም ተሣሣቁብን፡፡
\s5
\v 7 የሰራዊት አምላክ ሆይ፣ ፊትህን አብራልን እኛም እንድናለን፡፡
\v 8 የወይን ግንድ ከግብፅ አመጣህ አሕዛብን አባርረህ እርሷን ተከልህ፡፡
\s5
\v 9 መሬቱን መነጠርህላት፣ እርሷም ሥር ሰድዳ መሬቱን ሞላች፡፡
\v 10 ተራሮችም በጥላዋ ተሸፈኑ የቅርንጫፎቿም ጥላ የሊባኖስን ዛፎች ሸፈነ፡፡
\v 11 ቅርንጫፎቿን እስከ ባሕሩ ቁጥቋጦዋንም እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ዘረጋች፡፡
\s5
\v 12 ታዲያ፣ አላፊ፣ አግዳሚው ፍሬዋን እንዲቀጥፍ በዙሪያዋ የነበሩ አጥሮችን ለምን አፈረስህ፡፡
\v 13 የዱር አሳማ ያበላሻታል በሜዳ የሚንጋጋም አራዊት ይበላታል፡፡
\s5
\v 14 የሰራዊት አምላክ ሆይ፣ ወደ እኛ ተመለስ፣ ከሰማይ ተመልከት እይም ይህችን የወይን ተክልም ተንከባከባት፡፡
\v 15 ይህች ቀኝ እጅህ የተከላት ተክል አንተም ያጸደቅሃት ተክል ናት፡፡
\v 16 ነገር ግን ቆራርጠው በእሳት አቃጠሏት ከቁጣህ የተነሣ ይጠፋሉ፡፡
\s5
\v 17 እጅህ የቀኝ እጅህ የሆነው ሰው ላይ፣ አንተ ራስህ ብርቱ ያደረግኸው የሰው ልጅ ላይ ትሁን
\v 18 እኛም ከአንተ ወደ ኋላ አንልም፤ በሕይወት ጠብቀን፤ እኛም ስምህን እንጠራለን፡፡
\s5
\v 19 ሰራዊት አምላክ ያህዌ ሆይ፣ መልሰን ፊትህን አብራልን እኛም እንድናለን፡፡
\s5
\c 81
\p
\v 1 ብርታታችን ለሆነው አምላክ በደስታ ዘምሩ ለያዕቆብ አምላክ በደስታ እልል በሉ፡፡
\v 2 ለመዘመር ተነሡ፤ ከበሮም ምቱ በበገናና በመሰንቆ ደስ የሚል ዜማ አሰሙ፡፡
\v 3 በሙሉ ጨረቃ በክብረ በዓላችን ቀን በወሩ መግቢያ ጨረቃ ስትወለድ ቀንደ መለከት ንፉ፡፡
\s5
\v 4 ይህም ለእስራኤል የተደነገገ፣ የያዕቆብ አምላክ የሰጠው ሥርዐት ነው፡፡
\v 5 ግብፅን ለቅቆ በወጣ ጊዜ ይህን ለዮሴፍ ደነገገ፤ በማላውቀውም ቋንቋ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤
\s5
\v 6 «ከትከሻው ሸክምን አስወገድሁ እጆቹንም ቅርጫት ከመያዝ አሳረፍሁ፡፡
\v 7 በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ረዳሁህ በነጐድጓድ መሰወሪያ ውስጥ መለስሁልህ በመሪባ ውሃ ዘንድ ፈተንሁህ፡፡ ሴላ
\s5
\v 8 ሕዝቤ ሆይ፣ ሳስጠነቅቅህ ስማኝ እስራኤል ሆይ፣ ምነው ባደመጥኸኝ!
\v 9 ባዕድ አምላክ በመካከልህ አይሁን ሌሎች አማልክት አታምልክ፡፡
\v 10 እኔ ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ አምላክህ ያህዌ ነኝ፡፡ አፍህን በሰፊው ክፈት፤ እኔም እሞላዋለሁ፡፡
\s5
\v 11 ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰማም እስራኤልም ለእኔ አልታዘዝም፡፡
\v 12 ስለዚህ በእልከኝነት መንገዳቸው እንዲሄዱ፣ የፈለጉትንም እንዲያደርጉ ተውኳቸው፡፡
\s5
\v 13 ምነው ሕዝቤ ባደመጠኝ ኖሮ፣ እስራኤል በመንገዴ ሄዶ ቢሆን ኖሮ፡፡
\v 14 ፈጥኜ ጠላቶቻቸውን አስገዛላቸው ነበር እጄንም በጨቋኞቻቸው ላይ ባነሣሁ ነበር፡፡
\s5
\v 15 ያህዌን የሚጠሉ በፊቱ በፍርሃት ይሸማቀቃሉ! ለዘላለምም ያፍራሉ፡፡
\v 16 እስራኤልን ግን ምርጡን ስንዴ አበላዋለሁ ከዐለት ከሚገኘውም ማር አጠግባችኋለሁ፡፡»
\s5
\c 82
\p
\v 1 እግዚአብሔር በአማልክት ጉባኤ ቆመ፤ በአማልክትም ላይ፣ ይፈርዳል እንዲህም ይላል፤
\v 2 ፍትሕ የምታጓድሉት እስከ መቼ ነው? ለክፉዎች የምታደሉትስ እስከ መቼ ነው? ሴላ
\s5
\v 3 ለድኾችና ለሙት ልጆች ተሟገቱ፤ የችግረኛውንና የምስኪኑን መብት አስከብሩ፡፡
\v 4 ድኾችንና ምስኪኖችን ታደጉ፤ ከዐመፀኞችም እጅ አስጥሏቸው፡፡
\s5
\v 5 ዕውቀትም ሆነ ማስተዋል የላቸውም በጨለማ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይመላለሳሉ የምድር መሠረቶችም ተናወጡ፡፡
\s5
\v 6 እኔም፣ «እናንተ አማልክት ናችሁ፤ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ አልሁ፡፡
\v 7 ሆኖም፣ እንደ ማንኛውም ሰው ትሞታላችሁ እንደ ማንኛውም ገዥ ትወድቃላችሁ፡፡»
\s5
\v 8 እግዚአብሔር ሆይ፣ ተነሥ፤ ሕዝቦች ሁሉ ርስትህ ናቸውና፤ በምድር ላይ ፍረድ፡፡
\s5
\c 83
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ ዝም አትበል አትተወን ችላ አትበል፡፡
\v 2 ጠላቶችህ እንዴት እንደ ተነሣሡ ባላንጣዎችህም እንዴት ራሳቸውን ቀና ቀና እንዳደረጉ ተመልከት፡፡
\s5
\v 3 በሕዝብህ ላይ ያደባሉ፣ አንተ በምትጠብቃቸውም ላይ ያሣራሉ፡፡
\v 4 ‹የእስራኤል ስም ከእንግዲህ እንዳይታሰብ፣ ኑና ሕዝብ እንዳይሆኑ እንደምስሳቸው» አሉ፡፡
\v 5 በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ተማከሩ አንተም ላይ ተማማሉ፡፡
\s5
\v 6 የኤዶምና የእስማኤላውያን፣ የሞዓብና የአጋራውያን ድንኳኖች፣
\v 7 ጌባል አሞንና አማሌቅ፣ ፍልስጥኤምም ከጢሮስ ሕዝብ ጋር አብረው ዶለቱ፡፡
\s5
\v 8 አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ የሎጥም ልጆች ረዳት ሆነ፡፡ ሴላ
\s5
\v 9 ምድያም ላይ እንዳደረግኸው አድርግባቸው በቂሶን ወንዝ በሲሣራና በኢያቢስ ላይ ያደረስኸው ይድረስባቸው፡፡
\v 10 እነርሱ በዐይንዶር ጠፉ እንደ ምድር ትቢያ ሆኑ፡፡
\s5
\v 11 እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፣ መሳፍንቶቻቸውንም እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፤
\v 12 እነርሱም፣ «የእግዚአብሔርን ግጦሽ ቦታ እንውሰድ» አሉ፡፡
\s5
\v 13 አምላኬ ሆይ፣ በዐውሎ ነፋስ እንደሚወሰድ ትቢያ፣ ነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ አድርጋቸው፡፡
\v 14 እሳት ደንን እንደሚያቃጥል ተራራውን እንደሚያዳርስ እሳት ነበልባል
\v 15 እንዲሁ በማዕበልህ አሳዳቸው በሞገድህም አስደንግጣቸው፡፡
\s5
\v 16 አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ ስምህን ይሹ ዘንድ፣ ፊታቸውን በእፍረት ሙላ፤
\v 17 ለዘላለም ይፈሩ ይታወኩም፤ በውርደትም ይጥፉ፡፡
\s5
\v 18 ስምህ ያህዌ የሆነው አንተ ብቻ በምድር ላይ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ፡፡
\s5
\c 84
\p
\v 1 የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ ማደሪያህ ምንኛ ያማረ ነው፡፡
\v 2 ነፍሴ የያህዌን አደባባዮች ትናፍቃለች እጅግም ትጓጓለች፡፡ ልቤና ሁለንተናዬ ሕያው እግዚአብሔርን ይጣራሉ፡፡
\s5
\v 3 ንጉሤና አምላኬ የሰራዊት አምላክ ሆይ፣ መሠዊያህ ባለበት ስፍራ ድንቢጥ እንኳ መኖሪያ ቤት ዋኖስም ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቦታ አገኘች፡፡
\v 4 በቤትህ የሚኖሩ የተባረኩ ናቸው፤ እነርሱ ለዘላለም ያመሰግኑሃል፡፡ ሴላ
\s5
\v 5 አንተን ብርታታቸው ያደረጉ በልባቸው የጽዮንን መንገድ የሚያስቡ ቡሩካን ናቸው፡፡
\v 6 በልቅሶ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ የሚጠጡት የምንጭ ውሃ ያገኛሉ የበልግም ዝናብ ይሞላዋል፡፡
\s5
\v 7 ከኃይል ወደ ኃይል ይሸጋገራሉ እያንዳንዱም በጽዮን ባለው አምላክ ፊት ይቀርባል፡፡
\v 8 የሰራዊት አምላክ ያህዌ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፣ የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ ቃሌን አድምጥ፡፡ ሴላ
\v 9 አምላክ ሆይ፣ ጋሻችንን ጠብቅ፣ ለቀባኸውም ራራለት፡፡
\v 10 በሌላ ቦታ ሺህ ቀን ከመኖር፣ አንዲት ቀን በአደባባይህ መዋል ይሻላል፡፡
\s5
\v 11 አምላካችን ያህዌ ፀሐይና ጋሻችን ነውና፤ ያህዌ ጸጋንና ክብርን ይሰጣል፤ በቅንነት የሚሄዱትን መልካም ነገር አይነፍጋቸውም፡፡
\v 12 የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ በአንተ የተማመነ ሰው ቡሩክ ነው፡፡
\s5
\c 85
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ለምድርህ ሞገስ አሳየህ የያዕቆብን ምርኮ መለስህ፡፡
\v 2 የሕዝብህን ኃጢአት ይቅር አልህ በደላቸውንም ሸፈንህ፡፡ ሴላ
\s5
\v 3 መዓትህን ሁሉ አራቅህ ከጽኑ ቁጣህም ተመለስህ፡፡
\v 4 አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ፣ መልሰን፤ በእኛ ያዘንህብንን ሁሉ አርቅልን፡፡
\v 5 የምትቆጣን ለዘላለም ነውን? ቁጣህንስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ታስተላልፋለህን?
\s5
\v 6 እኛ ሕዝብህ በአንተ ደስ እንዲለን እንደ ገና በሕይወት አታኖረንምን?
\v 7 ያህዌ ሆይ፣ የኪዳን ታማኝነትህን አሳየን ማዳንህንም ስጠን፡፡
\s5
\v 8 ያህዌ አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ እንደ ገና በስሕተት መንገድ ካልሄዱ በቀር ለሕዝቡና ለታማኞቹ ሰላምን ያደርጋል፡፡
\v 9 ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ ማዳኑ ለሚፈሩት በእርግጥ ቅርብ ነው፡፡
\s5
\v 10 ምሕረትና ታማኝነት ተገናኙ፡ ጽድቅና ሰላም ተሳሳሙ፡፡
\v 11 ታማኝነት ከምድር በቀለች ጽድቅ ከሰማይ ተመለከተች፡፡
\s5
\v 12 ያህዌ መልካም ነገር ይሰጣል ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች፡፡
\v 13 ጽድቅ በፊቱ ትሄዳለች ለአረማመዱም መንገድ ያዘጋጃል፡፡
\s5
\c 86
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ እኔ ድኻና ምስኪን ነኝና እባክህ ስማኝ መልስልኝም፡፡
\v 2 እኔ ለአንተ ታማኝ ስለሆንሁ ጠብቀኝ አምላኬ ሆይ፤ በአንተ የታመነውን ባርያህን አድነው፡፡
\s5
\v 3 ጌታ ሆይ፣ ቀኑን ሙሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና እባክህ ማረኝ፡፡
\v 4 ጌታ ሆይ፣ ወደ አንተ እጸልያለሁና ባርያህን ደስ አሰኘው፡፡
\s5
\v 5 ጌታ ሆይ፣ አንተ መልካምና ይቅር ባይ ነህ ለሚጠሩህ ሁሉ ምሕረትህ ወሰን የለውም፡፡
\v 6 ያህዌ ሆይ ጸሎቴን አድምጥ የልመናዬንም ጩኸት ስማ፡፡
\v 7 አንተ ስለምትመልስልኝ በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጣራለሁ፡፡
\s5
\v 8 ጌታ ሆይ፣ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ የለም፡፡ ከአንተ ሥራ ጋር የሚወዳደር ሥራ የለም፡፡
\v 9 ጌታ ሆይ፣ የሠራሃቸው ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊት ይሰግዳሉ፡፡ ስምህን ያከብራሉ፡፡
\s5
\v 10 አንተ ታላቅ ነህና ተአምራትን ታደርጋለህ አንተ ብቻህን አምላክ ነህ፡፡
\v 11 ያህዌ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረን፤ እኔም በእውነትህ እሄዳለሁ፡፡ ባልተከፋፈለ ልብም እንዳከብርህ አድርገኝ፡፡
\v 12 ጌታ አምላኬ ሆይ፣ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ ስምህንም ለዘላለም አከብራለሁ
\s5
\v 13 ለእኔ የምታሳየው ዘላለማዊው ፍቅርህ እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ነፍሴንም ከጥልቁ ሲኦል አወጣሃት፡፡
\v 14 አምላክ ሆይ፣ እብሪተኞች ተነሥተውብኛል የክፉዎች ጉባኤ ነፍሴን ይፈልጓታል፡፡ አንተንም ከምንም አልቆጠሩም፡፡
\s5
\v 15 አንተ ግን ጌታ ሆይ፣ መሐሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ ለቁጣ የዘገየህ፣ ምህረትህና ታማኝነትህ የበዛ ነው፡፡
\v 16 ወደ እኔ ተመለስ ማረኝም ለባሪያህ ብርታትህን ስጥ የሴት ባሪያህንም ልጅ አድን፡፡
\v 17 የሞገስህን ምልክት አሳየኝ አንተ ያህዌ ረድተኸኛልና አጽናንተኸኛልምና የሚጠሉኝ ይህን አይተው ያፍራሉ፡፡
\s5
\c 87
\p
\v 1 እግዚአብሔር ከተማውን፣ በተቀደሰው ተራራ ላይ መሠረተ
\v 2 ያህዌ የጽዮንን ደጆች ከያዕቆብ መኖሪያዎች ይበልጥ ይወዳል፡፡
\v 3 የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፣ ስለ አንቺ አስደናቂ ነገሮች ተነግረዋል፡፡ ሴላ
\s5
\v 4 ከሚያውቁኝ መካከል ረዓብንና ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤ እነሆ ፍልስጥኤምና ጢሮስ ከኢትዮጵያ ጋር ሆነው፣ «ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው› ይላሉ፡፡
\s5
\v 5 ስለ ጽዮን ግን፣ ልዑል እግዚአብሔር ራሱ ስለሚመሠርታት፣ «እነዚህ ሁሉ የተወለዱ እዚያ ነው» ይላሉ፡፡
\v 6 ያህዌ ሕዝቦችን ሲመሠርት «ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው» ብሎ ይጽፋል፡፡
\s5
\v 7 ዘማሪዎችና መሣሪያ ተጫዋቾችም፣ «ምንጩ ሁሉ አንቺ ውስጥ ይገኛል» ይላሉ፡፡
\s5
\c 88
\p
\v 1 አዳኜ ያህዌ አምላክ ሆይ፤ ቀንና ሌሊት በፊትህ እጮኻለሁ፡፡
\v 2 እባክህ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፡፡
\s5
\v 3 በመከራ ተሞልቻለሁና ነፍሴም ወደ ሲኦል ተቃርባለች፡፡
\v 4 ወደ መቃብር ከሚወርዱ ጋር ተቆጥሬአለሁ፤ ዐቅም አጣሁ፡፡
\s5
\v 5 በሙታን መካከል ፈጽሞ እንደ ተተዉ ሞተው መቃብር ውስጥ እንደ ተጋደሙ ከእንግዲህ ፈጽሞ እንደማታስታውሳቸውና ከእጅህ ወጥተው እንደ ተወገዱ ሆንሁ፡፡
\v 6 ጥልቁ አዘቅት ውስጥ ጣልኸኝ ጨለማ ጉድጓድ ውስጥ ከተትኸኝ፡፡
\s5
\v 7 ቁጣህ እጅግ ከብዶኛል ማዕበልህም ሁሉ አጥለቅልቆኛል፡፡
\s5
\v 8 ወዳጆቼን ሁሉ ከእኔ አራቅህ እንዲጸየፉኝም አደረግህ ዙሪያውን ተከብቤአለሁና ማምለጥ አልችልም፡፡
\s5
\v 9 ዐይኖቼ በሐዘን ፈዘዙ ያህዌ ሆይ፣ ቀኑን ሙሉ ወደ አንተ እጮኻለሁ እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፡፡
\v 10 ለሙታን ተአምራት ታደርጋለህን? የሞቱትስ ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? ሴላ
\s5
\v 11 ምሕረትህ መቃብር ውስጥ ታማኝነትህስ በሙታን ዓለም ይነገራልን?
\v 12 ድንቅ ሥራህ በጨለማ ስፍራ ጽድቅህስ በመረሳት ምድር ትቃወቃለችን?
\s5
\v 13 ያህዌ ሆይ፣ እኔ ግን ወደ አንተ እጮኻለሁ በጧትም ጸሎቴን ወደ ፊት አቀርባለሁ፡፡
\v 14 ያህዌ ሆይ፣ ለምን ትተወኛለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?
\s5
\v 15 ከልጅነቴ ጀምሮ ችግረኛና ሞት አፋፍ ላይ ያለሁ ሰው ነበርሁ፤ ከማስደንገጥህ የተነሣ ተስፋ ቆርጫለሁ፡፡
\v 16 ቁጣህ እኔ ላይ ተከነበለ መዓትህም አጠፋኝ፡፡
\s5
\v 17 ቀኑን ሙሉ እንደ ጐርፍ ከበቡኝ ዙሪያውን አጥረው ያዙኝ፡፡፡
\v 18 ወዳጆቼንና የሚቀርቡኝን ሰዎች ሁሉ ከእኔ አራቅህ ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ፡፡
\s5
\c 89
\p
\v 1 ስለ ያህዌ ምሕረት ለዘላለሙ እዘምራለሁ፡፡ ታማኝነትህንም ለሚመጣው ትውልድ እናገራለሁ፡፡
\v 2 ምሕረትህን ለዘላለም እንደምትመሠርት ታማኝነትህንም በሰማያት እንደምታጸና እናገራለሁና
\s5
\v 3 አንተም እንዲህ ብለሃል፣ «ከመረጥሁት ጋር ኪዳን አድርጌአለሁ፤ ለባርያዬ ለዳዊት ምዬአለሁ፡፡
\v 4 ዘርህን ለዘላለም አተክላለሁ ዙፋንህንም በትውልድ ዘመን ሁሉ አጸናለሁ፡፡» ሴላ
\s5
\v 5 ያህዌ ሆይ፣ ሰማያት ድንቅ ሥራህን ያመሰግናሉ ጽድቅህም በቅዱሳን ጉባኤ ይወደሳል፡፡
\v 6 በላይ በሰማያት ከያህዌ ጋር ማን ሊስተካከል ይችላል? ከአማልክት ልጆችስ መካከል እንደ ያህዌ ያለ ማን ነው?
\s5
\v 7 እርሱ በቅዱሳኑ ጉባኤ መካከል እጅግ የተፈራ ነው፤ በዙሪያው ካሉትም ሁሉ ታላቅና አስፈሪ ነው፡፡
\v 8 የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ኃያል ማነው? ታማኝነትህም ከቦሃል፡፡
\s5
\v 9 የባሕሩን ቁጣ በሥልጣንህ ታዝዛለህ ማዕበሉንም ጸጥ ታደርጋለህ፡፡
\v 10 አንተ ረዓብን ቀጥቅጠህ ገደልኸው በታላቁ ኃይልህ ጠላቶችህን በተንሃቸው፡፡
\s5
\v 11 ሰማያት የአንተ ናቸው ምድርም የአንተ ናት፡፡ አንተ ዓለምንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ ፈጠርህ፡፡
\v 12 ሰሜኑን ደቡቡንም አንተ ፈጠርህ ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል፡፡
\s5
\v 13 አንተ ክንደ ብርቱ ነህ እጅህ ኃያል ናት፤ ቀኝ እጅህም ከፍ ከፍ ያለች ናት፡፡
\v 14 ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረት ናቸው ምሕረትና ታማኝነት በፊት ይሄዳሉ፡፡
\s5
\v 15 ያህዌ ሆይ፣ በፊት ብርሃን የሚሄድ አንተንም የሚያመልክ ሕዝብ ቡሩክ ነው፡፡
\v 16 ቀኑን ሙሉ በስምህ ደስ ይላቸዋል በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ፡፡
\s5
\v 17 ገናናው ኃይልህ ብርታት ይሰጣቸዋል በሞገስህም ድል ተቀዳጀን፡፡
\v 18 ጋሻችን የያህዌ ነው ንጉሣችንም የራሱ የእስራኤል ቅዱስ ነውና፡፡
\s5
\v 19 ከረጅም ጊዜ በፊት በራእይ ለሕዝብህ ተናገርህ እንዲህም አልህ፤ «ኃያሉን ሰው ሥልጣን አጐናጸፍሁ፤ ከሕዝብ መካከል እኔ የመረጥሁትን አስነሣሁ፡፡
\v 20 ባርያዬ ዳዊትን መረጥሁት በተቀደሰው ዘይቴም ቀባሁት
\v 21 እጄ ይደግፈዋል ክንዴም ያበረታዋል፡፡
\v 22 ጠላት አይረታውም ክፉ ሰውም አያሸንፈውም፡፡
\v 23 ጠላቶቹን በፊቱ አደቃለሁ፤ ባላንጣዎቹንም እገድላለሁ፡፡
\s5
\v 24 እውነቴና ታማኝነቴ ከእርሱ ጋር ይሆናል በስሜ ድል ይቀዳጃል፡፡
\v 25 እጁን በባሕሮች ቀኝ እጁንም በወንዞች ላይ አደርጋለሁ፡፡
\v 26 እርሱም፣ «አንተ አባቴ፣ አምላኬ የድነቴም ዐለት» ብሎ ይጠራኛል፡፡
\s5
\v 27 እኔም ደግሞ በኩሬ አደርገዋለሁ ከምድር ነገሥታትም ሁሉ በላይ ከፍ ይላል፡፡
\v 28 ምሕረቴንም ለዘላለም ለእርሱ እዘረጋለሁ ለእርሱ ጋር ያደረግሁትም ኪዳን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፡፡
\v 29 የዘር ሐረጉን ለዘላለም ዙፋኑንም በሰማያት ዕድሜ ልክ አጸናለሁ
\s5
\v 30 ልጆቹ ሕጌን ቢተው፣ ሥርዐቴን ባይጠብቁ፣
\v 31 ደንቤን ቢተላለፉ፣ ትእዛዞቼ ባያከብሩ፣
\v 32 ኃጢአታቸውን በበትር፣ በደላቸውንም በአለንጋ እቀጣለሁ፡፡
\s5
\v 33 ለእርሱ ያለኝ ፍቅር ግን አይቋረጥም ታማኝነቴንም አላጓድልበትም፡፡
\v 34 ኪዳኔን አላፈርስም ከአፌ የወጣውን አላጥፍም፡፡
\s5
\v 35 አንዴ በቅድስናዬ ምያለሁና ለዳዊት አልዋሽም፡፡
\v 36 ልጆቹ ለዘላለም ዙፋኑም በፀሐይ ዕድሜ ልክ ጸንቶ ይኖራል፡፡
\v 37 በሰማይ ታማኝ ምስክር ሆና እንደምትኖረው እንደ ጨረቃ እርሱም ለዘላለም ይመሠረታል፡፡ ሴላ
\s5
\v 38 አሁን ግን ናቅኸው፤ ጣልኸውም በቀባኸውም ንጉሥ ላይ ተቆጣህ፡፡
\v 39 ለባርያህ የገባኸውን ኪዳን አፈረስህ የክብር ዘውዱን መሬት ላይ ጣልህ፡፡
\v 40 ቅጥሮቹን ሁሉ አፈረስህ ምሽጉንም ደመሰስህ፡፡
\s5
\v 41 ዐላፊ አግዳሚ ሁሉ ዘረፈው ለጐረቤቶቹም መዘባበቻ ሆነ፡፡
\v 42 የጠላቶቹን ቀኝ እጅ ከፍ አደረግህ ባላንጣዎቹም ሁሉ ደስ አላቸው፡፡
\v 43 የሰይፉን ስለት አጠፍህ በጦርነትም ጊዜ አልረዳኸውም፡፡
\s5
\v 44 የክብሩን ውበት አጠፋህበት ዙፋኑንም መሬት ላይ ጣልህበት፡፡
\v 45 የወጣትነት ዘመኑን አሳጠርኸው ዕፍረትንም አከናነብኸው፡፡
\s5
\v 46 ያህዌ ሆይ፣ ይህ እስከ መቼ ነው? ራስህንስ ለዘላለም ትሰውራለህን? ቁጣህስ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው?
\v 47 ዕድሜዬ ምን ያህል አጭር እንደ ሆነ አስብ፤ የሰውን ልጆች እንዲሁ ለከንቱ ፈጠርሃቸው!
\v 48 ሞትን ሳያይ ሕያው ሆኖ የሚኖር ማን ነው? ሕይወቱን ከሲኦል እጅ ማዳን የሚችል ማነው? ሴላ
\s5
\v 49 ጌታ ሆይ፣ በታማኝነትህ ለዳዊት የማልህለት የቀድሞ ምሕረትህ የታለ?
\v 50 ጌታ ሆይ፣ ባርያህ ላይ የደረሰውን ፌዝ የብዙ ሰዎችንም ስድብ እንደ ታቀፍሁ አስብ፡፡
\v 51 ያህዌ ሆይ፣ ጠላቶችህ የሚሳደቡትን፣ አንተ የቀባኸውን ሰው ርምጃ የነቀፉበትን ሁኔታ አስብ፡፡
\s5
\v 52 ያህዌ ለዘላለም ይባረክ፡፡ አሜን፣ አሜን
\s5
\c 90
\p
\v 1 ጌታ ሆይ፣ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መጠጊያችን ነህ፡፡
\v 2 ተራሮችን ከመሥራትህና ዓለምንም ከመፍጠርህ በፊት አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ
\s5
\v 3 ሰዎችን ወደ ዐፈር ትመልሳለህ፤ «የሰው ልጆች ሆይ ወደ ቦታችሁ ተመለሱ» ትላለህ፡፡
\v 4 ሺህ ዓመት በፊትህ፣ እንዳለፈው ትናንት ቀን እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓቶች ነው፡፡
\s5
\v 5 እንደ ጐርፍ ጠርገህ ስትወስዳቸው እንደ ሕልም ይበናሉ በየማለዳው እንደሚታደስ የሣር ቡቃያ ይሆናሉ፡፡
\v 6 ሣር ወዲያው አድጐ ያብባል ሲመሽ ግን ጠውልጐ ይጠፋል፡፡
\s5
\v 7 እኛ በቁጣህ ጠፍተናል በመዓትህም ደንግጠናል፡፡
\v 8 ኃጢአታችንን በፊትህ፣ የተሰወረ ኃጢአታችንንም በግልጽ በሚታይ ቦታ ታኖራለህ፡፡
\s5
\v 9 ዘመናችን ሁሉ በቁጣህ ያልፋል ዕድሜያችንም በቅጽበት እንደሚያልፍ እስትንፋስ ነው፡፡
\v 10 ዕድሜያችን ሰባ፣ ጤነኞች ከሆንንም ሰማንያ ዓመት ነው፡፡ እነዚያም ቢሆኑ፣ በመከራና ሐዘን የተሞሉ ናቸው፡፡ ዕድሜያችን ቶሎ ያልቃል፤ እኛም ወዲያው እንነጉዳለን፡፡
\s5
\v 11 የቁጣህን ኃይል ማን ያውቃል? መዓትህም የመፈራትህን ያህል ታላቅ ነው፡፡
\v 12 ጥበበኞች መሆን እንድንችል ዕድሜያችን ምን ያህል መሆኑን አስተምረን፡፡
\v 13 ያህዌ ሆይ፣ ተመለስ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል፤ ለባሪያዎችህም ራራላቸው፡፡
\s5
\v 14 በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣ ሐሤትም እንድናደርግ በማለዳ ምሕረትህን አጥግበን፡፡
\v 15 መከራ ባየንበት ዘመን መጠን ችግር ባየንባቸው ዓመታት ልክ ደስ አሰኘን፡፡
\v 16 እኛ ባርያዎችህ ታላቁን ሥራህን፣ ልጆቻችንም ግርማህን እንዲያዩ ፍቀድልን፡፡
\s5
\v 17 የጌታ አምላካችን ሞገስ እኛ ላይ ይሁን የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ ያድርግልን አዎን ፍሬያማ ያድርግልን፡፡
\s5
\c 91
\p
\v 1 በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ሥር ያድራል፡፡
\v 2 ያህዌን፣ «መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ» እለዋለሁ፡፡
\s5
\v 3 ከአዳኝ ወጥመድ ከአደገኛም መቅሠፍት ያድንሃል
\v 4 በላባዎቹ ይጋርድሃል በክንፎቹም ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፡፡ ታማኝነቱም ጋሻና መከታ ይሆንልሃል፡፡
\s5
\v 5 የሌሊትን ሽብር፣ በቀን ከሚወረወር ፍላጻም አትፈራም
\v 6 በጨለማ ከሚያደባ ቸነፈር በቀትርም ከሚወርድ መቅሠፍት አትሰጋም፡፡
\v 7 በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም ዐሥር ሺህ ይወድቃሉ ወደ አንተ ግን አይቀርብም፡፡
\s5
\v 8 በዐይንህ ብቻ ታያለህ የክፉዎችንም መቀጣት ትመለከታለህ፡፡
\v 9 አንተ ያህዌን መሸሸጊያ ልዑል አምላክንም መጠጊያህ አድርገኸዋልና፡፡
\s5
\v 10 ክፉ ነገር አያገኝህም መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይጠጋም፡፡
\v 11 በመንገድህ ሁሉ እንዲጠብቁህ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋል፡፡
\s5
\v 12 እግሮችህ በድንጋይ እንዳይሰናከሉ በእጆቻቸው ያነሡሃል፡፡
\v 13 አንበሳና እፉኝት ላይ ትጫማለህ ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ፡፡
\s5
\v 14 ወዶኛልና አታደገዋለሁ በእኔ ተማምኖአልና እጠብቀዋለሁ፡፡
\v 15 ይጠራኛል እኔም እመልስለታለሁ በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ ድል አቀዳጀዋለሁ፤ አከብረውማለሁ፡፡
\v 16 ረጅም ዕድሜ አጠግበዋለሁ ማዳኔንም አሳየዋለሁ፡፡
\s5
\c 92
\p
\v 1 ያህዌን ማመስገን መልካም ነው፤ ልዑል ሆይ፣ ለስምህ መዘመር መልካም ነው፡፡
\v 2 ምህረትህን በማለዳ ታማኝነትህን በሌሊት ማወጅ መልካም ነው፡፡
\v 3 ዐሥር አውታር ባለው በገና ከመሰንቆም ጣዕመ ዜማ ጋር ማወጅ መልካም ነው፡፡
\s5
\v 4 ያህዌ ሆይ፣ በሥራህ ደስ ስላሰኘኸኝ ስለ እጅህ ሥራ በደስታ እዘምራለሁ፡፡
\v 5 ያህዌ ሆይ፣ ሥራህ እንዴት ታላቅ ነው? ሐሳብህ እጅግ ጥልቅ ነው፡፡
\s5
\v 6 ደነዝ ሰው ይህን አያስተውልም ሞኝም ይህን አይረዳም፣
\v 7 ክፉ ሰዎች እንደ ሣር ቢበቅሉ ተንኰለኞችም ቢለመልሙ ለዘላለሙ ይጠፋሉ፡፡
\s5
\v 8 አንተ ግን ያህዌ ሆይ፣ ለዘላለም ትነግሣለህ፡፡
\v 9 ጠላቶችህ ያህዌ ሆይ፣ ጠላቶችህ ይጠፋሉ ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ይበተናሉ፡፡
\s5
\v 10 እንደ ጐሽ ቀንድ ቀንዴን ከፍ ከፍ አደረግህ በትኩስ ዘይትም ቀባኸኝ፡፡
\v 11 ዐይኖቼ የባላንጣዎቹን ውድቀት አዩ ጆሮቼም የክፉ ጠላቶቼን ጥፋት ሰሙ፡፡
\s5
\v 12 ጻድቃን እንደ ዘንባባ ዛፍ ይለመልማሉ እንደ ሊባኖስ ዛፍም ያድጋሉ፡፡
\v 13 በያህዌ ቤት ተተክለዋል በአምላካችን አደባባይ ይንሰራፋሉ፡፡
\s5
\v 14 ባረጁ ጊዜ እንኳ ያፈራሉ እንደ ለመለሙና እንደ ጠነከሩም ይኖራሉ፡፡
\v 15 እግዚአብሔር ትክክለኛ ነው፤ እርሱ ዐለቴ ነው፤ በእርሱ ዘንድ እንከን የለም፡፡
\s5
\c 93
\p
\v 1 ያህዌ ነገሠ ግርማንም ለበሰ፣ ያህዌ ግርማን ተጐናጸፈ ብርታትንም ታጠቀ ዓለምን በአንድ ስፍራ አጸናት፤ ከቶም አትናወጥም፡፡
\v 2 ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው አንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም ነህ፡፡
\s5
\v 3 ያህዌ ሆይ፣ ባሕሮች ይነሣሉ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው ይጮኻሉ ወንዞች የሚያስገመግም ማዕበላቸውን ከፍ አደረጉ፡፡
\v 4 ከብዙ ውሆች ድምፅ ይልቅ ከባሕርም ሞገድ ይልቅ ከፍ ብሎ ያለው ያህዌ ብርቱ ነው፡፡
\s5
\v 5 ትእዛዛትህ ያጸኑ ናቸው ያህዌ ሆይ፣ ቤትህ ለዘላለም በቅድስና ይዋባል፡፡
\s5
\c 94
\p
\v 1 የበቀል አምላክ አንተ ያህዌ ሆይ፣ የበቀል አምላክ ሆይ፣ ብርሃንህ ይብራልን፡፡
\v 2 የምድር ዳኛ ሆይ፣ ተነሥ ለትዕቢተኞች የእጃቸውን ስጣቸው፡፡
\s5
\v 3 ያህዌ ሆይ፣ ክፉዎች እስከ መቼ፣ ክፉዎች እስከ መቼ ነው የሚፈነጩት?
\v 4 የእብሪት ቃሎች ያዥጐደጉዳሉ ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ጉራ ይነዛሉ፡፡
\s5
\v 5 ያህዌ ሆይ፣ ሕዝብህን ያደቅቃሉ የአንተን ወገኖች ይጨቁናሉ፡፡
\v 6 በአገራቸው የሚኖሩ መበለቶችንና መጻተኞችን ይገድላሉ፤
\v 7 «ያህዌ አያይም፤ የያዕቆብ አምላክም አያስተውልም» ይላሉ፡፡
\s5
\v 8 እናንት አላዋቂዎች ይህን አስተውሉ፤ እናንት ሞኞች ለመሆኑ፣ ጥበበኞች የምትሆኑት መቼ ነው?
\v 9 ጆሮን የተከለ እርሱ አይሰማምን? ዐይንን የሠራ እርሱ አያይምን?
\s5
\v 10 ሕዝቦችን የሚገሥጸው አይቀጣምን? ለሰው ዕውቀት የሚሰጥ እርሱ ነው፡፡
\v 11 ያህዌ የሰው ሐሳብ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል፡፡
\s5
\v 12 ያህዌ ሆይ፣ አንተ የምትገሥጸው ሕግህንም የምታስተምረው ሰው ቡሩክ ነው፡፡
\v 13 ለክፉዎች ጉድጓድ እስኪቆፈር ድረስ አንተ እርሱን ከመከራ ታሳርፈዋለህ፡፡
\s5
\v 14 ያህዌ ሕዝቡን አይጥልምና ርስቱንም አይተውም፡፡
\v 15 ፍርድ ተመልሶ በጽድቅ አሠራር ላይ ይመሠረታል ልበ ቀናዎችም ሁሉ ይከተሉታል፡፡
\v 16 ክፉዎችን የሚቋቋምልኝ ማን ነው? ከክፉ አድራጊዎች የሚሟገትልንስ ማን ነው?
\s5
\v 17 ያህዌ ረዳቴ ባይሆን ኖሮ ፈጥኜ ወደ ዝምታው ዓለም በወረድሁ ነበር፡፡
\v 18 እኔ፣ «እግሬን አዳለጠኝ» ባልሁ ጊዜ ያህዌ ሆይ፣ ምሕረትህ ደግፎ ያዘኝ፡፡
\v 19 ሐዘኔ በበዛ ጊዜ፣ ማጽናናትህ ደስ አሰኘኝ፡፡
\s5
\v 20 ዓመፅን ሕጋዊ የሚያደርግ የጥፋት ዙፋን ከአንተ ጋር ሊያብር ይችላልን?
\v 21 ጻድቃንን ለማጥፋት ያሤራሉ በንጹሐን ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ ይበይናሉ፡፡
\s5
\v 22 ለእኔ ግን ያህዌ ጠንካራ ምሽግ አምላኬም መጠጊያ ዐለት ሆኖኛል፡፡
\v 23 ኃጢአታቸውን ወደ ራሳቸው ይመልሳል በገዛ ክፋታቸውም ያጠፋቸዋል፡፡ ያህዌ አምላካችን ይደመስሳቸዋል፡፡
\s5
\c 95
\p
\v 1 ኑ፣ ያህዌን እናመስግን የመዳን ዐለታችን ለሆነው ለእርሱ በደስታ እንዘምር፡፡
\v 2 ወደ ፊቱ በምስጋና እንግባ በዝማሬም እናወድሰው፡፡
\v 3 ያህዌ ታላቅ አምላክ ነውና ከአማልክትም ሁሉ የበለጠ ታላቅ ንጉሥ ነው፡፡
\s5
\v 4 የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው፡፡
\v 5 ባሕር የእርሱ ነው፤ እርሱ ሠራው እጆቹም የብሱን አበጁ፡፡
\s5
\v 6 ኑ እናምልከው እንስገድለትም በፈጠረን በያህዌ ፊት እንንበርከክ
\v 7 እርሱ አምላካችን ነውና እኛ የመሰማሪያው ሕዝብ የእጁም በጐች ነን፡፡ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ
\s5
\v 8 «በምድረ በዳ በነበራችሁበት ቀን በማሳህ፣ በመረባም እንዳደረጋችሁት ልባችሁን አታደንድኑት፡፡
\v 9 ሥራዬን ቢያዩም አባቶቻችሁ ፈተኑኝ፤ ተፈታተኑኝም፤
\s5
\v 10 ያንን ትውልድ አርባ ዓመት ሙሉ ተቆጣሁት፣ እኔም፣ «ልቡ የሸፈተ ሕዝብ ነው፤ መንገዴንም አላወቁም» አልሁ፡፡
\v 11 ስለዚህ፣ «በፍጹም ወደ እኔ ዕረፍቴ ቦታ አይገቡም» ብዬ በቁጣየ ማልሁ፡፡
\s5
\c 96
\p
\v 1 ለያህዌ አዲስ መዝሙር ዘምሩ ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ
\v 2 ለያህዌ ዘምሩ፤ ስሙንም ባርኩ ማዳኑንንም ዕለት በዕለት ተናገሩ፡፡
\s5
\v 3 ክብሩን በሕዝቦች መካከል ድንቅ ሥራውንም በሕዝቦች መካከል ተናገሩ፡፡
\v 4 እግዚአብሔር ታላቅ ነው፣ ከፍ ያለ ምስጋናም ይገባዋል ከአማልክት ሁሉ በላይ ሊፈራ ይገባዋል፡፡
\s5
\v 5 የሕዝቦች አማልክት ሁሉ ጣዖቶች ናቸው ያህዌ ግን ሰማያትን ሠራ፡፡
\v 6 ክብርና ግርማ በፊቱ ናቸው ብርታትና ውበትም መቅደሱ ውስጥ አሉ፡፡
\s5
\v 7 የሕዝብ ወገኖች ሁሉ ለያህዌ ምስጋና ስጡ ክብርንና ብርታትን ለያህዌ ስጡ፡፡
\v 8 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለያህዌ ስጡ ስጦታ ይዛችሁ ወደ አደባባዩ ግቡ፡፡
\s5
\v 9 ክብርን በተሞላ ቅድስና ለያህዌ ስገዱ ምድር ሁሉ በፊቱ፤ ተንቀጥቀጡ፡፡
\v 10 በሕዝቦች መካከል፣ «እግዚአብሔር ነገሠ» በሉ፤ ምድር በጽኑ ስለ ተመሠረተች አትናወጥም፡፡ እርሱ ሕዝቦች ላይ በጽድቅ ይፈርዳል፡፡
\s5
\v 11 ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሴት ታድርግ፡፡ ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ እልል ይበል፡፡
\v 12 መስክና በላዩ ያለው ሁሉ ይፈንጥዝ ያን ጊዜ የዱር ዛፎች ሁሉ በደስታ ይዘምራሉ፡፡
\v 13 እርሱ ይመጣልና በያህዌ ፊት ይዘምራሉ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል በዓለም ላይ በጽድቅ፣ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል፡፡
\s5
\c 97
\p
\v 1 እግዚአብሔር ነገሠ ምድር ደስ ይበላት፤ በሩቅ ያሉ የባሕር ጠረፎች ሐሤት ያድርጉ፡፡
\v 2 ደመናና ጥቅጥቅ ያለ ጭጋግ በዙሪያው አለ ጻድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው፡፡
\s5
\v 3 እሳት በፊቱ ይሄዳል በዙሪያው ያሉ ባላንጣዎቹን ይፈጃል፡፡
\v 4 መብረቁ ዓለምን አበራ ምድር ዐይታ ተንቀጠቀጠች፡፡
\v 5 ተራሮች ያህዌ ፊት የምድር ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ
\s5
\v 6 ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ ሕዝቦችም ሁሉ ክብሩን ያያሉ፡፡
\v 7 የተቀረጹ ምስሎች የሚያመልኩ፣ በጣዖቶች የሚመኩ ሁሉ ይፈሩ እናንት አማልክት ሁላችሁ ለእርሱ ስገዱ
\v 8 ያህዌ ሆይ፣ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት የይሁዳም ከተሞች ሐሤት አደረጉ፡፡
\s5
\v 9 ያህዌ ሆይ፣ አንተ በምድር ሁሉ ልዑል ነህና ከአማልክት ሁሉ ይልቅ እጅግ ከፍ ያልህ ነህ፡፡
\v 10 ያህዌን የምትወዱ ክፋትን ጥሉ! እርሱ የቅዱሳኑን ሕይወት ይጠብቃል ከክፉዎችም እጅ ይታደጋቸዋል፡፡
\v 11 ብርሃን ለጻድቃን ሐሤትም ለልበ ቅኖች ወጣ፡፡
\s5
\v 12 እናንተ ጻድቃን በያህዌ ደስ ይበላችሁ ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ፡፡
\s5
\c 98
\p
\v 1 እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጐአልና ለያህዌ አዲስ መዝሙር አቅርቡ ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም ድል ሰጥተውታል፡፡
\v 2 ያህዌ ማዳኑን አሳወቀ ጽድቁንም ለሕዝቦች ሁሉ በግልጽ አሳየ፡፡
\s5
\v 3 ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን ታማኝነቱንም አሰበ፡፡ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ድል አድራጊነት አዩ፡፡
\v 4 ምድር ሁሉ ለያህዌ እልል በሉ ውዳሴ አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፡፡
\s5
\v 5 በገና በመደርደርና በመዝሙር ለያህዌ ምስጋና አቅርቡ፡፡
\v 6 በመለከትና በእምቢልታ ድምፅ በንጉሡ በያህዌ ፊት እልል በሉ፡፡
\s5
\v 7 ባሕርና በውስጡ ያለው ሁሉ ዓለምና የሚኖሩባትም ሁሉ ያስገምግሙ
\v 8 ወንዞች ያጨብጭቡ ተራሮችም በደስታ እልል ይበሉ፡፡
\v 9 ያህዌ በምድር ላይ ለመፍረድ ይመጣል በዓለም ላይ በጽድቅ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል፡፡
\s5
\c 99
\p
\v 1 ያህዌ ነገሠ፤ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ በኪሩቤል ላይ በዙፋኑ ተቀምጧል፤ ምድር ትናወጥ፡፡
\v 2 ያህዌ በጽዮን ታላቅ ነው ከሕዝቦችም ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፡፡
\v 3 ታላቁንና አስፈሪውን ስምህን ይወድሱ እርሱ ቅዱስ ነው፡፡
\s5
\v 4 ፍትሕ የምትወድ ኃያል ንጉሥ ሆይ ጽድቅንና ፍትሕን ለያዕቆብ አደረግህ፡፡
\v 5 አምላካችን ያህዌን አመስግኑት በእግሩ መርገጫ ስገዱ፡፡ እርሱ ቅዱስ ነው፡፡
\s5
\v 6 ሙሴና አሮን ካህናቱ መካከል ነበሩ ሳሙኤልም ስሙን ከጠሩት መካከል ነበረ እነርሱ ወደ ያህዌ ጸለዩ እርሱም መለሰላቸው፡፡
\v 7 በደመና ዐምድ ውስጥ ተናገራቸው እነርሱም ሥርዐቱንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠበቁ፡፡
\s5
\v 8 አምላካችን ያህዌ ሆይ፣ አንተ መለስህላቸው ይቅር ባይ አምላክ ሆንህላቸው ኃጢአታቸውን ግን ቀጣህ፡፡
\v 9 አምላካችን ያህዌን አመስግኑ አምላካችን ያህዌ ቅዱስ ነውና በቅዱስ ተራራው ሰገዱ፡፡
\s5
\c 100
\p
\v 1 ምድር ሁሉ ለያህዌ እልል በሉ
\v 2 ያህዌን በደስታ አገልግሉት፡፡ በደስታ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ
\s5
\v 3 ያህዌ አምላክ መሆኑን ዕወቁ እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የእርሱ ነን፡፡ እኛ ሕዝቡ የመሰማሪያውም በጐች ነን፡፡
\s5
\v 4 በምስጋና ወደ ደጆቹ፣ በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፡፡ አመስግኑት ስሙንም ባርኩ፤
\v 5 ያህዌ ቸር ነው፤ ምሕረቱም ለዘላለም ነው፤ ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው፡፡
\s5
\c 101
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ስለ ታማኝነትህና ስለ ትክክለኛ ፍርድህ ምስጋና እዘምራለሁ፡፡
\s5
\v 2 ነቀፋ በሌለበት መንገድ እሄዳለሁ አንተ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው? በቤቴ ውስጥ ያለ ነቀፋ እመላለሳለሁ፡፡
\v 3 በዐይኖቼ ፊት በደል አላኖርም የክፉዎችን ሥራ እጠላለሁ ከቶም አልተባበራቸውም፡፡
\s5
\v 4 ጠማማ ሰዎች ከእኔ ይርቃሉ ከክፋት ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም፡፡
\v 5 ባልንጀራውን በስውር የሚያማውን አጠፋለሁ፡፡ ትዕቢተኛ ዐይንና እብሪተኛ ልብ ያለውን ሰው አልታገሠውም፡፡
\v 6 ከእኔ ጋር እንዲኖሩ፣ ዐይኖቼ በምድሪቱ ያሉ ታማኞች ላይ ናቸው በንጹሕና የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል፡፡
\s5
\v 7 አታላይ ሰው ቤቴ ውስጥ አይኖርም ሐሰተኛም በዐይኖቼ ፊት አይከብርም፡፡
\v 8 በምድሪቱ ያሉትን ክፉ አድራጊዎች በየማለዳው አጠፋቸዋለሁ፤ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ከያህዌ ከተማ አስወግዳቸዋለሁ፡፡
\s5
\c 102
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ ጸሎቴን ሰማ ጩኸቴንም አድምጥ፡፡
\v 2 በመከራዬ ጊዜ ፊትህን ከእኔ አትሰውር ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል ወደ አንተ ስጣራ ፈጥነህ አድምጠኝ፡፡
\s5
\v 3 ዘመኔ እንደ ጢስ እየበነነ ነው ዐጥንቶቼም እንደ እሳት እየነደዱ ነው፡፡
\v 4 ልቤ ተሰብሮአል፤ እኔም እንደ ደረቀ ሣር ሆኛለሁ፡፡ እህል መብላትንም ዘንግቻለሁ፡፡
\s5
\v 5 ዘወትር ከመቃተቴ የተነሣ ዐጥንቴ ከቆዳዬ ጋር ተጣበቀ፡፡
\v 6 በምድረ በዳ እንዳለ እርኩም መሰልሁ፤ በፍርስራሽ መካከል እንዳ ጉጉት ሆንሁ፡፡
\s5
\v 7 ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤ በቤት ጣራ ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆኛለሁ
\v 8 ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይሳለቁብኛል የሚያፌዙብኝም ስሜን እንደ ርግማን ቆጥረውታል፡፡
\s5
\v 9 ዐመድ እንደ እህል ቅሜአለሁ! እንባዬም ከምጠጣው ነገር ጋር ተደባልቆአል፡፡
\v 10 ወደ ላይ አነሣኸኝ፤ ከቁጣህና ከመዓትህም የተነሣ መልሰህ ጣልኸኝ፡፡
\s5
\v 11 ዘመኖቼ ቶሎ እንደሚያልፍ ጥላ ናቸው እኔም እንደ ሣር ደረቅሁ
\v 12 አንተ ግን ያህዌ ሆይ፣ ለዘላለም ትኖራለህ ስምህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ገናና ነው፡፡
\s5
\v 13 ትነሣህ፤ ጽዮንንም ትምራታለህ ለእርሷ ርኅራኄህን የምታሳይበት ጊዜ ነው፤
\v 14 አገልጋዮችህ ድንጋዮዋን ወደዋልና ለፍርስራሾቿ ራርተዋል፡፡
\v 15 ሕዝቦች የያህዌን ስም የምድር ነገሥታትም ክብርህን ይፈራሉ፡፡
\v 16 ያህዌ ጽዮንን እንደ ገና ይሠራታልና በክብሩም ይገለጣል፡፡
\s5
\v 17 በዚያ ጊዜ እርሱ ለችግረኞች ጸሎት መልስ ይሰጣል፤ ልመናቸውንም አይንቅም፡፡
\v 18 ገና ያልተወለዱ ሰዎች እንዲያመሰግኑት ይህ ያህዌ ያደረገው ድንቅ ነገር ለሚመጣው ትውልድ ይጻፍ፡፡
\s5
\v 19 በከፍታ ካለው መቅደሱ ወደ ታች ተመልክቶአልና ያህዌ ከሰማይ ምድርን ዐይቶአል፡፡
\v 20 ይኸውም የእስረኞችን መቃተት ይሰማ ዘንድ ሞት የተፈረደባቸውን ያድን ዘንድ ነው፡፡
\s5
\v 21 ስለዚህ የያህዌ ስም በጽዮን፣ ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይነገራል፡፡
\v 22 ይህም የሚሆነው ሕዝቦችና መንግሥታት ያህዌን ለማምለክ በአንድት ሲሰበሰቡ ነው፡፡
\s5
\v 23 በሕይወቴ እኩሌታ ብርታቴን ቀጨው ዕድሜዬንም ባጭሩ አስቀረው፡፡
\v 24 እኔም፣ «አምላኬ ሆይ፣ የአንተ ዘመን ከትውልድ እስከ ትውልድ ስለሆነ በዕድሜዬ እኩሌታ አትውሰደኝ» አልሁ፡፡
\s5
\v 25 አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው፡፡
\v 26 እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ እነርሱ እንደ ልብስ ያረጃሉ እንደ መጐናጸፊያ ትለውጣቸዋለህ እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ፡፡
\v 27 አንተ ግን ያው አንተ ነህ ዘመኖችህም ፍጻሜ የላቸውም፡፡
\s5
\v 28 የአገልጋዮችህ ልጆች በሰላም ይኖራሉ ትውልዳቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል፡፡
\s5
\c 103
\p
\v 1 ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌ አመስግኚ የያህዌን ቅዱስ ስም በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ፡፡
\v 2 ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን አመሰግኚ ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፡፡
\s5
\v 3 ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር ይላል ደዌሽንም ሁሉ ይፈውሳል፡፡
\v 4 ሕይወትሽንም ከጥፋት ጉድጓድ ያድናል ምሕረትና ርኅራኄውን ያቀዳጅሻል፡፡
\v 5 ወጣትነትሽ እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ ሕይወትሽን በመልካም ነገር ያጠግባል፡፡
\s5
\v 6 ያህዌ ለተጨቆኑ ሁሉ፣ ቅን ፍርድንና ፍትሕን ይሰጣል፡፡
\v 7 መንገዱን ለሙሴ፣ ሥራውንም ለእስራኤል ልጆች አሳወቀ፡፡
\v 8 ያህዌ መሐሪና ይቅር ባይ ለቁጣ የዘገየ፣ ታማኝነቱም የበዛ ነው፡፡
\s5
\v 9 እርሱ ሁልጊዜ አይገሥጽም ለዘላለምም አይቆጣም፡፡
\v 10 እንደ ኃጢአታችን አላደረግብንም እንደ በደላችንም አልከፈለንም፡፡
\s5
\v 11 ሰማይ ከምድር ከፍ የማለቱን ያህል እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ነው፡፡
\v 12 ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ በደልና ኃጢአታችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ፡፡
\v 13 አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ ያህዌም ለሚፈሩት ይራራል፡፡
\s5
\v 14 እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና ትቢያ መሆናችንንም ይገነዘባል፡፡
\v 15 ሰው እኮ እንደ ሣር እንደሚያድግ የዱር አበባ ነው፡፡
\v 16 ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ ድራሹ ይጠፋል፤ የነበረበት ስፍራ እንኳ አይታወቅም፡፡
\s5
\v 17 የያህዌ ምሕረት ግን ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፡፡ ጽድቁም እስከ ልጅ ልጃቻቸው ዘመን በላያቸው ይሆናል፤
\v 18 ይህም ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ ትእዛዙንም በሚያከብሩት ላይ ይሆናል፡፡
\v 19 ያህዌ ዙፋኑን በሰማይ አጽንቶአል መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች፡፡
\s5
\v 20 እናንተ ለቃሉ የምትታዘዙ መላእክት ትእዛዙንም የምትፈጽሙ እናንተ ኃያላን፣ ያህዌን አመስግኑ፡፡
\v 21 አገልጋዩ የሆናችሁ፣ ፈቃዱንም የምትፈጽሙ እናንተ የሰማይ ሰራዊት ያህዌን አመስግኑ፡፡
\v 22 በግዛቱ ሁሉ የምትገኙ ፍጥረቶቹ ያህዌን አመስግኑ፤ ነፍሴ ሆይ ያህዌን አመስግኚ፡፡
\s5
\c 104
\p
\v 1 ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን አመስግኚ አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ ውበትና ግርማን ለብሰሃል፡፡
\v 2 ብርሃንን እንደ ሸማ ተጐናጽፈሃል ሰማያትን እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፡፡
\v 3 በጠፈር ላይ ካለው ውሃ በላይ ቤትህን ሠርተሃል ደመናትን ሰረገላህ አደረግህ በነፋስ ክንፎች ትሄዳለህ፡፡
\s5
\v 4 ነፋሶችን መልእክተኞቹ፣ ነበልባልንም አገልጋዮቹ አደረግ፡፡
\v 5 ምድርን መሠረት ላይ አጸና ከቶም አትናወጥም፡፡
\s5
\v 6 በጥልቁ እንደ ልብስ ሸፈንሃት ውሆችም ከተራሮች በላይ ቆሙ፡፡
\v 7 በገሠጸካቸው ጊዜ ግን ፈጥነው ሄዱ የነጐድጓድህንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ሸሹ፡፡
\s5
\v 8 በተራሮች ላይ ፈሰሱ አንተ ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ ወደ ሸለቆዎች ወረዱ፡፡
\v 9 ዳግመኛ ምድርን እንዳይሸፍኑም አልፈውም እንዳይመጡ ድንበር አበጀህላቸው፡፡
\s5
\v 10 ምንጮች በሸለቆው ውስጥ እንዲ ወንዞችም በተራሮች መካከል እንዲወርዱ አደረግህ፡፡
\v 11 የዱር እንስሳት ከዚያ ይጠጣሉ የሜዳ አህዮችም ጥማቸውን ያረካሉ፡፡
\v 12 ወንዙ ዳር ወፎች ጐጆአቸውን ይሠራሉ በቅርንጫፎቹም መካከል ይዘምራሉ፡፡
\s5
\v 13 ከላይ ከእልፍኙ ተራሮችን ያጠጣል፤ ምድርም በሥራው ፍሬ ትረካለች፡፡
\v 14 ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ ለእንስሶች ሣርን ታበቅላለህ ለሰው ልጆች ሥራ አትክልቶችን ታበቅላለህ፡፡
\v 15 ስለዚህ ልቡን ደስ የሚሰኘውን ወይን ጠጅ፣ ፊቱን የሚያበራ ዘይትና በሕይወት የሚያኖረውን እህል ያዘጋጃል፡፡
\s5
\v 16 ደግሞም የያህዌ ዛፎች፣ እርሱ የተከላቸውም የሊባኖስ ዝግባዎች በቂ ዝናብ ያገኛሉ፡፡
\v 17 በዚያ ወፎች ጐጆአቸውን ይሠራሉ ሽመላዎችም በጥዶቹ ውስጥ ማደሪያ ያገኛሉ፡፡
\v 18 ረጃጅሙ ተራራ የዋልያ ተራራ የዐለቱም ዋሻዎች የሽኮኮ መሸሸጊያ ናቸው፡፡
\s5
\v 19 ጨረቃ የወቅቶች ምልክት እንድትሆን አደረገ ፀሐይም የምትጠልቀበትን ጊዜ ታውቃለች፡፡
\v 20 ጨለማን ፈጠርህ፤ ሌሊትም ሆነ፤ በጨለማም የዱር አውሬዎች ሁሉ ይወጣሉ፡፡
\s5
\v 21 የአንበሳ ግልግሎች ምግብ ለማግኘት ይጫኸሉ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምግባቸውን ይፈልጋሉ፡፡
\v 22 ፀሐይ በወጣች ጊዜ ሸሽተው ይሄዳሉ፤ በየመኖሪያቸው ውስጥ ይተኛሉ፡፡
\s5
\v 23 ሰውም ወደ ሥራው ይሄዳል እስኪመሽም ድረስ ሲሠራ ይውላል፡፡
\v 24 ያህዌ ሆይ፣ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው! ሁሉን በጥበብ አደረግህ ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች፡፡
\s5
\v 25 እዚያ ደግሞ ሰፊና የተንጣለለ ባሕር አለ ታላላቅና ታናናሽ እንስሳት፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸውም ነፍሳት በውስጡ አሉ፡፡
\v 26 መርከቦች በላዩ ይመላለሳሉ አንተ የፈጠርኸው ሌዋታን በውስጡ ይፈነጫል፡፡
\s5
\v 27 እነዚህ ሁሉ በጊዜው ምግባቸውን እንድትሰጣቸው አንተን ተስፋ ያደርጋሉ፡፡
\v 28 በሰጠሃቸው ጊዜ አንድ ላይ ይከማቻሉ፣ እጅህንም ስትዘረጋ በመልካም ነገር ይጠግባሉ፡፡
\s5
\v 29 ፊትህን ስትሰውር፣ በጣም ይደነግጣሉ እስትንፋሳቸውን ስትወስድ ይሞታሉ፤ ወደ አፈርም ይመለሳሉ፡፡
\v 30 መንፈስህ ስትልክ እነርሱ ይፈጠራሉ የምድርንም ገጽ ታድሳለህ፡፡
\s5
\v 31 ለዘላለም ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ያህዌ በፍጥረቱ ደስ ይበለው፡፡
\v 32 ከላይ ምድርን ሲመለከት ትንቀጠቀጣለች ተራሮችን ሲዳስሳቸው ይጨሳሉ
\s5
\v 33 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ለያህዌ እዘምራለሁ በሕይወትም እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ፡፡
\v 34 ደስታዬ በእርሱ ስለሆነ የልቤ ሐሳብ እርሱን ደስ ያሰኘው፡፡
\s5
\v 35 ኅጥአን ከምድር ይጥፉ ዐመፀኞች ከእንግዲህ አይኑሩ፡፡ ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን አመስግኚ፡፡ ያህዌ ይመስገን፡፡
\s5
\c 105
\p
\v 1 ያህዌን አመስግኑ፣ ስሙንም ጥሩ ሥራውንም በሕዝቦች መካከል ግለጡ፡፡
\v 2 ለእርሱ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ ድንቅ ሥራዎቹን ሁሉ ተናገሩ፡፡
\v 3 በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ ያህዌን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው፡፡
\s5
\v 4 ያህዌንና ብርታቱን ፈልጉ ፊቱንም ዘወትር ፈልጉ፡፡
\v 5 ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች ተአምራቱንና ከአፉ የወጣውን ፍርድ ፈልጉ፡፡
\v 6 እናንት የአገልጋዩ የአብርሃም ዘሮች እርሱ የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ አስታውሱ፡፡
\s5
\v 7 እርሱ አምላካችን ያህዌ ነው ፍርዱም በምድር ሁሉ ላይ ነው፡፡
\v 8 ኪዳኑን ለዘላለም፣ ያዘዘውንም ቃል እስከ ሺህ ትውልድ ዘመን ያስታውሳል፡፡
\s5
\v 9 ከአብርሃም ጋር ያደረገውን ኪዳን ለይስሐቅም በመሐላ የሰጠውን ተስፋ አይረሳም፡፡
\v 10 ይህን ለያዕቆብ ሥርዐት ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አድርጐ አጸናው፡፡
\v 11 እንዲህም አለ፣ «የርስትህ ድርሻ እንዲሆን የከነዓንን ምድር እሰጥሃለሁ፡፡
\s5
\v 12 ይህን ያለው እነርሱ በቁጥር አነስተኞች፣ እጅግ ጥቂትና ባይተዋሮች ሳሉ፣
\v 13 ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ሲንከራተቱ፣ ከአንዱ መንግሥት ወደ ሌላው መንግሥት ሲቅበዘበዙ ነበር፡፡
\s5
\v 14 ማንም እንዲጨቁናቸው አልፈቀደም ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ፡፡
\v 15 «የቀባኋቸውን አትንኩ፤ ነቢያቶቼንም አትጉዱ» አለ፡፡
\s5
\v 16 በምድር ላይ ችጋርን ጠራ የምግብንም አቅርቦት ሁሉ አቋረጠ፡፡
\v 17 ከእነርሱ አስቀድሞ በባርነት የተሸጠው ዮሴፍን ላከ፡፡
\s5
\v 18 እግሮቹ በእግር ብረት ተላላጡ አንገቱም ላይ የብረት ማነቆ ገባ፡፡
\v 19 የተናገረው እስኪፈጸም ድረስ የያህዌ ቃል ፈተነው፡፡
\s5
\v 20 እርሱን እንዲፈቱ ንጉሡ አገልጋዮቹን ላከ፤ የሕዝቦችም ገዢ ነጻ አወጣው፡፡
\v 21 የቤቱ ጌታ የንብረቱም ሁሉ አስተዳዳሪ አደረገው፡፡
\v 22 በንጉሡ ባለ ሥልጣኖች ላይ አዛዥ ሆነ ለንጉሡም አማካሪዎች ጥበብን እንዲያስተምር ሥልጣን ተሰጠው፡፡
\v 23 ከዚያም እስራኤል ወደ ግብፅ ሄደ እስከ ጊዜው ድረስ ያዕቆብ በካም ምድር ተቀመጠ፡፡
\s5
\v 24 ያህዌ ሕዝቡን እጅግ አበዛ ከጠላቶቻቸውም ይልቅ ብርቱ አደረጋቸው፡፡
\v 25 ሕዝቡን እንዲጠሉ ባርያዎቹንም እንዲበድሉ ልባቸውን አስጨከነ፡፡
\v 26 ባርያውን ሙሴን እርሱ የመረጠውንም አሮንን ላከ፡፡
\v 27 በግብፃውያን መካከል ምልክቶችን በካም ምድርም ድንቆችን አደረጉ፡፡
\s5
\v 28 ጨለማን ልኮ ምድርን ጽልመት አለበሳት ይሁን እንጂ ትእዛዞቹን አልፈጸሙም፡፡
\v 29 ውሃቸውን ወደ ደም ለወጠ ዓሣዎቻቸውንም ፈጀ፡፡
\v 30 የነገሥታት እልፍኝ እንኳ ሳይቀር ምድራቸው በእንቁራሪት ተሸፈነች፡፡
\s5
\v 31 እርሱ ሲናገር ተናካሽ ዝንቦችና ተናዳፊ ትንኞች በአገራቸው ተርመሰመሱ፡፡
\v 32 በአገራቸው ላይ የበረዶ ድንጋይና መብረቅ አወረደ፡፡
\v 33 ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ ሌሎች ዛፎቻቸውንም ሰባበረ፡፡
\s5
\v 34 እርሱ ሲናገር አንበጣ መጣ ስፍር ቁጠር የሌለውም ኩብኩባ ከተፍ አለ፡፡
\v 35 አንበጣ የምድሪቱን ዕፅዋት ሁሉ በላ እህላቸውንም ሁሉ ፈጀ፡፡
\v 36 ደግሞም የእያንዳንዱን ግብፃዊ በኩር ሁሉ የኃይላቸውንም ሁሉ በኩራት መታ፡፡
\s5
\v 37 እስራኤላውያንን ከወርቅና ከብር ጋር ከዚያ መርቶ አወጣ፤ ከነገዶቻቸው አንዱ እንኳ አልተደናቀፈም፡፡
\v 38 እጅግ ፈርተዋቸው ነበርና እስራኤላውያን አገር ለቀው ሲወጡ ግብፅ ደስ አላት፡፡
\v 39 በሚሄዱበት ጊዜ በደመና ጋረዳቸው እሳትም በሌሊት አበራላቸው፡፡
\s5
\v 40 ምግብ እንዲሰጣቸው በለመኑት ጊዜ ድርጭት አመጣላቸው የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው፡፡
\v 41 ዐለቱን ሰነጠቀ፤ ውሃም ተንዶለዶለ
\v 42 ለባርያው ለአብርሃም የሰጠውን ቅዱስ የተስፋ ቃል አስታውሶአልና
\s5
\v 43 ሕዝቡን በደስታ፣ ምርጦቹንም በእልልታ መራቸው፡፡
\v 44 የሕዝቦችን ምድር ሰጣቸው የእነርሱንም ሀብት ወረሱ፡፡
\v 45 ይህም ሥርዐቱን ይጠብቁ ዘንድ ሕጉንም ይፈጽሙ ዘንድ ነው፡፡ ያህዌ ይመስገን
\s5
\c 106
\p
\v 1 ያህዌን አመስግኑ ቸር ነውና ያህዌን አመስግኑ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፡፡
\v 2 የያህዌን ብርቱ ሥራ ማን ሊናገር ይችላል? ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ተናግሮ ይጨርሳል?
\s5
\v 3 ዘወትር መልካሙንና ትክክል የሆነውን የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው፡፡
\v 4 ያህዌ ሆይ፣ ለሕዝብህ ሞገስ ስታደርግ አስበኝ፤ በምታድናቸውም ጊዜ ርዳኝ፡፡
\v 5 ይኸውም፣ አንተ የመረጥሃቸውን መበልጸግ እንዳይ፣ በሕዝብህ ደስ መሰኘት እኔንም ደስ እንዲለኝ በርስትህም ክብር መመካት እንድችል ነው፡፡
\s5
\v 6 እኛም እንደ አባቶቻችን ኃጢአት ሠራን፣ በደልን፣ ክፉም አደረግን፡፡
\v 7 አባቶቻችን በግብፅ ምድር ያደረግኸውን አላስተዋሉም፡፡ ብዙዎቹን የቸርነት ሥራዎቹን አላስተዋሉም፡፡ በባሕሩ አጠገብ፣ ቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁብህ፡፡
\s5
\v 8 እርሱ ግን የኃይሉን ታላቅነት ለማሳየት ስለ ስሙ አዳናቸው፡፡
\v 9 ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው፡፡
\s5
\v 10 ከባላጋራቸው እጅ አዳናቸው ከጠላትም እጅ ታደጋቸው፡፡
\v 11 ባላጋራዎቻቸውን ውሃ ዋጣቸው ከእነርሱ አንድ አልተረፈም፡፡
\v 12 ከዚያ በኋላ የተስፋ ቃሉን አመኑ በዝማሬም አመሰገኑት፡፡
\s5
\v 13 ሆኖም፣ ወዲያውኑ እርሱ ያደረገውን ረሱ በምክሩም ለመሄድ አልታገሡም፡፡
\v 14 በምድረ በዳ ብዙ ነገር ተመኙ፤ በበረሐም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት፡፡
\v 15 እርሱም የለመኑትን ሰጣቸው ነገር ግን የሚያኮሰምን ደዌ ሰደደባቸው፡፡
\s5
\v 16 ሰፈር ውስጥ በሙሴ ላይ የተቀደሰው የያህዌ ካህን ላይ ቀኑ፡፡
\v 17 ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች የአቤሮንንም ሰዎች ሰለቀጠች፡፡
\v 18 በመካከላቸው እሳት ነድዶ ነበልባልም ክፉዎችን ፈጅቶ አስወገደ፡፡
\s5
\v 19 በኮሬብ ጥጃ ሠሩ ቀልጦ ለተሠራ ምስል ሰገዱ፡፡
\v 20 ክብራቸውን ሣር በሚበላ የበሬ ምስል ለወጡ፡፡
\v 21 በግብፅ ታላላቅ ነገሮች ያደረገውን ያዳናቸውን እግዚአብሔርን ረሱ፡፡
\s5
\v 22 እርሱ በካም ምድር ድንቅ ሥራ በቀይ ባሕርም አስደናቂ ነገር አደረገ፡፡
\v 23 ቁጣውን እንዲመልስ እርሱ የመረጠው ሙሴ በመካከል ባይገባ ኖሮ እነርሱን ለማጥፋት ወስኖ ነበር፡፡
\s5
\v 24 መልካሚቱን ምድር ናቁ በተስፋ ቃሉም አላመኑም፡፡
\v 25 ድንኳናቸው ውስጥ አጉረመረሙ ለያህዌም አልታዘዙም፡፡
\s5
\v 26 ስለዚህ በምድረ በዳ እንደሚያጠፋቸው እጁን አንሥቶ ማለ፡፡
\v 27 ዘሮቻቸውን በአሕዛብ መካከል ለመጣል እነርሱንም ወደ ተለያየ አገሮች እንደሚበትናቸው ማለ፡፡
\s5
\v 28 ብዔል ፌጐርን አመለኩ ለሙታን የተሠዋውን በሉ፡፡
\v 29 በተግባራቸውም እግዚአብሔርን አስቆጡት፤ በዚህም ምክንያት በመካከላቸው መቅሠፍት ተነሣ፡፡
\s5
\v 30 ፊንሐስ ተነሥቶ ጣልቃ ገባ፤ መቅሠፍቱም ተገታ፡፡
\v 31 ይህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ለዘላለም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት፡፡
\s5
\v 32 ደግሞም በመሪባ ውሃ አጠገብ ያህዌን አስቆጡት ሙሴም በእነርሱም ምክንያት ችግር ላይ ወደቀ፡፡
\v 33 ሙሴን ስላስመረሩት ራሱን ባለ መቆጣጠር ተናገረ፡፡
\v 34 እግዚአብሔር ባዘዛቸው መሠረት ሕዝቦችን ከማጥፋት ወደ ኃላ አሉ፡፡
\v 35 እንዲያውም ከእነርሱ ጋር በመደባለቅ የእነርሱን መንገድ ተማሩ፡፡
\v 36 ጣዖቶቻቸውን አመለኩ፤ ይህም ወጥመድ ሆነባቸው፡፡
\s5
\v 37 ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንት ሠዉ፡፡
\v 38 የወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ደም ለከነዓን ጣዖቶች መሥዋዕት በማቅረባቸው ንጹሕ ደም አፈሰሱ ምድሪቱንም አረከሱ፡፡
\v 39 እነርሱ በሥራቸው ረከሱ በድርጊታቸውም አመንዝሮች ሆኑ፡፡
\s5
\v 40 ስለዚህ ያህዌ በሕዝቡ ላይ እጅግ ተቆጣ ርስቱንም ተጸየፈ፡፡
\v 41 ለአሕዛብ አሳልፎ ሰጣቸው ጠላቶቻቸውም በላያቸው ገዢዎች ሆኑባቸው፡፡
\s5
\v 42 ጠላቶቻቸው ጨቆኑአቸው በሥልጣናቸውም ሥር አደረጓቸው፡፡
\v 43 እርሱ ብዙ ጊዜ ታደጋቸው እነርሱ ግን ዐመፅ ማድረጋቸውን ገፉበት፡፡ በገዛ ኃጢአታቸው ተዋረዱ፡፡
\s5
\v 44 ይህም ሆኖ እንዲረዳቸው ወደ እርሱ ሲጮኹ ጩኸታቸውን ሰማ ጭንቀታቸውንም ተመለከተ፡፡
\v 45 ለእነርሱ ሲል ቃል ኪዳኑን አሰበ እንደ ምሕረቱም ብዛት ከቁጣው ተመለሰ፡፡
\v 46 የሚጨቁኑአቸው ሁሉ እንዲራሩላቸው አደረገ፡፡
\s5
\v 47 አምላካችን ያህዌ ሆይ፣ አድነን፤ ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣ አንተን በመወደስ እንድንከብር ከሕዝቦች መካከል ሰብስበህ አምጣን፡፡
\v 48 የእስራኤል አምላክ ያህዌ ከዘላለም እስከ ዘለላም ይባረክ፡፡ ሕዝብም ሁሉ አሜን ይበል፡፡ ያህዌ ይባረክ፡፡
\s5
\c 107
\p
\v 1 ቸር ነውና ምሕረቱም ለዘላለም ነውና ያህዌን አመስግኑ፡፡
\v 2 ያህዌ የተቤዣቸው ከጠላትም እጅ የታደጋቸው ይናገሩ፡፡
\v 3 ለባዕድ ምድር፣ ከምሥራቅና ከምዕራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ ሰበሰባቸው፡፡
\s5
\v 4 በበረሐ መንገድ ጠፍቶአቸው በምድረ በዳ ተንከራተቱ የሚኖሩበትም ከተማ አላገኙም፡፡
\v 5 ተራቡ፤ ተጠሙ ከድካም የተነሣ ዛሉ፡፡
\v 6 በተጨነቁ ጊዜ ወደ ያህዌ ጮኹ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው፡፡
\v 7 ወደሚኖሩበት ከተማ በቀና መንገድ መራቸው፡፡
\s5
\v 8 ለሰው ልጆች ስላደረገው ድንቅ ነገርና ስለዘላለማዊ ፍቅሩ ሕዝቡ ያህዌን ያመስግኑ፡፡
\v 9 እርሱ የተጠማችውን ነፍስ አርክቶአልና የተራበችውን ነፍስ በመልካም ነገር አጥግቦአል፡፡
\v 10 አንዳንዶች በሰንሰለት ታስረው ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡
\s5
\v 11 ይህም የሆነው በእግዚአብሔር ቃል በማመፃቸው የልዑልንም ምክር በማቃለላቸው ነበር፡፡
\v 12 በከባድ ሥራ ልባቸውን አዛለ ተዘለፈለፉ፤ የሚረዳቸውም አላገኙም፡፡
\v 13 በተጨነቁ ጊዜ ወደ ያህዌ ጮኹ፤ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው፡፡
\s5
\v 14 ከነበሩበት ድቅድቅ ጨለማ አወጣቸው የታሰሩበትንም ሰንሰለት ሰባበረ፡፡
\v 15 ለሰው ልጆች ስላደረገው ድንቅ ነገርና ስለ ዘላለማዊ ፍቅሩ ሕዝቡ ያህዌን ያመስግኑ፡፡
\v 16 እርሱ የናሱን በሮች ሰብሮአልና የብረቱንም መወርወሪያ ቆርጦአል፡፡
\s5
\v 17 አንዳንዶች የዐመፃን መንገድ በመከተላቸው ቂሎች ሆኑ ከበደላቸው የተነሣ ችግር ውስጥ ወደቁ፡፡
\v 18 ምግብ የመብላት ፍላጐት አጡ፤ ወደ ሞት በሮችም ተቃረቡ፡፡
\v 19 በተጨነቁ ጊዜ ወደ ያህዌ ጮኹ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው፡፡
\s5
\v 20 ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፡፡ ከመቃብር አፋፍ መለሳቸው፡፡
\v 21 ለሰው ልጆች ስላደረገው ድንቅ ነገርና ስለ ዘላለማዊ ፍቅሩ ሕዝቡ ያህዌን ያመስግኑ፡፡
\v 22 የምስጋና መሥዋዕት ያቅርቡለት በዝማሬም ሥራውን ያውጁ፡፡
\s5
\v 23 አንዳንዶች በመርከብ እየተጓዙ ንግዳቸውን ያካሄዱ ነበር፡፡
\v 24 እነርሱ የያህዌን ሥራ አዩ ድንቅ አድራጐቱንም በጥልቅ ውስጥ ተመለከቱ፡፡
\s5
\v 25 ትእዛዝ በሰጠ ጊዜ ባሕሩን የሚያናውጥ ዐውሎ ነፋስ ነፈሰ፡፡
\v 26 ወደ ሰማይ ወጡ፤ ወደ ጥልቅም ወረዱ ከመከራቸው የተነሣ ልባቸው ቀለጠ፡፡
\v 27 እንደ ሰካራም ዞሮባቸው ወዲያ ወዲህ ተንገዳገዱ፤ መላው ጠፍቶባቸው የሚያደርጉትን አጡ፡፡
\s5
\v 28 በመከራቸው ጊዜ ወደ ያህዌ ጮኹ፤ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው፡፡
\v 29 ዐውሎ ነፋሱን ጸጥ አደረገ ሞገዱም ረጭ አለ፡፡
\v 30 ባሕሩ ጸጥ በማለቱ ደስ አላቸው ወዳሰቡትም ወደብ አደረሳቸው፡፡
\s5
\v 31 ለሰው ልጆች ስላደረገው ድንቅ ነገር ስለ ዘላለማዊ ፍቅሩ ሕዝቡ ያህዌን ያመስግኑ፡፡
\v 32 በሕዝቦች ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያደርጉት በሽማግሌዎችም ሸንጐ ያመስግኑት፡፡
\s5
\v 33 ወንዞችን ወደ ምድረ በዳ የውሃ ምንጮችንም ወደ ደረቅ ምድር ለወጠ፡፡
\v 34 ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ ፍሬያማዋን መሬት ደረቅ ምድር አደረገ፡፡
\v 35 ምድረ በዳውን ወደ ኩሬ ደረቁንም ምድር ወደ ውሃ ምንጭ ቀየረ፡፡
\s5
\v 36 የተራቡትን በዚያ አኖረ የሚኖሩበትንም ከተማ ሠሩ፡፡
\v 37 በእርሻዎች እህል ዘሩ ወይንን ተከሉ፤ ብዙ መከርም ሰበሰቡ፡፡
\v 38 ይባርካቸዋል፤ እነርሱም እጅግ ይበዛሉ የከብቶቻቸውም ብዛት እንዲያንስ አያደርግም፡፡
\s5
\v 39 በጭንቅ፣ በመከራና በሐዘን፣ ቁጥራቸው አንሶ ተዋርደው ነበር፤ በመኳንንቱም ላይ መናቅን አወረደባቸው
\v 40 መውጪያ መግቢያው በማይታወቅ በረሐ ውስጥም አንከራተታቸው፡፡
\s5
\v 41 ሆኖም፣ ችግረኞችን ከስቃይ አወጣቸው ለቤተ ሰቡም እንደ በግ መንጋ ተጠነቀቀ፡፡
\v 42 ቅኖች ይህን ዐይተው ደስ ይላቸዋል ክፋትም አፏን ትዘጋለች፡፡
\v 43 አስተዋይ የሆነ ሰው ይህን ልብ ይበል፤ እርሱም የያህዌን ምሕረት ያስተውል፡፡
\s5
\c 108
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ ልቤ ጽኑ ነው፡፡ እዘምራለሁ፤ በፍጹም ልቤም እዘምራለሁ፡፡
\v 2 በገናና መሰንቆም ተነሡ፤ እኔም ማልጄ እነሣለሁ፡፡
\s5
\v 3 ያህዌ ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ በመንግሥታት መካከል የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ
\v 4 ምሕረትህ ከሰማያት በላይ ታላቅ ናትና ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ይደርሳል፡፡
\s5
\v 5 አምላክ ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል ክብርህም በምድር ሁሉ ይንሰራፋ፡፡
\v 6 የምትወደው ሕዝብህ ይድን ዘንድ በቀኝ እጅህ ታደግ መልሰልኝም፡፡
\s5
\v 7 እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ አለ፤ ደስ እያለኝ ሴኬምን እከፍላለሁ የሱከትንም ሸለቆ እለካለሁ፡፡
\v 8 ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራስ ቁሬ፣ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው፡፡
\s5
\v 9 ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው በኤዶም ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤ በፍልስጥኤም ላይ በድል አድራጊነት እፎክራለሁ፡፡
\v 10 ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል? ወደ ኤዶምስ ማን ያደርሰኛል?
\s5
\v 11 እግዚአብሔር ሆይ፣ ያጣልኸን አንተ አይደለህምን? ከሰራዊታችንም ጋር ወደ ጦርነት አልወጣህም፡፡
\v 12 አሁንም የሰው ማዳን ከንቱ ነውና በጠላታችን ላይ ድል አቀዳጀን፡፡
\v 13 በእግዚአብሔር ረድኤት ድል እናደርጋለን ጠላቶቻችንንም ከእግሩ በታች የሚረግጥ እርሱ ነው፡፡
\s5
\c 109
\p
\v 1 የማመሰግንህ አምላክ ሆይ፣ ዝም አትበለኝ
\v 2 ክፉዎችና አታላዮች አጥቅተውኛልና በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ፡፡
\v 3 በጥላቻ ዙሪያዬን ከበቡኝ ያለ ምክንያትም በድለውኛል፡፡
\s5
\v 4 ስወዳቸው ይወነጅሉኛል፤ እኔ ግን ለእነርሱ እጸልያለሁ፡፡
\v 5 በመልካም ፈንታ ክፋትን በወደድኃቸው ፈንታ ጥላቻን ይመልሱልኛል፡፡
\s5
\v 6 በእንዲህ ያለው ሰው፣ ክፉ ሰው በላዩ ሹም ከሳሽም በቀኙ ይቁም፡፡
\v 7 በተሟገተ ጊዜ ተረትቶ ይግባ ጸሎቱ እንኳ እንደ ኃጢአት ይቆጠርበት፡፡
\s5
\v 8 ዕድሜው ይጠር ሹመቱን ሌላው ይውሰደው፡፡
\v 9 ልጆቹ ድኻ አደጐች ይሁኑ ሚስቱም መበለት ትሁን፡፡
\v 10 ልጆቹ ይንከራተቱ፤ ለማኞችም ይሁኑ ከፈረሰው ቤታቸው ይሰደዱ፡፡
\s5
\v 11 ንብረቱ ሁሉ በዕዳ ይያዝበት ለፍቶ ያገኘውን ጥሪት ባዕዳን ሰዎች ይውሰዱበት፡፡
\v 12 ማንም ሰው ደግ አይሁንለት ለድኻ አደግ ልጆቹ የሚራራላቸው አይገኝ፡፡
\v 13 ዘሩ ተለይቶ ይጥፋ ስማቸውም በሚቀጥለው ትውልድ ይደምሰስ፡፡
\s5
\v 14 የአባቶቹ ኃጢአት በያህዌ ፊት ይታሰብ የእናቱም ኃጢአት አይደምሰስ፡፡
\v 15 በደላቸው ሁልጊዜ በያህዌ ፊት ይሁን የእነርሱ መታሰቢያ ግን ጨርሶ ይጥፋ፡፡
\v 16 ይህ ሰው ምሕረት ከማድረግ ይልቅ፣ ችግረኛውንና ምስኪኑን ልቡም የቆሰለውን እስከ ሞት አሳድዶአልና ያህዌ ይህን ያደርግበት
\s5
\v 17 መርገምን ወደደ፤ ወደ እርሱም መጣች መባረክ አልወደደም በረከት ከእርሱ ይራቅ፡፡
\v 18 መርገምን እንደ ልብስ ለበሳት፤ ስለዚህ መርገም እንደ ውሃ ወደ ውስጥ ሰውነቱ፣ እንደ ዘይትም ወደ አጥንቱ ዘለቀች፡፡
\s5
\v 19 ገላውን እንደሚሸፍንበት ልብስ፣ ዘወትር እንደሚታጠቀውም መቀነት ትሁነው፡፡
\v 20 ለሚወነጅሉኝ ሰዎች፣ እኔ ላይ ክፉ ለሚናገሩ ያህዌ የሚከፍለው ይኸው ይሁን፡፡
\s5
\v 21 አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ ስለ ስምህ ስትል እኔን በበጐ ተመልከተኝ፡፡
\v 22 እኔ ድኽና ችግረኛ ነኝ ልቤም በውስጤ ቆስሎአል፡፡
\v 23 እንደ ምሽት ጥላ ላልፍ ተቃርቤአለሁ እንደ አንበጣም ረግፌአለሁ፡፡
\s5
\v 24 በጾም ምንያት ጉልበቴ ደከመ ሰውነቴም ከስቶ ዐመድ መሰለ፡፡
\v 25 ለጠላቶቼ መሣለቂያ ሆንሁላቸው ሲያዩኝም ራሳቸውን ይነቀንቁብኛል፡፡
\s5
\v 26 አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ ርዳኝ ስለ ታማኝነትህም አድነኝ፡፡
\v 27 ያህዌ ሆይ፣ እጅህ ይህን እንዳደረገች አንተም ይህን እንደ ፈጸምህ ይወቁ፡፡
\s5
\v 28 እነርሱ ቢራገሙ እንኳ አንተ ግን ባርከኝ እኔን ሲያጠቁኝ ይዋረዱ ባርያህ ግን ሐሤት ያደርጋል፡፡
\v 29 ባላንጣዎቼ ውርደትን እንደ ልብስ ይልበሱ እፍረትንም እንደ ሸማ ይጐናጸፉ፡፡
\s5
\v 30 በአንደበቴ ያህዌን እጅግ አመሰግለሁ በጉባኤም መካከል እባርከዋለሁ፡፡
\v 31 በእርሱ ላይ ከሚፈርዱ ለማዳን እርሱ በችግረኛው ቀኝ ይቆማልና፡፡
\s5
\c 110
\p
\v 1 ያህዌ ጌታዬን፣ «ጠላቶችህን ለእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ» አለው፡፡
\s5
\v 2 ያህዌ ብርቱ በትርህን ከጽዮን ወደ ውጭ ይሰዳል አንተም በጠላቶችህ መካከል ትገዛለህ፡፡
\v 3 በኃይልህ ቀን ተከታዮችህ የተቀደሰ ልብስ ተጐናጽፈው በፈቃዳቸው ይከተሉሃል፡፡ ከንጋት ማሕፀን ጐልማሳነትህ እንደ ጠል ይወጣል፡፡
\s5
\v 4 «እንደ መልከጼዴቅ ሥርዐት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ» ብሎ ያህዌ ምሎአል፤ እርሱም ሐሳቡን አይለውጥም፡፡
\s5
\v 5 ጌታ በቀኝህ ነው በቁጣው ቀን ነገሥታትን ይገድላል፡፡
\v 6 በሕዝብ ላይ ይፈርዳል የጦር ሜዳዎችን ሬሳ በሬሳ ያደርጋል፡፡ የብዙ አገሮችን ነገሥታት ይደመሰሳል፡፡
\s5
\v 7 መንገድ ዳር ካለች ፈሳሽ ውሃ ይጠጣል ከድል በኃላ ራሱን ቀና ያደርጋል፡፡
\s5
\c 111
\p
\v 1 ያህዌ ይመስገን፡፡ በቅኖች ሸንጐ በጉባኤም መካከል በፍጹም ልቤ ያህዌን አመሰግናለሁ፡፡
\v 2 የያህዌ ሥራ ታላቅ ናት፤ የሚፈልጓትም ሁሉ አጥብቀው ይናፍቋታል፡፡
\v 3 ሥራው ባለ ግርማና ባለ ክብር ነው ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፡፡
\s5
\v 4 ያህዌ ቸርና መሐሪ ነው ሲታወስ የሚኖር ድንቅ ሥራ አደረገ፡፡
\v 5 ለሚፈሩት ምግባቸውን ይሰጣል ኪዳኑንም ዘወትር ያስባል፡፡
\v 6 ለእነርሱ የአሕዛብን ርስት በመስጠት የአሠራሩን ብርታት አሳይቶአል፡፡
\s5
\v 7 የእጁ ሥራ እውነተኛና ቅን ነው ትእዛዞቹም የታመኑ ናቸው፡፡
\v 8 እነርሱም ለዘላለም የጸኑ ናቸው በታማኝነትና በቅንነት ይጠበቃሉ፡፡
\v 9 ለሕዝቡ ድልን ሰጠ ኪዳኑን ለዘላለም አዘዘ ስሙም የተቀደሰና የተፈራ ነው፡፡
\s5
\v 10 ያህዌን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው ትእዛዙንም የሚጠብቁ ጥሩ ማስተዋል አላቸው፡፡ ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል፡፡
\s5
\c 112
\p
\v 1 ያህዌ ይመስገን ያህዌን የሚፈራ በትእዛዞቹም እጅግ ደስ የሚሰኝ የተባረከ ነው፡፡
\v 2 ዘሩ በምድር ላይ ኃያል ይሆናል የቅኖች ትውልድ ይባረካል፡፡
\s5
\v 3 ሀብትና ብልጽግና ቤቱን ይሞላል ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል፡፡
\v 4 ምሕረትና ቸርነት፣ ቅንነትንም ለሚያደርግ ደግ ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል፡፡
\v 5 ሥራውን በትክክል የሚያከናውን፣ ለጋስና ሳይሰስት የሚያበድር ሰው መልካም ይሆንለታል፡፡
\s5
\v 6 እርሱ ከቶውንም አይናወጥምና ጻድቅ ሰው ሲታወስ ይኖራል፡፡
\v 7 እምነቱን ያህዌ ላይ ያደረገ ልበ ሙሉ ስለሆነ ክፉ ወሬ አያሸብረውም፡፡
\s5
\v 8 ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው፡፡ በመጨረሻ የጠላቶቹን ውድቀት ያያል፡፡
\v 9 በልግስና ለድኾች ይሰጣል ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል፡፡ በክብር ከፍ ከፍ ይላል፡፡
\s5
\v 10 ክፉ ሰው ይህን፤ በማየት ይበሳጫል ጥርሱን ያፋጫል፤ እየመነመነም ይጠፋል፡፡ የክፉዎች ምኞት ትጠፋለች፡፡
\s5
\c 113
\p
\v 1 ያህዌ ይመስገን፡፡ የያህዌ አገልጋዮች ሆይ፣ የያህዌን ስም አመስግኑ፡፡
\v 2 ከአሁን እስከ ዘላለም የያህዌ ስም ይመስገን፡፡
\s5
\v 3 ከፀሐይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ የያህዌ ስም ይመስገን፡፡
\v 4 ያህዌ ከሕዝቦች ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፤ ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው፡፡
\s5
\v 5 እንደ አምላካችን እንደ ያህዌ በላይ በዙፋኑ የተቀመጠ ማን ነው?
\v 6 ራሱን ዝቅ አድርጐ በሰማይና በምድር ያሉትንስ የሚያይ ማን ነው?
\s5
\v 7 ድኻውን ከትቢያ ያነሣል ችግረኛውንም ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡
\v 8 ከመኳንንት ጋር፣ ከሕዝቡም ሹማምንት ጋር ያስቀምጠዋል፡፡
\s5
\v 9 መካኒቱን በቤት ያኖራታል ደስ የተሰኘች የልጆች እናት ያደርጋታል፡፡ ያህዌ ይመስገን!
\s5
\c 114
\p
\v 1 እስራኤል ከግብፅ ወጥቶ ሲሄድ የያዕቆብም ቤት ከባዕድ ሕዝብ ተለይቶ ሲወጣ
\v 2 ይሁዳ ቅዱስ ማደሪያው እስራኤልም ግዛቱ ሆነ፡፡
\s5
\v 3 ባሕር ዐይታ ሸሸች ዮርዳኖስም ወደ ላኋው ተመለሰ፡፡
\v 4 ተራሮች እንደ አውራ በግ ፈነጩ ኮረብቶችም እንደ ጠቦት ዘለሉ፡፡
\s5
\v 5 አንተ ባሕር ምን ሆነህ ሸሸህ? አንተስ ዮርዳኖስ ለምን ወደ ኃላህ ተመለስህ?
\v 6 እናንተ ተራሮች ስለምን እንደ አውራ በግ ፈነጫችሁ? ኮረብቶችስ ለምን እንደ ጠቦት ዘለላችሁ?
\v 7 ምድር ሆይ፣ በጌታ ፊት በያዕቆብ አምላክ ፊት ተንቀጥቀጪ፡፡
\s5
\v 8 እርሱ ዐለቱን ወደ ውሃ ኩሬ ቋጥኙንም ወደ ውሃ ምንጭ ለወጠ፡፡
\s5
\c 115
\p
\v 1 ለእኛ ሳይሆን፣ ያህዌ ሆይ ለእኛ ሳይሆን ስለ ፍቅርህ፣ ስለ ታማኝነትህ ስምህን አክብረው፡፡
\v 2 ስለ ምን ሕዝቦች፣ «አምላካቸው የት አለ?» ይበሉ
\s5
\v 3 አምላካችን በሰማይ ነው እርሱ ደስ የሚለውን አደረገ፡፡
\v 4 የአሕዛብ ጣዖቶች ብርና ወርቅ የሰው እጅ ሥራዎችም ናቸው፡፡
\s5
\v 5 አፍ አላቸው ግን አይናገሩም ዐይን አላቸው ግን አያዩም
\v 6 ጆሮ አላቸው ግን አይሰሙም አፍንጫ አላቸው ግን አያሸቱም፡፡
\s5
\v 7 እጅ አላቸው ግን አይዳሰስም እግር አላቸው ግን አይራመዱም ድምፅም ማሰማት አይችሉም፡፡
\v 8 የሠሩአቸውና የሚታመኑባቸው ሁሉ እንደ እነዚህ ጣዖቶች ናቸው፡፡
\s5
\v 9 የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በያህዌ ታመኑ ረዳታችሁና ጋሻችሁ እርሱ ነው፡፡
\v 10 የአሮን ቤት ሆይ፣ በያህዌ ታመኑ ረዳታችሁና ጋሻችሁ እርሱ ነው፡፡
\v 11 እናንት ያህዌን የምትፈሩ፣ በእርሱ ታመኑ ረዳታችሁና ጋሻችሁ እርሱ ነው፡፡
\s5
\v 12 ያህዌ ያስበናል፤ ይባርከናልም፤ እርሱ የእስራኤልን ቤት ይባርካል የአሮንንም ቤት ይባርካል፡፡
\v 13 ታላላቆችም ሆኑ ታናናሾች እርሱ የሚፈሩትን ሁሉ ይባርካል፡፡
\v 14 ያህዌ እናንተንና ልጆቻችሁን በባርኮቱ ይባርካችሁ፡፡
\s5
\v 15 ሰማይና ምድርን የፈጠረ ያህዌ ይባርካችሁ፡፡
\v 16 ሰማያት የእግዚአብሔር ናቸው ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት፡፡
\s5
\v 17 ወደ ዝምታ ዓለም፣ ወደ መቃብር የወረዱ ሙታን ያህዌን ሊያመሰግኑ አይችሉም፡፡
\v 18 እኛ ግን፣ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም ያህዌን እንባርካለን፡፡ ያህዌ ይመስገን፡፡
\s5
\c 116
\p
\v 1 የልመናዬን ድምፅ ስለ ሰማ ያህዌን ወደድሁት፡፡
\v 2 እርሱ ሰምቶኛልና በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ፡፡
\s5
\v 3 የሞት ወጥመድ ያዘኝ የሲኦልም ጣር አገኘኝ ጭንቅና ሐዘን በረታብኝ፡፡
\v 4 እኔም የያህዌን ስም ጠራሁ «ያህዌ ሆይ፣ እባክህ ነፍሴን አድናት፡፡»
\s5
\v 5 ያህዌ ቸርና መሐሪ ነው፡፡ አምላካችን ርኅሩኅ ነው፡፡
\v 6 አምላካችን ገሮችን ይጠብቃል እኔም በተቸገርኩ ጊዜ አድኖኛል፡፡
\s5
\v 7 ያህዌ መልካም ነገር አድርጐልኛልና ከእንግዲህ ነፍሴ ወደ እረፍት ቦታ ትመለሳለች፡፡
\v 8 አንተ ነፍሴን ከሞት፣ ዐይኔን ከእንባ እግሮቼን ከመሰናክል አድነሃልና፡፡
\s5
\v 9 እኔም በሕያዋን ምድር ያህዌን አገለግላለሁ፡፡
\v 10 «እጅግ ተጨንቄአለሁ» ባልሁ ጊዜ እንኳ በእርሱ ማመኔን አልተውሁም፡፡
\v 11 ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣ «ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው» አልሁ፡፡
\s5
\v 12 ስላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ ለያህዌ ምን ልክፈለው?
\v 13 የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ የያህዌንም ስም እጠራለሁ፡፡
\v 14 በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለያህዌ እፈጽማለሁ፡፡
\v 15 የቅዱሳኑ ሞት በያህዌ ፊት የከበረ ነው፡፡
\s5
\v 16 ያህዌ ሆይ፣ እኔ በእውነት ባርያህ ነኝ፣ የሴት ባርያህም ልጅ ነኝ፡፡ ከእስራቴም ፈታኸኝ፡፡
\v 17 ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ የያህዌንም ስም እጠራለሁ፡፡
\s5
\v 18 በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለያህዌ እፈጽማለሁ
\v 19 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ በመካከልሽ በያህዌ ቤት አደባባይ ይህን አደርጋለሁ፡፡
\s5
\c 117
\p
\v 1 አሕዛብ ሁላችሁ ያህዌን አመስግኑት ሕዝቦችም ሁሉ በምስጋና ከፍ ከፍ አድርጉት፡፡
\v 2 እርሱ ለእኛ ያሳየው ምሕረት ታላቅ ነውና የያህዌ ታማኝነት ጸንቶ ይኖራል፡፡ ያህዌ ይመስገን፡፡
\s5
\c 118
\p
\v 1 ቸር ነውና ያህዌን አመስግኑት ምሕረቱም ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች፡፡
\v 2 የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ «ምሕረቱ ለዘላለም ነው» ይበል፡፡
\s5
\v 3 የአሮን ቤት፣ «ምሕረቱ ለዘላለም ነው» ይበል፡፡
\v 4 ያህዌን የሚፈሩ ሁሉ፣ «ምሕረቱ ለዘላለም ነው» ይበሉ፡፡
\s5
\v 5 በተጨነቅሁ ጊዜ ያህዌን ጠራሁት እርሱም ሰማኝ፤ ነጻም አወጣኝ፡፡
\v 6 ያህዌ ከእኔ ጋር ነው፤ አልፈራም ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
\v 7 ይረዳኝ ዘንድ ያህዌ ከእኔ ጋር ነው የጠላቶቼንም ውድቀት አያለሁ፡፡
\s5
\v 8 በሰው ከመታመን ይልቅ ያህዌን መከታ ማድረግ ይሻላል፡፡
\v 9 በመሪዎች ከመመካት ይልቅ ያህዌን መጠጊያ ማድረግ ይሻላል፡፡
\s5
\v 10 ሕዝቦች ሁሉ ከበቡኝ ነገር ግን በያህዌ ስም አሸነፍኃቸው
\v 11 መክበቡንስ፣ ዙሪያዬን ከበቡኝ ነገር ግን በያህዌ ስም አሸነፍኃቸው፡፡
\v 12 እንደ ንብ መንጋ ከበቡኝ ሆኖም፣ እንደሚነድ እሾኽ ከሰሙ በእርግጥም በያህዌ ስም አሸነፍኃቸው፡፡
\s5
\v 13 ሊጥሉኝ ገፈተሩኝ ያህዌ ግን ረዳኝ፡፡
\v 14 ያህዌ ብርታቴና ደስታዬ ነው፤ የሚታደገኝም እርሱ ነው፡፡
\s5
\v 15 በጻድቃን ድንኳን፣ የእልልታና የሆታ ድምፅ፣ እንዲህ እያለ ያስተጋባል የያህዌ ቀኝ እጅ አሸነፈ፡፡
\v 16 የያህዌ ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አለ፤ የያህዌ ቀኝ እጅ አሸነፈ፡፡
\s5
\v 17 በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፣ አልሞትም የያህዌንም ሥራ ገና እናገራለሁ፡፡
\v 18 ያህዌ ክፉኛ ቀጥቶኝ ነበር ነገር ግን ለሞት አሳልፎ አልሰጠኝም፡፡
\s5
\v 19 የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ ወደዚያ ገብቼ ያህዌን አመሰግናለሁ፡፡
\v 20 ይህች የያህዌ ደጅ ናት፤ ጻድቃንም በእርሷ በኩል ይገባሉ፡፡
\v 21 ሰምተህ መልሰህልኛና፣ አዳኝም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ፡፡
\s5
\v 22 ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማእዘን ራስ ሆነ፡፡
\v 23 ይህም የያህዌ ሥራ ነው ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፡፡
\s5
\v 24 ያህዌ የሠራት ቀን ይህች ናት፣ በእርሷ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፡፡
\v 25 ያህዌ ሆይ፣ እባክህ ድል አቀዳጀን! ያህዌ ሆይ፣ እባክህ አከናውንልን፡፡
\s5
\v 26 በያህዌ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እኛም ከያህዌ ቤት ባረክናችሁ፡፡
\v 27 ያህዌ አምላካችን ነው፤ ብርሃኑንም በላያችን አበራ መሥዋዕቱን መሠዊያው ቀንዶች ላይ በገመድ እሰሩ፡፡
\v 28 አንተ አምላኬ ነህ፤ አመሰግንሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፡፡
\s5
\v 29 ቸር ነውና ያህዌን አመስግኑ ምሕረቱም ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች፡፡
\s5
\c 119
\p
\v 1 መንገዳቸው ነቀፋ የሌለበት በያህዌም ሕግ የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው፡፡
\v 2 ትእዛኦቹን የሚጠብቁ በሙሉ ልባቸውም የሚፈልጉት የተባረኩ ናቸው፡፡
\s5
\v 3 በመንገዱ ይሄዳሉ እንጂ ዐመፅ አያደርጉም፡፡
\v 4 ጠንቅቀን እንጠብቃት ዘንድ አንተ ሥርዐትን አዝዘሃል፡፡
\s5
\v 5 ሥርዐትህን እጠብቅ ዘንድ ምነው መንገዴ ጽኑ በሆነልኝ ኖሮ!
\v 6 ትእዛዞችህን ሁሉ በጥንቃቄ ካስተዋልሁ እፍረት ከቶ አይደርስብኝም፡፡
\s5
\v 7 የጽድቅ ፍርድህን ስማር በቅን ልብ ምስጋና አቀርብልሃለሁ፡፡
\v 8 ሥርዐትህን እጠብቃለሁ አንተ ፈጽሞ አትተወኝ፡፡ ቤት
\s5
\v 9 ጐልማሳ መንገዱን እንዴት ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው፡፡
\v 10 በሙሉ ልቤ እፈልግሃለሁ ከትእዛዞችህ እንድርቅ አትተወኝ፡፡
\s5
\v 11 አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ አኖራለሁ፡፡
\v 12 ያህዌ ሆይ፣ አንተ ቡሩክ ነህ ሥርዐትህን አስተምረኝ፡፡
\s5
\v 13 አንተ የገለጥኸውን የጽድቅ ሥርዐት ሁሉ በአንደበቴ እናገራለሁ፡፡
\v 14 ከብዙ ሀብት ይልቅ በኪዳንህ ሥርዐት ደስ ይለኛል፡፡
\s5
\v 15 ድንጋጌህን አሰላስላለሁ መንገድህም ላይ አተኩራለሁ፡፡
\v 16 በሥርዐትህ ደስ ይለኛል ቃልህንም አልዘነጋም፡፡ ጋሜል
\s5
\v 17 በሕይወት እንድኖርና ቃልህን እንድጠብቅ ለባርያህ መልካም አድርግ፡፡
\v 18 ከሕግህ ድንቅ ነገር እንዳይ ዐይኖቼን ክፈት፡፡
\s5
\v 19 በምድር ላይ መጻተኛ ነኝ ትእዛዞችህን ከእኔ አትሰውር፡፡
\v 20 ጻድቅ ሥርዐትህን ለማወቅ ዘወትር ከመናፈቄ የተነሣ ነፍሴ እጅግ ዛለች፡፡
\s5
\v 21 ከትእዛዞችህ የሳቱትን የተረጉሙ ዕቡያንን ገሠጽህ፡፡
\v 22 ሥርዐቶችህን ጠብቄአለሁና ስድብና ውርደትን ከእኔ አርቅ፡፡
\s5
\v 23 ገዦች ተሰብስበው በእኔ ላይ ቢዶልቱም እንኳ ባርያህ ሥርዐትህን ያሰላስላል፡፡
\v 24 ትእዛዝህ ለእኔ ደስታዬ ነው መካሪየም ነው፡፡ ዳሌጥ
\s5
\v 25 ነፍሴ ከዐፈር ጋር ተጣበቀች በቃልህ ሕይወት ስጠኝ፡፡
\v 26 ስለ መንገዴ ገልጬ ነገርሁህ አንተም መልሰህልኝ ሥርዐትህን አስተምረኝ፡፡
\s5
\v 27 ድንቅ ሥራህን አሰላስል ዘንድ የድንጋጌህን መንገድ እንዳስተውል አድርገኝ፡፡
\v 28 ሐዘን በርትቶብኛል በቃልህ አበርታኝ፡፡
\s5
\v 29 የሽንገላን መንገድ ከእኔ አርቅ በቸርነትህ ሕግህን አስተምረኝ፡፡
\v 30 የእውነትን መንገድ መርጫለሁ ሕግህንም ፊት ለፊቴ አድርጌአለሁ፡፡
\s5
\v 31 ከሥርዐትህ ጋር ተጣብቄአለሁ ያህዌ ሆይ፣ ለውርደት አሳልፈህ አትስጠኝ፡፡
\v 32 ያን እንዳደርግ አንተ ልቤን አስፍተኸዋል በትእዛዞችህ መንገድ እሮጣለሁ፡፡ ሄ
\s5
\v 33 ያህዌ ሆይ፣ የሥርዐትህን መንገድ አስተምረኝ እኔም እስከ መጨረሻው እጠብቀዋለሁ፡፡
\v 34 ሕግህን እንድጠብቅ፣ በፍጹም ልቤም እንድታዘዘው ማስተዋልን ስጠኝ፡፡
\s5
\v 35 በዚያ መሄድ ደስ ይለኛልና በትእዛዞችህ መንገድ ምራኝ፡፡
\v 36 ጽድቅ ከሌለበት ጥቅም ይልቅ ልቤን ወደ ሥርዐትህ አዘንብል፡፡
\s5
\v 37 ከንቱ ነገር ከማየት ዐይኖቼን መልስ በጽድቅህ ሕይወቴን አድስልኝ፡፡
\v 38 ለእኔ ለአገልጋይህና ለሚፈሩህ ሁሉ የሰጠኸውን ተስፋ ቃል ፈጽም፡፡
\s5
\v 39 ጻድቅ ፍርድህ መልካም ነውና የምፈራውን ስድብ አርቅልኝ፡፡
\v 40 እነሆ፣ ድንጋጌህን ናፈቅሁ በጽድቅህም ሕያው አድርገኝ፡፡ ዋው
\s5
\v 41 ያህዌ ሆይ፣ ዘላለማዊ ፍቅርህን ስጠኝ በተስፋ ቃልህ መሠረት አድነኝ፡፡
\v 42 በቃልህ ታምኛለሁና ለሚሰድቡኝ መልስ እሰጣለሁ፡፡
\s5
\v 43 ሕግህን ተስፋ አድርጌአለሁና የእውነትን ቃል ከአፌ አታርቅ፡፡
\v 44 ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕግህን ዘወትር እጠብቃለሁ፡፡
\s5
\v 45 ሥርዐትህን እሻለሁና በፍጹም ነጻነት እኖራለሁ፡፡
\v 46 ትእዛዞችህን በነገሥታት ፊት እናገራለሁ ይህን በማድረጌም እፍረት አይሰማኝም፡፡
\s5
\v 47 አጥብቄ እወደዋለሁና በትእዛዞችህ ደስ ይለኛል፡፡
\v 48 እጆቼን ወደምወዳቸው ትእዛዞችህ አነሣለሁ፤ ሥርዐትህንም አሰላስላለሁ፡፡ ዛይ
\s5
\v 49 በዚያ ተስፋ ሰጥተኸኛልና ለባርያህ የገባኸውን ቃል አስብ፡፡
\v 50 የተስፋ ቃልህ ሕያው አድርጐኛልና ይህ በመከራዬ መጽናኛዬ ሆነ፡፡
\s5
\v 51 ትዕቢተኞች እጅግ ተሳለቁብኝ እኔ ግን ከሕግህ ንቅንቅ አላልሁም፡፡
\v 52 ያህዌ ሆይ፣ ከጥንት የነበረውን ድንጋጌህን አሰብሁ በዚህም ተጽናናሁ፡፡
\s5
\v 53 ሕግህን ከናቁ ክፉዎች የተነሣ እጅግ ተቆጣሁ፡፡
\v 54 በእንግድነቴ አገር ሥርዐትህ መዝሙሬ ሆነ፡፡
\s5
\v 55 ያህዌ ሆይ፣ ስምህን በሌሊት አስባለሁ ሕግህንም እጠብቃለሁ፡፡
\v 56 ሥርዐትህን ጠብቄአለሁና ይህ የሁልጊዜ ልምዴ ሆነ፡፡ ሔት
\s5
\v 57 ያህዌ ዕድል ፈንታዬ ነው ቃልህን ለመታዘዝ ቆርጫለሁ፡፡
\v 58 በፍጹም ልቤ የአንተን ሞገስ እፈልጋለሁ እንደ ቃልህ ቸርነት አሳየኝ፡፡
\s5
\v 59 መንገዴን መረመርሁ አካሄዴንም ወደ ሥርዐትህ አቀናሁ፡፡
\v 60 ትእዛዝህን ለመጠበቅ ቸኮልሁ፤ አልዘገየሁም፡፡
\s5
\v 61 የክፉዎች ገመድ ተተበተበብኝ እኔ ግን ሕግህን አልረሳሁም፡፡
\v 62 ስለ ጻድቅ ሥርዐትህ አንተን ለማመስገን በእኩለ ሌሊት እነሣለሁ፡፡
\s5
\v 63 እኔ አንተን የሚፈሩና ሥርዐትህንም የሚጠብቁ ሁሉ ባልንጀራ ነኝ፡፡
\v 64 ያህዌ ሆይ፣ ምድር በምሕረትህ ተሞላች ሥርዐትህን አስተምረኝ፡፡ጤት
\s5
\v 65 ያህዌ ሆይ፣ እንደ ቃልህ ለአገልጋይህ መልካም አድርገሃል፡፡
\v 66 በትእዛዞችህ አምናለሁና ተገቢውን ማስተዋልና ዕውቀትን አስተምረኝ፡፡
\s5
\v 67 አንዳች ጉዳት ሳይደርስብኝ መንገድ ስቼ ሄድሁ አሁን ግን ቃልህን እጠብቃለሁ፡፡
\v 68 አንተ መልካም ነህ፤ የምታደርገውም መልካም ነው እንግዲህ ሥርዐትህን አስተምረኝ፡፡
\s5
\v 69 እብሪተኞች በሐሰት ስሜን አጠፉ እኔ ግን በፍጹም ልቤ ትእዛዝህን እጠብቃለሁ፡፡
\v 70 ልባቸው የሰባና የደነደነ ነው እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል፡፡
\s5
\v 71 ሥርዐትህን እማር ዘንድ በመከራ ውስጥ ማለፌ መልካም ሆነልኝ፡፡
\v 72 ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል፡፡ ዮድ
\s5
\v 73 እጆችህ ሠሩኝ፣ አበጃጁኝም ትእዛዞችህን እንድማር ማስተዋልን ስጠኝ፡፡
\v 74 ቃልህን ተስፋ አድርጌአለሁና የሚፈሩህ እኔን ዐይተው ደስ ይላቸዋል፡፡
\s5
\v 75 ያህዌ ሆይ፣ ፍርድህ እውነተኛ እንደ ሆነ ያስጨነቅኸኝም በታማኝነት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፡፡
\v 76 ለአገልጋይህ በገባኸው ቃል መሠረት ምሕረትህ መጽናኛዬ ይሁንልኝ፡፡
\s5
\v 77 ሕግህ ደስታዬ ነውና በሕይወት እንድኖር ራራልኝ፡፡
\v 78 በሐሰት የሚከሱኝ ትዕቢተኞች ይዋረዱ እኔ ግን ሥርዐትህን አሰላስላለሁ፡፡
\s5
\v 79 አንተን የሚፈሩህ ሥርዐቶችህንም የሚያውቁ ወደ እኔ ይመለሱ፡፡
\v 80 እፍረት እንዳይደርስብኝ ልቤ በሥርዐትህ ያለ ነቀፋ ይሁን፡፡ ካፍ
\s5
\v 81 ነፍሴ ማዳንህን እጅግ ናፈቀች ቃልህንም ተስፋ አድርጌአለሁ፡፡
\v 82 «መቼ ታጽናናኛለህ?» እያልሁ በመጠባበቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ፡፡
\s5
\v 83 ጢስ እንደ ጠገበ የወይን ጠጅ አቁማዳ ሆኛለሁ ሥርዐትህን አልረሳሁም፡፡
\v 84 እኔ አገልጋይህ እስከ መቼ ልቆይ? በሚያሳድዱኝ ላይ የምትፈርደው መቼ ነው?
\s5
\v 85 ሕግህን የማያከብሩ፤ ትዕቢተኞች ጉድጓድ ቆፈሩልኝ፡፡
\v 86 ትእዛዞችህ ሁሉ አስተማማኝ ናቸው ሰዎች ያለ ምክንያት እያሳደዱኝ ስለሆነ ርዳኝ፡፡
\s5
\v 87 ከምድር ሊያጠፉኝ ጥቂት ቀራቸው እኔ ግን ትእዛዞችህን ችላ አላልሁም፡፡
\v 88 ሕግህን እጠብቅ ዘንድ በዘላለማዊ ፍቅርህ ሕያው አድርገኝ፡፡ ላሜድ
\s5
\v 89 ያህዌ ሆይ፣ ቃልህ በሰማይ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፡፡
\v 90 ታማኝነትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ሁሉ ነው ምድርን መሠረትሃት እርሷም ጸንታ ትኖራለች፡፡
\s5
\v 91 ነገሮች ሁሉ አገልጋዮችህ ስለሆኑ በሕግህ መሠረት እስከ ዛሬ ድረስ ጸንተው ይኖራሉ፡፡
\v 92 ሕግህ ደስታዬ ባይሆን ኖሮ፣ በደረሰብኝ መከራ በጠፋሁ ነበር፡፡
\s5
\v 93 በእርሱ ሕያው አድርገኸኛልና ትእዛዞችህን ከቶ አልረሳሁም፡፡
\v 94 እኔ የአንተ ነኝ፤ እባክህ አድነኝ ሕግህንም ፈልጌአለሁ፡፡
\s5
\v 95 ክፉዎች ሊያጠፉኝ አድብተዋል እኔ ግን ሕግህን መረዳት እፈልጋለሁ፡፡
\v 96 ማንኛውም ነገር የራሱ ወሰን እንዳለው አየሁ፤ ትእዛእህ ግን እጅግ ሰፊ ነው፡፡ ሜም
\s5
\v 97 አቤቱ ሕግህን ምንኛ ወደዱሁ ቀኑን ሙሉ አሰላስለዋለሁ፡፡
\v 98 ዘወትር ከእኔ ጋር በመሆኑ፣ ሕግህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ፡፡
\s5
\v 99 ሥርዐቶችህን አሰላስላለሁና ከአስተማሪዎቼ ሁሉ የበለጠ ማስተዋል አለኝ፡፡
\v 100 መመሪያህን ተከትዬ ስለምሄድ ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋይ ሆንሁ፡፡
\s5
\v 101 ቃልህን እጠብቅ ዘንድ እግሬን ከክፉ መንገድ ከለከልሁ፡፡
\v 102 አንተው ራስህ አስተምረኸኛልና ከድንጋጌህ ዘወር አላልሁም፡፡
\s5
\v 103 ቃልህ ለምላሴ ምንኛ ጣፋጭ ነው ለአፌም ከማር ወለላ ይልቅ ጣዕም አለው፡፡
\v 104 ከመመሪያህ ማስተዋል አገኘሁ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ፡፡ ኖን
\s5
\v 105 ቃልህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴም ብርሃን ነው፡፡
\v 106 ጻድቅ ትእዛዞችህን ለመጠበቅ በመሐላ የገባሁትን ቃል አጸናለሁ፡፡
\s5
\v 107 እጅግ ተጐድቻለሁና ያህዌ ሆይ፣ እንደ ቃል ሕያው አድርገኝ፡፡
\v 108 ያህዌ ሆይ፣ ፈቅጄ የማቀርበውን የአፌን ምስጋና መሥዋዕት ተቀበል፡፡
\s5
\v 109 ነፍሴ ዘወትር አደጋ ላይ ናት፤ እኔ ግን ሕግህን አልረሳሁም፡፡
\v 110 ክፉዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ እኔ ግን ከመመሪያህ ፈቀቅ አላልሁም፡፡
\s5
\v 111 ሕግህ የዘላለም ውርሴ ነው የልቤም ደስታ ይኸው ነው፡፡
\v 112 ትእዛዝህን እስከ መጨረሻው ለዘላለም ለመፈጸም ልቤን ወደዚያው አዘነበልሁ፡፡ ሳምኬት
\s5
\v 113 መንታ ልብ ያላቸው ወላዋዮችን ጠላሁ፤ ሕግህን ግን ወደድሁ፡፡
\v 114 አንተ ጋሻዬና መሸሸጊያ ነህ ቃልህን በተስፋ እጠብቃለሁ፡፡
\s5
\v 115 የአምላኬን ትእዛዞች እጠብቅ ዘንድ እናንት ክፉ አድራጊዎች ከእኔ ራቁ
\v 116 በሕይወት እኖር ዘንድ በቃልህ ደግፈኝ ተስፋዬም መና ቀርቶ አልፈር፡፡
\s5
\v 117 ያለ ስጋት እንድኖር ደግፈህ ያዘኝ ሥርዐትህንም ዘወትር አሰላስላለሁ፡፡
\v 118 አታላዮችና የማያስተማምኑ ስለሆኑ ከሥርዐትህ የሚያፈነግጡትን ሁሉ ወዲያ አስወገድሃቸው፡፡
\s5
\v 119 የምድርን ክፉዎች ሁሉ እንደ ጥራጊ አስወገድሃቸው፡፡ ስለዚህ እኔ ትእዛዞችህን ወደድሁ፡፡
\v 120 አንተን በመፍራት ሥጋዬ ተንቀጠቀጠ ፍርድህን እፈራለሁ፡፡ ዔ
\s5
\v 121 ትክክልና መልም የሆነውን አድርጌአለሁና ለሚጨቁኑኝ አሳልፈህ አትስጠኝ፡፡
\v 122 ለባርያህ ደኅንነት ዋስትና ሁን ትዕቢተኛ እንዲረግጠኝ አትፍቀድለት፡፡
\s5
\v 123 ማዳንህንና የጽድቅ ቃልህን በመጠባበቅ ዐይኖቼ ደከሙ፡፡
\v 124 ለእኔ ለአገልጋይህ ታማኝትህን አሳይ፣ ሥርዐቶችህንም አስተምረኝ፡፡
\s5
\v 125 እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ ሥርዐትህንም እንዳውቅ ማስተዋልን ስጠኝ፡፡
\v 126 ያህዌ ሆይ፣ ሕግህ እየተጣሰ ነውና ጊዜው አንተ የምትሠራበት ነው፡፡
\s5
\v 127 ከወርቅ፣ ከንጹሕም ወርቅ ይልቅ በእውነት ትእዛዞችህን ወደድሁ፡፡
\v 128 ስለዚህ መመሪያዎችን በጥንቃቄ ጠበቅሁ የሐሰትንም መንገድ ጠላሁ፡፡ ፌ
\s5
\v 129 ሥርዐቶችህ አስደናቂ ናቸው እኔም በሙሉ ልቤ እታዘዛቸዋለሁ፡፡
\v 130 የቃልህ ፍቺ ያበራል አላዋቂዎችን አስተዋይ ያደርጋል፡፡
\s5
\v 131 ትእዛዝህን በመናፈቄ አፌን ከፊትሁ አለከለክሁም፡፡
\v 132 ስምህን ለሚፈሩ ዘወትር እንደምታደርገው ወደ እኔ ተመልሰህ ምሕረት አድርግልኝ፡፡
\s5
\v 133 እንደ ቃልህ አካሄዴን ቀና አድርግልኝ ኃጢአት እንዲሠለጥንብኝም አትፍቀድ፡፡
\v 134 ትእዛዝህን መጠበቅ እንድችል ከሰዎች ጥቃት አድነኝ፡፡
\s5
\v 135 ፊትህ በባርያህ ላይ ያብራ ሥርዐትህንም አስተምረኝ፡፡
\v 136 ሰዎች ሕግህን ስለ ጣሱ እንባዬ እንደ ወራጅ ውሃ ፈሰሰ፡፡
\s5
\v 137 ያህዌ ሆይ፣ አንተ ጻድቅ ነህ ፍርድህም ትክክል ነው፡፡
\v 138 ሕግህ በፍጹም እውነትና ትክክል ነው፡፡
\s5
\v 139 ጠላቶቼ ቃልህን መዘንጋታቸው በጣም አበሳጨኝ፡፡
\v 140 ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው ባርያህም ወደደው፡፡
\s5
\v 141 እኔ የማልጠቅምና የተናቅሁ ብሆን እንኳ፣ መመሪያህን አልዘነጋሁም፡፡
\v 142 ጽድቅህ ለዘላለም ትክክል ነው ሕግህም የታመነ ነው፡፡
\s5
\v 143 መከራና ስቃይ ቢደርስብኝ እንኳ አሁንም ትእዛዝህ ደስታዬ ነው፡፡
\v 144 ሥርዐትህ ለዘላለም ጻድቅ ነው በሕይወት መኖር እንድችል ማስተዋል ስጠኝ፡፡ ቆፍ
\s5
\v 145 ያህዌ ሆይ፣ በፍጹም ልቤ እጮኻለሁና መልስልኝ፤ ሥርዐትህንም እጠብቃለሁ፡፡
\v 146 ወደ አንተ እጣራለሁና አድነኝ ሥርዐትህንም እጠብቃለሁ፡፡
\s5
\v 147 ጐሕ ከመቅደዱ በፊት ርዳታህን በመፈለግ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ቃልህንም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
\v 148 ቃልህን አሰላስል ዘንድ ሌሊቱን ሙሉ ዐይኔ ሳይከደን ያድራል፡፡
\s5
\v 149 እንደ ቸርነትህ መጠን ድምፄን ስማ ያህዌ ሆይ፣ በትእዛዝህ መሠረት ሕይወቴን ጠብቅ፡፡
\v 150 የሚያሳድዱኝ ወደ እኔ ቀርበዋል ከሕግህ ግን ርቀዋል፡፡
\s5
\v 151 ያህዌ ሆይ፣ አንተ ቅርብ ነህ መመሪያዎችህም የታመኑ ናቸው፡፡
\v 152 ለዘላለም እንደ መሠረትሃቸው ጥንት ከሥርዐትህ ተምሬአለሁ፡፡ ሬስ
\s5
\v 153 ሕግህን አልረሳሁምና መከራዬን ተመልከት አድነኝም፡፡
\v 154 ተሟገትልኝ አድነኝም እንደ ተስፋ ቃልህም ጠብቀኝ፡፡
\s5
\v 155 ሥርዐትህን ስለማይፈልጉ ድነት ከክፉዎች የራቀ ነው፡፡
\v 156 ያህዌ ሆይ፣ ርኅራኄህ ታላቅ ነው፤ እንደ ሁልጊዜው በሕይወት ጠብቀኝ፡፡
\s5
\v 157 አሳዳጆቼና ጠላቶቼ በዝተዋል፤ እኔ ግን ከሥርዐትህ ፈቀቅ አላልሁም፡፡
\v 158 ቃህን አልጠበቁም ከዳተኞችን ዐይቼ ተጸየፍኃቸው፡፡
\s5
\v 159 መመሪያህን እንዴት እንደምወድ እይ፤ ያህዌ ሆይ፣ እንደ ምሕረትህ ሕያው አድርገኝ፡፡
\v 160 የቃልህ ሥረ መሠረት እውነት ነው ጻድቅ የሆነው ሕግህም ዘላለማዊ ነው፡፡ ሳን
\s5
\v 161 መመሪያህን እንዴት እንደምወድ እይ፤ ያህዌ ሆይ፣ እንደ ምሕረትህ ሕያው አድርገኝ፡፡
\v 162 የቃልህ ሥረ መሠረት እውነት ነው ጻድቅ የሆነው ሕግህም ዘላለማዊ ነው፡፡ ሳን
\s5
\v 163 ሐሰትን እጠላለሁ፤ እጸየፋለሁ ሕግህን ግን ወደድሁ፡፡
\v 164 ጻድቅ ስለሆነው ሕግህ በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለሁ፡፡
\s5
\v 165 ሕግህን ለሚወዱ ብዙ ሰላም አላቸው ዕንቅፋትም የለባቸውም፡፡
\v 166 ያህዌ ሆይ፣ ማዳንህን እጠብቃለሁ ትእዛዞችህንም እፈጽማለሁ፡፡
\s5
\v 167 ትእዛዝህን እጠብቃለሁ በሙሉ ልቤም እወዳቸዋለሁ፡፡
\v 168 ትእዛዝህንና ሕግህን አከብራለሁ አንተ የምሠራውን ሁሉ ታውቃለህ፡፡ ታው
\s5
\v 169 ያህዌ ሆይ፣ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ስጮኽ ስማኝ እንደ ቃልህም ማስተዋልን ስጠኝ፡፡
\v 170 ልመናዬ ወደ አንተ ይድረስ በተስፋ ቃልህም መሠረት አድነኝ፡፡
\s5
\v 171 ሥርዐትህን አስተምረኸኛልና ከንፈሮቼ ምስጋናን አፈለቁ፡፡
\v 172 ትእዛዞችህ ሁሉ ትክክል ስለሆኑ ስለ ቃልህ እዘምራለሁ፡፡
\s5
\v 173 መመሪያህን መርጫለሁና እጅህ እኔን ለመርዳት ዝግጁ ይሁን፡፡
\v 174 ያህዌ ሆይ፣ ማዳንህን ናፈቅሁ ሕግህም ደስታዬ ነው፡፡
\s5
\v 175 አመሰግንህ ዘንድ በሕይወት ልኑር ሕግህም ይርዳኝ፡፡
\v 176 እንደ ጠፋ በግ ተቅበዘበዝሁ ትእዛዞችህን አልረሳሁምና ባርያህን ፈልገው፡፡
\s5
\c 120
\p
\v 1 በጨነቀኝ ጊዜ ወደ ያህዌ ተጣራሁ እርሱም መለሰልኝ፡፡
\v 2 ከሐሰተኛ ከንፈር፣ ከአታላይ ምላስም አድነኝ፡፡
\s5
\v 3 እናንት አታላዮች እግዚአብሔር እንዴት ይቅጣችሁ፣ ምንስ ቢከፍላችሁ ይሻላል?
\v 4 በተሳለ የጦረኛ ቀስት በግራር ከሰል ፍም ይቀጣችኃል፡፡
\s5
\v 5 የምኖረው በሜሼክ ስለ ሆነ የነበርኩትም በቄዳር ድንኳኖች መካከል ስለ ነበር ወዮልኝ፡፡
\v 6 ሰላምን ከሚጠሉ ጋር በጣም ረጅም ጊዜ ኖርሁ፡፡
\v 7 እኔ ሰላም ፈላጊ ነኝ፡፡ በተናገርሁ ጊዜ ግን እነርሱ ጠብ ይፈልጋሉ፡፡
\s5
\c 121
\p
\v 1 ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ ረዳቴ ከወዴት ይመጣል?
\v 2 ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከያህዌ ዘንድ ይመጣል፡፡
\s5
\v 3 እግርህ እንዲንሸራተት አይፈቅድም አንተን የሚጠብቅህም አይተኛም፡፡
\v 4 እነሆ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፉምም፡፡
\s5
\v 5 ያህዌ ይጠብቅሃል፤ ያህዌ በቀኝህ በኩል ይከልልሃል፡፡
\v 6 ፀሐይ በቀን አያቃጥልህም ጨረቃም በሌሊት አይጐዳህም፡፡
\s5
\v 7 ያህዌ ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል እርሱ ሕይወትህንም ይጠብቃል፡፡
\v 8 ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም ያህዌ በምታደርገው ሁሉ ይጠብቅሃል፡፡
\s5
\c 122
\p
\v 1 «ወደ ያህዌ ቤት እንሂድ» ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ፡፡
\v 2 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ እግሮቻችን በደጆችሽ ውስጥ ቆመዋል፡፡
\v 3 ኢየሩሳሌም በጥንቃቄ የተገነባች ከተማ ናት!
\s5
\v 4 ለእስራኤል ምስክር ይሆን ዘንድ ነገዶች፣ የያህዌ ነገዶች ወደዚያ ይወጣሉ፡፡
\v 5 በዚያም የፍርድ ዙፋኖች የዳዊት ቤት ዙፋኖች ተዘርግተዋል፡፡
\s5
\v 6 ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ፡፡ «የሚወዱሽ ሰላም ይሁንላቸው፡፡
\v 7 በቅጥሮችሽ ውስጥ ሰላም ይሁን በምሽጐችሽም ውስጥ መረጋጋት ይስፈን፡፡»
\s5
\v 8 ስለ ወንድሞቼና ስለ ወዳጆቼ ኢየሩሳሌምን፣ «ሰላም ከአንቺ ጋር ይሁን» እላታለሁ፡፡
\v 9 ስለ አምላካችን ያህዌ ቤት መልካም እንዲሆንልሽ እሻለሁ፡፡
\s5
\c 123
\p
\v 1 በሰማያት የምትኖር ሆይ፣ ዐይኖቼን ወደ አንተ እነሣለሁ፡፡
\v 2 የባርያዎች ዐይን ወደ ጌታቸው እጅ እንደሚመለከት የባርያዪቱም ዐይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደሚመለከት ምሕረት እስኪያደርግልን ድረስ የእኛም ዐይን ወደ አምላካችን ወደ ያህዌ ይመለከታሉ፡፡
\s5
\v 3 ያህዌ ሆይ፣ እጅግ ተዋርደናልና ማረን፣ አቤቱ ማረን፡፡
\v 4 በትዕቢተኞች ብዙ ተዋርደናል፣ በትምክሕተኞችም እጅግ ተንቀናል፡፡
\s5
\c 124
\p
\v 1 «ያህዌ ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ» ይበል እስራኤል፡፡
\v 2 ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ ያህዌ ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ
\v 3 ቁጣቸው በእኛ ላይ በነደደ ጊዜ በሕይወት እያለን በዋጡን ነበር፡፡
\s5
\v 4 ጐርፍ በወሰደን፣ ውሃም በሸፈነን ነበር፡፡
\v 5 ብርቱ ማዕበልም ባሰጠመን ነበር
\s5
\v 6 በጥርሳቸው እንዲቦጫጭቁን ያልፈቀደ ያህዌ ይባረክ
\v 7 ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኝ ወጥመድ አመለጠች ወጥመዱ ተሰበረ እኛም አመለጥን፡፡
\s5
\v 8 ሰማይና ምድርን የሠራ ያህዌ ረዳታችን ነው፡፡
\s5
\c 125
\p
\v 1 በያህዌ የሚተማመኑ ሳትናወጥ ለዘላለም እንደምትኖር የጽዮን ተራራ ናቸው፡፡
\v 2 ተራሮች ኢየሩሳሌምን እንደ ከበቧት ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ያህዌም በሕዝቡ ዙሪያ ነው፡፡
\v 3 ጻድቁ ክፉ እንዳያደርግ የዐመፃ በትረ መንግሥት የጻድቃንን ምድር አይግዛ፡፡
\s5
\v 4 ያህዌ ሆይ፣ መልካም ለሆኑ፣ ልባቸውም ቀና ለሆኑት መልካም አድርግ፡፡
\v 5 ወደ ጠማማ መንገዳቸው የሚመለሱትን ግን ያህዌ ከክፉ አድራጊዎች ጋር ያጠፋቸዋል፡፡ ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን፡፡
\s5
\c 126
\p
\v 1 ያህዌ የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ ሕልም እንጂ፣ እውን አልመሰለንም፡፡
\s5
\v 2 በዚያ ጊዜ አፋችን በሣቅ፣ አንደበታችንም በዝማሬ ተሞላ፡፡ በዚያ ጊዜ በሕዝቦች መካከል፣ «ያህዌ ታላቅ ነገር አደረገላቸው» ተባለ፡፡
\v 3 ያህዌ ታላቅ ነገር አደረገልን እኛም እጅግ ደስ አለን፡፡
\s5
\v 4 ያህዌ ሆይ፣ በኔጌቭ እንዳሉ ምንጮች ምርኮአችን መልስ፡፡
\v 5 በእንባ የሚዘሩ በእልልታ ይዘራሉ
\v 6 ዘሩን ተሸክመው እያለቀሱ የተሰማሩ ነዶአቸውን ተሸክመው እልል እያሉ ይመለሳሉ፡፡
\s5
\c 127
\p
\v 1 ያህዌ ቤትን ካልሠራ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ ያህዌ ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል፡፡
\v 2 የዕለት ጉርስ ለማግኘት በመጣር ማለዳ መነሣት፣ አምሽቶም መግባት ከንቱ ነው፡፡ ያህዌ ለወዳጆቹ ተኝተው እያለ የሚያስፈልጋቸውን ይሰጣቸዋል፡፡
\s5
\v 3 እነሆ ልጆች የያህዌ ስጦታ ናቸው የማሕፀንም ፍሬ የእርሱ ችሮታ ነው፡፡
\v 4 በወጣትነት የተገኙ ልጆች በጦረኛ እጅ እንዳሉ ፍላጾች ናቸው
\v 5 ኮረጆዎቹን በእነዚህ የሞላ ሰው የተባረከ ነው፡፡ ከጠላቶቹ ጋር በሚሟገትበት ጊዜ አፍሮ አይገባም፡፡
\s5
\c 128
\p
\v 1 ያህዌን የሚፈሩ ሁሉ በመንገዶቹም የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው፡፡
\v 2 በእጆችህ ሥራ ደስ ይልሃል ትባረካለህ፤ ይሳካልሃልም፡፡
\s5
\v 3 በቤትህ ውስጥ ሚስትህ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች ልጆችህም በማእድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ተክል ይሆናሉ፡
\v 4 አዎን፣ ያህዌን የሚፈራ እንዲህ ይባረካል፡፡
\v 5 ያህዌ ከጽዮን ይባርክህ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ያሳይህ፡፡
\v 6 የልጅ ልጆችን ለማየት ያብቃህ እስራኤል ላይ ሰላም ይሁን፡፡
\s5
\c 129
\p
\v 1 «ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ» ይበል እስራኤል፡፡
\v 2 በእርግጥ፣ ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ ይሁን እንጂ አላሸነፉኝም፡፡
\v 3 አራሾች ጀርባዬን አረሱት ትልማቸውንም አስረዘሙት፡፡
\s5
\v 4 እግዚአብሔር ጻድቅ ነው የክፉዎችን ገመድ በጣጥሶ ጣለ፡፡
\v 5 ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ ወደ ኃላቸውም ይመለሱ፡፡
\s5
\v 6 ገና ከመብቀሉ እንደሚደርቅ ቤት ጣር ላይ እንዳለ ሣር ይሁኑ፡፡
\v 7 ደግሞ ለዐጫጁ እጁን ለነዶ ሰብሳቢ እቅፉን እንደማይሞላ ነዶ ይሁኑ፡፡
\v 8 መንገድ ዐላፊዎችም፣ «የያህዌ በረከት እናንተ ላይ ይሁን፤ በያህዌ ስም ባረክናችሁ አይበሉ፡፡»
\s5
\c 130
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ከጥልቅ ወደ አንተ እጮኻለሁ፡፡
\v 2 ጌታ ሆይ፣ ምሕረትን ፈልጌ ስጮኽ ድምፄን ስማ ጆሮህንም ወደ እኔ አዘንብል፡፡
\s5
\v 3 ያህዌ ሆይ፣ አንተ ኃጢአትን ብትከታተል ኖሮ ማን መቆም ይችል ነበር፡፡
\v 4 ነገር ግን በአንተ ዘንድ ይቅርታ አለ ስለዚህ ልትፈራ ይገባሃል፡፡
\s5
\v 5 ያህዌን በትዕግሥት እጠብቃለሁ በቃሉም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
\v 6 ዘብ አዳሪ ንጋትን እንደሚጠብቅ እኔም ጌታን በትዕግሥት እጠብቃለሁ፡፡
\s5
\v 7 ያህዌ መሓሪ ነው፤ ይቅር ለማለትም ፈቃደኛ ነው እስራኤል ሆይ፣ ያህዌን ተስፋ አድርግ፡፡
\v 8 እርሱ እስራኤልን ከኃጢአቱ ሁሉ ያድነዋል፡፡
\s5
\c 131
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ልቤ አልታበየም ዐይኔም ከፍ ከፍ አላለም፡፡ ለራሴም ታላላቅ ነገሮችን ተስፋ አላደረግሁም ከእኔ በላይ በሆነ ነገርም አልተጨነቅሁም፡፡
\s5
\v 2 ነገር ግን ነፍሴን ጸጥ፣ ዝም አሰኘኃት ነፍሴ ጡት እንዳስተውት ሕፃን በውስጤ ጸጥ አለች፡፡
\v 3 እስራኤል ሆይ አሁንና ለዘላለም ያህዌ ተስፋ አድርግ፡፡
\s5
\c 132
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ዳዊትን፣ የተቀበለውንም መከራ ሁሉ አስብ፡፡
\v 2 እርሱ ለያህዌ ማለ፣ ለያዕቆብም ኃያል አምላክ ቃል ገባ፤
\s5
\v 3 እንዲህም አለ፣ «ወደ ቤቴ አልገባም፤ አልጋዬ ላይ አልወጣም
\v 4 ለዐይኖቼ እንቅልፍን ለሽፋሽፍቶቼም ዕረፍትን አልሰጥም፤
\v 5 ለያህዌ ስፍራን፣ ለያዕቆብ ኃያል ማደሪያን እስካገኝ ድረስ፡፡
\s5
\v 6 እነሆ፣ በኤፍራታ ሰማነው፣ በይዓሪም አገኘነው፡፡
\v 7 ወደ ማደሪያው እንግባ እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንስገድ፡፡
\v 8 ያህዌ ሆይ ተነሥ አንተና የኃይልህ ታቦታ ወደ ማደሪያህ ስፍራ ሂዱ፡፡
\s5
\v 9 ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ ታማኞችህ እልል ይበሉ፡፡
\v 10 ስለ ባርያህ ስለ ዳዊት ስትል የተቀባኸውን ንጉሥ አትተወው፡፡
\s5
\v 11 ያህዌ ለዳዊት በእውነት ማለ በማይታጠፍ መሐላ እንዲህ አለ «ከልጆችህ አንዱን ዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ
\v 12 ልጆችህ ኪዳኔን፣ የማስተምራቸውንም ሕጌን ቢጠብቁ፣ ልጆቻቸው ለዘላለም በዙፋንህ ላይ ይቀመጣሉ፡፡»
\s5
\v 13 ያህዌ ጽዮንን መርጧልና ማደሪያው እንድትሆን ወዶአልና፡፡
\v 14 «ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት ፈልጌአታለሁና በእርሷ እኖራለሁ፡፡
\s5
\v 15 እጅግ አትረፍርፌ እባርካታለሁ ድኾቿን እንጀራ አጠግባለሁ፡፡
\v 16 ካህናቶቿን ማዳንን አለብሳቸዋለሁ ታማኞቿም እልል ይላሉ፡፡
\s5
\v 17 በዚያ ለዳዊት ቀንድ አበቅላለሁ ለቀባሁትም ሰው መብራት አዘጋጃለሁ፡፡
\v 18 ጠላቶቹን እፍረት አከናንባቸዋለሁ እርሱ ላይ ግን አክሊሉ ያበራል፡፡
\s5
\c 133
\p
\v 1 ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ቢኖሩ እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ አስደሳች ነው፡፡
\s5
\v 2 በአሮን ራስና ጢም ላይ እንደሚፈስስ እስከ ልብሱን ዐንገት ጌጥ ድረስ እንደሚወርድ ውድ ሽቱ ነው፡፡
\v 3 ደግሞም በጽዮን ተራራ ላይ እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፡፡ ያህዌ በዚያ በረከቱን አዞአልና ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዞአል፡፡
\s5
\c 134
\p
\v 1 እናንት በሌሊት ቆማችሁ በያህዌ ቤት የምታገለግሉ የያህዌ ባርያዎች ሁላችሁ፣ ያህዌን አመስግኑ፡፡
\v 2 ወደ መቅደሱ እጃችሁን አንሡና ያህዌን ባርኩ፡፡
\s5
\v 3 ሰማይና ምድርን የሠራ ያህዌ ከጽዮን ይባርካችሁ፡፡
\s5
\c 135
\p
\v 1 ያህዌን አመስግኑ የያህዌን ስም ወድሱ፤ እናንት የያህዌ አገልጋዮች አመስግኑት፡፡
\v 2 በያህዌ ቤት በአምላካችንም ቤት አደባባይ የምትቆሙ አመስግኑት፡፡
\s5
\v 3 መልካም ነውና ያህዌን አመስግኑ ደስ የሚያሰኝ ነውና ለስሙ ዘምሩ፡፡
\v 4 ያህዌ ያዕቆብን ለራሱ፣ እስራኤልም ርስቱ እንዲሆን መርጦአልና፡፡
\s5
\v 5 ያህዌ ታላቅ መሆኑን፣ ጌታችንም ከአማልክት በላይ መሆን ዐውቃለሁ፡፡
\v 6 በሰማይም ሆነ በምድር በባሕርና በጥልቅ ውቅያኖስ ያህዌ የወደደውን ያደርጋል፡፡
\s5
\v 7 እርሱ ደመናትን ከሩቅ ቦታ ያመጣል ከዝናብ ጋር መብረቅ እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ነፋሳትንም ከማከማቻው ያወጣል፡፡
\s5
\v 8 ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ የግብፃውያንን በኩር ገደለ፡፡
\v 9 ግብፅ ሆይ፣ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ፣ በመካከልሽም ምልክቶችንና ድንቆችን አደረገ፡፡
\s5
\v 10 ብዙ ሕዝቦች መታ ኃያላን ነገሥታት ገደለ፡፡
\v 11 የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎንን የባሰን ንጉሥ ዐግን የከነዓንን ነገሥታት ሁሉ ገደለ፡፡
\s5
\v 12 ምድራቸውንም ለሕዝቡ ለእስራኤል ርስት አድርጐ ሰጠ፡፡
\v 13 ያህዌ ሆይ፣ ስምህ ዘላለማዊ ነው መታሰቢያህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል፡፡
\s5
\v 14 ያህዌ ለሕዝቡ ይፈርዳልና ለአገልጋዮቹም ይራራልና፡፡
\v 15 የአሕዛብ ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ በሰው እጅ የተሠሩ ናቸው
\v 16 አፍ አላቸው አይናገሩም ዐይን አላቸው አያዩም፡፡
\v 17 ጆሮ አላቸው አይሰሙም፤ በአፋቸውም እስትንፋስ የለም፡፡
\v 18 የሚሠሩዋቸውና የሚታመኑባቸው ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ፡፡
\s5
\v 19 የእስራኤል ልጆች ሆይ፣ ያህዌን ባርኩ የአሮን ልጆች ሆይ፣ ያህዌን ባርኩ፡፡
\v 20 የሌዊ ልጆች ሆይ፣ ያህዌን ባርኩ ያህዌን የምትፈሩ ሆይ፣ ያህዌን ባርኩ፡፡
\v 21 በኢየሩሳሌም የሚኖር ያህዌ ከጽዮን ይባረክ ያህዌን አመስግኑ፡፡
\s5
\c 136
\p
\v 1 ቸር ነውና ያህዌን አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 2 የአማልክትን አምላክ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 3 የጌቶችን ጌታ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\s5
\v 4 ብቻውን ታላላቅ ተአምራት ያደረገውን አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 5 በጥበብ ሰማያትን የሠራ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\s5
\v 6 ምድርን ውሃ ላይ የዘረጋ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 7 ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\s5
\v 8 ፀሐይ በቀን እንዲገዛ ያደረገ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 9 ጨረቃና ከዋክብት ሌሊት እንዲገዙ ያደረገ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\s5
\v 10 የግብፅን በኩር የገደለ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 11 እስራኤልን ከመካከላቸው ያወጣ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 12 በብርቱ እጅ፣ በተዘረጋችም ክንድ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\s5
\v 13 ቀይ ባሕርን የከፈለውን አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 14 እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 15 ፈርዖንና ሰራዊቱን ቀይ ባሕር ውስጥ ያሰጠመ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\s5
\v 16 ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራውን አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 17 ታላላቅ ነገሥታትን የገደለውን ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\s5
\v 18 ኃያላን ነገሥታትን የገደለ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 19 የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎንን ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 20 የባሳንን ንጉሥ ዐግን የገደለ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\s5
\v 21 ምድራቸውን ርስት አድርጐ የሰጠ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 22 ለባርያው ለእስራኤል ርስት አድርጐ የሰጠ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 23 በውርደታች ያሰበን፣ የረዳንም ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\s5
\v 24 በጠላቶቻችን ላይ ድል የሰጠን ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 25 ለፍጡር ሁሉ ምግብ የሚሰጥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\v 26 የሰማይን አምላክ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
\s5
\c 137
\p
\v 1 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ ተቀምጠን ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን፡፡
\v 2 እዚያ በገናዎቻችንን በአኻያ ዛፎች ላይ ሰቀልን፡፡
\s5
\v 3 የማረኩን ሰዎች እንድንዘምርላቸው ጠየቁን ሲያፌዙብን የነበሩት የደስታ ዜማ ፈለጉብን፣ «እስቲ ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን» አሉን፡፡
\v 4 የያህዌን መዝሙር እንዴት ብለን በባዕድ ምድር እንዘምራለን?
\s5
\v 5 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ብረሳሽ ቀኝ እኔ ይክዳኝ፡፡
\v 6 አንቺን ሳላስታውስ፣ ደስ ከሚያሰኘኝ ነገር ሁሉ በላይ ሳላደርግሽ ብቀር ምላሴ ከትናጋዬ ትጣበቅ፡፡
\s5
\v 7 ያህዌ ሆይ፣ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን ኤዶማውያን ያደረጉትን አስብ፡፡ እነርሱ፣ «አፍርሷት፣ ጨርሳችሁ አፍርሷት!» አሉ፡፡
\s5
\v 8 የባቢሎን ልጅ ሆይ፣ እኛ ላይ ስላደረግሺው ድርጊት ብዙም ሳይቆይ፣ የእጅሽን የሚሰጥሽ የተባረከ ነው
\v 9 ሕፃናቶችሽን ዐለት ላይ የሚፈጠፍጥ እርሱ የተመሰገነ ነው፡፡
\s5
\c 138
\p
\v 1 በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ በአማልክትም ፊት በመዝሙር እወድስሃለሁ፡፡
\v 2 ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ ስለ ምሕረትህና ስለ ታማኝነትህ ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ ቃልህንና ስምህን ከሁሉ በላይ ከፍ አደረግህ፡፡
\s5
\v 3 በጠራሁህ ቀን መለስህልኝ ነፍሴን በማጽናናት አደፋፈርሃት፡፡
\v 4 ያህዌ ሆይ፣ የአፍህን ቃል ሲሰሙ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል፡፡
\s5
\v 5 የያህዌ ክብር ታላቅ ነውና ስለ ያህዌ ሥራ ይዘምራሉ፡፡
\v 6 ያህዌ እጅግ ከፍ ያለ ቢሆንም፣ ዝቅ ያሉትንም ይመለከታል ትዕቢተኞችን ግን ገና ከሩቅ ያውቃቸዋል፡፡
\s5
\v 7 በአደጋ መካከል ብሄድ እንኳ አንተ ሕይወቴን ትጠብቃለህ፡፡ እጅህን ዘርግተህ ከጠላቶቼ ቁጣ ታወጣኛለህ በቀኝ እጅህም ታድነኛለህ፡፡
\v 8 ያህዌ እስከ መጨረሻ ከእኔ ጋር ነህ ያህዌ ሆይ፣ ምሕረትህ ለዘላለም ነው፡፡ የእጅህን ሥራ ቸል አትበል፡፡
\s5
\c 139
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ መረመርኸኝ፤ ደግሞም ዐወቅኸኝ፡፡
\v 2 አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ የልቤንም ሐሳብ ገና ከሩቅ ትረዳለህ፡፡
\s5
\v 3 መሄድ መተኛቴን በሚገባ ታውቃለህ መንገዶቼንም ሁሉ ዐውቀሃቸዋል
\v 4 ገና ቃል ከአንደበቴ ሳይወጣ ያህዌ ሆይ፣ ፈጽመህ ታውቃለህ፡፡
\v 5 አንተ ከኋላም ከፊትም ዙሪያዬን ከለልኸኝ እጅህንም በላዬ አደረግህ፡፡
\v 6 እንዲህ ያለው ዕውቀት እጅግ ጥልቅ ነው ከእኔም ማስተዋል በላይ ነው፡፡
\s5
\v 7 ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ፡፡
\v 8 ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ መኝታዬን በሲኦል ባደርግ በዚያ ትገኛለህ፡፡
\s5
\v 9 በንጋት ክንፍ ተነሥቼ ብበር እስከ ባሕሩ መጨረሻ ብሄድ
\v 10 በዚያም ቢሆን እጅህ ትመራኛለች ቀኝ እጅህም ትይዘኛለች፡፡
\s5
\v 11 ደግሞም፣ «ጨለማው በእርግጥ ይሸፍነኛል በዙሪያዬ ያለውም ብርሃን ሌሊት ይሆናል» ብል
\v 12 ጨለማ እንኳ ለአንተ አይጨልምም ሌሊቱም እንደ ቀን ያበራል በአንተ ጨለማም ሆነ ብርሃን አንድ ናቸው፡፡
\s5
\v 13 አንተ የውስጥ ሰውነቴን ፈጥረሃል በእናቴ ማሕፀን ውስጥ አበጃጅተህ ሠራኸኝ፡፡
\v 14 ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ ሥራህ እጅግ ድንቅ ነው ነፍሴም ይህን በሚገባ ታውቃለች፡፡
\s5
\v 15 እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ ዐጥንቶቼ ከአንተ አልተደበቁም፡፡ በምድር ጥልቅ ውስጥ በጥበብ በተሠራሁ ጊዜ
\v 16 በእናቴ ማሕፀን እያለሁ አየኸኝ፡፡ ገና አንዳቸውም ወደ መኖር ሳይመጡ ለእኔ የተወሰኑልኝ ዘመኖች በመጽሐፍህ ተጻፉ፡፡
\s5
\v 17 አምላኬ ሆይ፣ ለእኔ ያለህ ሐሳብ እንዴት ግሩም ነው! ቁጥሩስ ምንኛ የበዛ ነው!
\v 18 ልቁጠራቸው ብል ከአሸዋ ቁጥር ይበልጣሉ ተኛሁ ነቃሁም፤ ያም ሆኖ ግን አሁንም ከአንተው ጋር ነኝ፡፡
\s5
\v 19 አምላክ ሆይ፣ ክፉዎችን ብትገድላቸው ምናለበት! ደም የጠማችሁ ዐመፀኞች ከእኔ ራቁ፡፡
\v 20 እነርሱ በአንተም ላይ ክፉ ይናገራሉ በጠላትነትም ስምህን በክፉ ያጠፋሉ፡፡
\s5
\v 21 ያህዌ ሆይ፣ የሚጠሉህን አልጠላሁምን? በአንተ ላይ የሚነሡትንስ አልተጸየፍሁምን?
\v 22 በፍጹም ጥላቻ ጠልቻቸዋለሁ እነርሱም ባላጋራዎቼ ሆነዋል፡፡
\s5
\v 23 እግዚአብሔር ሆይ፣ መርምረኝ ልቤንም ዕወቅ ፈትነኝ ሐሳቤንም ዕወቅ፡፡
\v 24 በእኔ ውስጥ የዐመፅ መንገድ ቢኖር እይ በዘላለምም መንገድ ምራኝ፡፡
\s5
\c 140
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ከክፉ ሰዎች አድነኝ ከዐመፀኞችም ጠብቀኝ፡፡
\v 2 እነርሱ በልባቸው ክፉ ነገር ያውጠነጥናሉ በየዕለቱም ጦርነት ይጭራሉ፡፡
\v 3 ምላሳቸው እንደ እባብ ይነድፋል የእፉኝትም መርዝ በከንፈራቸው አለ፡፡ ሴላ
\s5
\v 4 ያህዌ ሆይ፣ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ መትተው ሊጥሉኝ ከሚፈልጉ ዐመፀኛ ሰዎች አድነኝ፡፡
\v 5 ትዕቢተኞች በስውር ወጥመድ ዘርግተውብኛል የመረባቸውን ገመድ ዘረጉብኝ በመንገዴም አሽክላ አኖሩ፡፡ ሴላ
\s5
\v 6 እኔም ያህዌን፣ «አንተ አምላኬ ነህ እንድትምረኝ የማቀርበውን ጩኸት ስማ» እለዋለሁ፡፡
\v 7 ያህዌ ሆይ፣ እኔን ለማዳን ብርቱ ነህ በጦርነት ቀን ራሴን ከለልህ፡፡
\v 8 ያህዌ ሆይ፣ የክፉዎች ምኞት አይሳካ ሤራቸውም አይከናወን፡፡
\s5
\v 9 ዙሪያዬን የከበቡኝ ራሳቸውን ቀና ቀና አደረጉ የገዛ ከንፈራቸው ሸፍጥ ይዋጣቸው፡፡
\v 10 የእሳት ፍም በላያቸው ይውረድ እሳት ውስጥ ጣላቸው ዳግመኛም እንዳይነሡ ማጥ ወዳለበት ጉድጓድ ይውደቁ፡፡
\v 11 ምላሰኛ በምድሪቱ ጸንቶ አይኑር ዐመፀኛውን ክፋት አሳድዶ ያጥፋውቨ
\s5
\v 12 ያህዌ ለተበደሉ እንደሚፈርድ ለችግረኛውም ፍትሕ እንደሚሰጥ ዐውቃለሁ፡፡
\v 13 ጻድቃን በእውነት ስምህን ያመሰግናሉ ቅኖችም በፊትህ ይኖራሉ፡፡
\s5
\c 141
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ወደ አንተ እጣራለሁ ፈጥነህ ድረስልኝ ወደ አንተ ስጣራ ድምፄን ስማ
\v 2 ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን ይሁንልኝ ወደ አንተ ያነሣሁት እጄም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ይቆጠርልኝ፡፡
\s5
\v 3 ያህዌ ሆይ፣ ለአፌ ጠባቂ አኑር የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ
\v 4 ክፉ ለማድረግ ከመመኘትና ከክፉ አድራጊዎች ጋር ከመተባበር፣ የድግሳቸውም ተካፋይ ከመሆን ጠብቀኝ፡፡
\s5
\v 5 ጻድቅ ሰው ቢቀጣኝ ለእኔ በጐነት ነው፤ እርሱ ቢገሥጸኝ ራሴን እንደሚቀባ ዘይት ነው እኔ ራሴም ይህን እንቢ አልልም፡፡ ጸሎቴ ግን ሁሌም በክፉዎች ተግባር ላይ ነው፡፡
\v 6 መሪዎቻቸው ከገደል ጫፍ ቁልቁል ይወርወሩ ቃሌ እውነት መሆኗንም ይሰማሉ፡፡
\v 7 ደግሞም፣ «ሰው ምድርን እንደሚያርስና ዐፈሩን እንደሚፈረካክስ፣ እንዲሁ ዐጥንታችን በሲኦል አፋፍ ላይ ተበታተነ» ይላሉ፡፡
\s5
\v 8 ጌታ፣ ያህዌ ሆይ፣ ዐይኖቼ ወደ አንተ ይመለከታሉ መጠጊያዬ አንተ ነህ፤ ከእንግዲህ ነፍሴን አትተዋት፡፡
\v 9 ከዘረጉብኝ ወጥመድ ከክፉ አድራጊዎችም አሽክላ ጠብቀኝ፡፡
\v 10 እኔ በደኅና ሳመልጥ ክፉዎች በገዛ ወጥመዳቸው ይውደቁ፡፡
\s5
\c 142
\p
\v 1 ድምፄን ከፍ አድርጌ እንዲረዳኝ ወደ ያህዌ እጮኻለሁ ድምፄን ከፍ አድርጌ እንዲምረኝ ልመናየን ወደ ያህዌ አቀርባለሁ፡፡
\v 2 ብሶቴን በፊቱ አፈስሳለሁ ችግሬንም እነግረዋለሁ፡፡
\s5
\v 3 መንፈሴ በውስጤ ሲዝል አንተ መንገዴን ታውቃለህ፤ መተላለፊያ መንገዴ ላይ በስውር ወጥመድ ዘረጉብኝ፡፡
\v 4 ወደ ቀኜ ብመለከት የሚያስብልኝ ሰው አጣሁ ማምለጫም የለኝም ለሕይወቴም ደንታ ያለው የለም፡፡
\v 5 ያህዌ ሆይ፣ ወደ አንተ እጮኻለሁ «አንተ መጠጊያዬ ነህ በሕያዋን ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ» እላለሁ፡፡
\s5
\v 6 እጅግ ተስፋ ቆርጫለሁና ጩኸቴን ስማ ከእኔ ይበልጥ ብርቱ ስለሆኑ ከአሳዶጆቼ አድነኝ፡፡
\v 7 ስምህን እንዳመሰግን ነፍሴን ከእስር ቤት አውጣት፡፡ ለእኔ ያደረግኸውን መልካም ነገር ሲመለከቱ ጻድቃን በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ፡፡
\s5
\c 143
\p
\v 1 ያህዌ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ ልመናዬንም አድምጥ፡፡ በታማኝነትህና በጽድቅህ ሰምተህ መልስልኝ፡፡
\v 2 በአንተ ፊት ማንም ጻድቅ አይደለምና ከባርያህ ጋር ወደ ፍርድ አትግባ፡፡
\s5
\v 3 ጠላት ነፍሴን አሳደዳት ገፍትሮም ወደ መሬት ጣለኝ፡፡ ቀደም ብለው እንደ ሞቱ ሰዎች በጨለማ ውስጥ አኑሮኛል፡፡
\v 4 ስለዚህ መንፈሴ በውስጤ ልቤም ተስፋ ቆረጠ፡፡
\s5
\v 5 የቀድሞውን ዘመን አስታወስሁ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ አንተ ያደረግኸውንም አውጠነጠንሁ፡፡
\v 6 በጸሎት እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ እንደ ደረቀች ምድር ነፍሴ አንተን ተጠማች፡፡ ሴላ
\s5
\v 7 ያህዌ ሆይ፣ መንፈሴ ዝሎአልና ፈጥነህ ስማኝ፡፡ ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ እንዳልሆን ፊትህንም ከእኔ አትሰውር፡፡
\v 8 በአንተ ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፡፡ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ፡፡
\s5
\v 9 ያህዌ ሆይ፣ አንተን መሸሸጊያ አድርጌአለሁና ከጠላቶቼ አድነኝ፡፡
\v 10 አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ማድረግ አስተምረኝ፡፡ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ፡፡
\s5
\v 11 ያህዌ ሆይ፣ ስለ ስምህ በሕይወት ጠብቀኝ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት፡፡
\v 12 ከታማኝነትሀ የተነሣ ጠላቶቼን አጥፋቸው እኔ ባርያህ ነንና የሕይወቴን ጠላቶች ደምስሳቸው፡፡
\s5
\c 144
\p
\v 1 እጆቼን ለጦርነት ጣቶቼንም ለውጊያ የሚያሠለጥን ዐለቴ ያህዌ ይባረክ፡፡
\v 2 አንተ መታመኛዬና መጠጊያዬ ነህ ጽኑ ዐምባዬና ታዳጊዬ የምከለልበት ጋሻዬም ነህ ሕዝቦችን ከእግሬ በታች የምታስገዛልኝም አንተ ነህ፡፡
\s5
\v 3 ያህዌ ሆይ፣ ይህን ያህል የምትንከባከበው ሰው ምን ስለሆነ ነው? ይህን ያህል የምታስብለት የሰው ልጅስ ምንድነው?
\v 4 ሰው እንደ እስትንፋስ ነው ዘመኑም እንደ ጥላ ያልፋል፡፡
\s5
\v 5 ያህዌ ሆይ፣ ሰማያትን ሰንጥቀህ ውረድ ይጤሱም ዘንድ ተራሮችን ዳስሳቸው፡፡
\v 6 የመብረቅ ብልጭታ ልከህ ጠላቶቼን በትናቸው ፍላጻህን ሰድደህ ግራ አጋባቸው፡፡
\s5
\v 7 ከላይ እጅህን ሰደህ ከብዙ ውሆች፣ ከባዕድ ሰዎችም እጅ ታደገኝ፡፡
\v 8 አንደበታቸው ሐሰት ይናገራል ቀኝ እጃቸውም የቅጥፈት ቀኝ እጅ ናት፡፡
\s5
\v 9 አምላክ ሆይ፣ አዲስ መዝሙር እዘምርልሃለሁ ዐሥር አውታር ባለው በገና ምስጋና አቀርብልሃለሁ፡፡
\v 10 አንተ ነገሥታትን ድልን ታጐናጽፋቸዋለህ አገልጋይህ ዳዊትንም ከስለታም ሰይፍ ትታደገዋለህ፡፡
\v 11 አንደበታቸው ሐሰት ከሚናገር ቀኝ እጃቸው የቅጥፈት ቀኝ እጅ ከሆነችው ከባዕዳን እጅ ታደገኝ፡፡
\s5
\v 12 ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው የተሟላ ዕድገት እንዳገኘ ተክል ሴቶች ልጆቻችንም ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ እንደ ተቀረጹ የማእዘን ዐምዶች ይሁኑ፡፡
\v 13 ጐተራዎቻችን በተለያዩ የእህል ዐይነቶች የተሞሉ ይሁኑ፡፡ በመስኮቻችን የተሰማሩ በጐች እስከ ሺህ ይወለዱ፣ እስከ ዐሥር ሺህ ይባዙ፡፡
\s5
\v 14 ከብቶቻችን ወላድ ይሁኑ፡፡ አይጨንግፉ አይጥፉ ቅሮቻችን በማንም አይደፈሩ እኛም በምርኮ አንወሰድ፡፡ በአደባባዮቻችን ጩኸት አይሰማ፡፡
\v 15 እንዲህ የሚሆንለት ሕዝብ የተባረከ ነው ያህዌ አምላኩ የሆነለት ሕዝብ የተባረከ ነው፡፡
\s5
\c 145
\p
\v 1 አምላኬና ንጉሤ ሆይ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ስምህንም ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ፡፡
\v 2 በየቀኑ እባርክሃለሁ ስምህንም ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ፡፡
\v 3 ያህዌ ምስጋናው ታላቅ ነው ታላቅነቱም አይመረመርም፡፡
\s5
\v 4 አንዱ ትውልድ ለቀጣዩ ትውልድ ሥራህን ያስተላልፋል ድቅ ሥራህንም ያውጃል፡፡
\v 5 የክብርህን ግርማ፣ የሥራህንም አስደናቂነት አሰላስላለሁ፡፡
\s5
\v 6 ስለ ድንቅ ሥራህ ኃይል ይናገራሉ እኔም ታላቅነትህን ዐውጃለሁ፡፡
\v 7 የበጐነትህን ብዛት ያወሳሉ ስለ ጽድቅህም ይዘምራሉ፡፡
\s5
\v 8 ያህዌ ቸር ነው፤ ርኅሩኅም ነው ለቁጣ የዘገየ ምሕረቱም የበዛ ነው፡፡
\v 9 ያህዌ ለሁሉም ቸር ነው ምሕረቱም በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ነው፡፡
\s5
\v 10 ያህዌ ሆይ፣ ፍጥረቶችህ ሁሉ ያመሰግኑሃል ቅዱሳንህም ይባርኩሃል፡፡
\v 11 ቅዱሳንህ የመንግሥትህን ክብር ይናገራሉ ስለ ኃይልህምይነጋገራሉ፡፡
\v 12 የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ለሰው ልጆች ያሳውቃሉ የመንግሥቱንም ክብር ይናገራሉ፡፡
\s5
\v 13 መንግሥትህ የዘላለም መግሥት ነው ግዛትህም ለትውልድ ሁሉ ጸንቶ ይኖራል፡፡
\s5
\v 14 ያህዌ የሚንገዳገዱትን ሁሉ ይደግፋል የወደቁትንም ሁሉ ያነሣል፡፡
\v 15 የሁሉም ዐይን አንተን በተስፋ ይጠብቃል በተገቢ ጊዜ ምግባቸውን ትሰጣቸዋለህ፡፡
\v 16 እጅህን ትዘረጋለህ የሕያዋንን ሁሉ ፍላጐት ታረካለህ፡፡
\s5
\v 17 ያህዌ በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው በሥራውም ሁሉ ቸር ነው፡፡
\v 18 ያህዌ ለሚጠሩት ሁሉ በእምነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፡፡
\v 19 የሚፈሩትን ፍላጐት ይፈጽማል ጩኸታቸውንም ሰምቶ ያድናቸዋል፡፡
\s5
\v 20 ያህዌ የሚወዱትን ይጠብቃል ዐመፀኞችን ሁሉ ግን ያጠፋል፡፡
\v 21 አፌ የያህዌን ምስጋና ይናገራል የሰው ልጅ ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ቅዱስ ስሙን ይባርክ፡፡
\s5
\c 146
\p
\v 1 ያህዌን አመስግኑ ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን ባርኪ፡፡
\v 2 በሕይወት በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለያህዌ እዘምራለሁ፡፡
\s5
\v 3 በገዦች አትተማመኑ ማዳን በማይችል የሰው ልጅም አትመኩ፡፡
\v 4 የሰው እስትንፋስ ሲያቆም ወደ መሬት ይመለሳል፡፡ ያን ጊዜ ዕቅዱ እንዳልነበረ ይሆናል፡፡
\s5
\v 5 ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ ተስፋውም ያህዌ የሆነለት ሰው የተባረከ ነው፡፡
\v 6 ሰማይና ምድርን፣ ባሕርንና በውስጡ ያሉትንም የፈጠረ ያህዌ
\s5
\v 7 ለተጨቆኑት የሚፈርድ፣ ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፡፡ ያህዌ እስረኞችን ነጻ ያወጣል፡፡
\v 8 ያህዌ የዕውራን ዐይን ይከፍታል፡፡ ያህዌ የተዋረዱን ከፍ ያደርጋል፡፡ ያህዌ ጻድቃንን ይወዳል፡፡
\s5
\v 9 ያህዌ መጻተኞን በምድር ይጠብቃል ደኸ አደጐችንና መበለቶችን ይደግፋል፡፡ የክፉዎችን መንገድ ግን ያጠፋል፡፡
\v 10 ያህዌ ለዘላለም ይነግሣል ጽዮን ሆይ፣ አምላክሽ ለትውልድ ሁሉ ንጉሥ ነው፡፡ ያህዌ ይመስገን፡፡
\s5
\c 147
\p
\v 1 ያህዌ ይመስገን አምላካችንን በመዝሙር ማመስገን እንዴት መልካም ነው እርሱን ማመስገን ደስ ያሰኛል፤ ተገቢም ነው፡፡
\s5
\v 2 ያህዌ ኢየሩሳሌምን መልሶ ይሠራታል የተበተነውን የእስራኤል ሕዝብ ይሰበስባል፡፡
\v 3 ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል ቁስላቸውንም ይጠግናል፡፡
\s5
\v 4 ከዋክብቱን ይቆጥራል ለእያንዳንዳቸውም ስም ይሰጣቸዋል፡፡
\v 5 ጌታችን ታላቅ፣ ኃይሉን የሚያስፈራ ነው ማስተዋሉም አይመረመርም፡፡
\s5
\v 6 ያህዌ የተጨቆኑትን ያነሣል ክፉዎችን ግን ወደ ምድር ይጥላል፡፡
\v 7 ለያህዌ በምስጋና ዘምሩ ለአምላካችን በበገና ዘምሩ፡፡
\s5
\v 8 ሰማያትን በደመና ይሸፍናል በተራሮች ሣር እንዲበቅል ለምድር ዝናብ ያዘጋጃል፡፡
\v 9 ለእንስሳት ምግባቸውን፣ የቁራ ጫጩቶች ሲንጫጩ ምግባቸውን ይሰጣቸዋል፡፡
\s5
\v 10 በፈረስ ኃይል አይደሰትም ደስታውን በሰው ጉልበት ጥንካሬ አያደርግም፡፡
\v 11 ያህዌ በሚፈሩት፣ በምሕረቱም በሚታመኑ ይደሰታል፡፡
\s5
\v 12 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ያህዌን አመስግኚ ጽዮንም አምላክሽን አወድሺ
\v 13 እርሱ የበሮችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና በመካከልሽ ያሉ ልጆችሽንም ባርኮአል፡፡
\v 14 በድንበርሽ ውስጥ ብልጽግና አድርጐአል ማለፊያ ስንዴም ያጠግብሻል፡፡
\s5
\v 15 ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል ቃሉም በፍጥነት ይሮጣል፡፡
\v 16 በረዶውን እንደ ባዘቶ ያነጥፈዋል ጭጋጉንም እንደ ደመና ይበትነዋል፡፡
\s5
\v 17 የበረዶውን ድንጋይ ቁልቁል ይለቃል በውሽንፍሩስ ቅዝቃዜ ፊት ማን መቆም ይችላል?
\v 18 ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል ነፋሱን ያነፍሳል ውሃንም ያፈስሳል፡፡
\s5
\v 19 ቃሉን ለያዕቆብ፣ ሥርዐት ጽድቁንም ለእስራኤል ያውጃል፡፡
\v 20 ለማንኛውም ሌላ ሕዝብ ይህን አላደረገም እነርሱም ፍርዱን አላወቁም፡፡ ያህዌ ይመስገን፡፡
\s5
\c 148
\p
\v 1 ያህዌን አመስግኑ በሰማያት ያላችሁ ያህዌን አመስግኑ በከፍታዎች ያላችሁ ያህዌን አመስግኑ፡፡
\v 2 መላእክቱ ሁሉ አመስግኑ የመላእክቱ ሰራዊት ሁሉ አመስግት፡፡
\s5
\v 3 ፀሐይና ጨረቃ አመስግት የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት፡፡
\v 4 ሰማየ ሰማያት አመስግኑት ከሰማይ በላይ ያላችሁ ውሆች አመስግኑት፡፡
\s5
\v 5 እርሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና የያህዌን ስም ያመስግኑ፡፡
\v 6 ከዘላለም እስከ ዘላለም አጸናቸው የማይሻር ሕግም ደነገገላቸው፡፡
\s5
\v 7 የባሕር ውስጥ ፍጥረትና ጥልቁ ውሃ ሁሉ ያህዌን ከምድር አመስግኑት፡፡
\v 8 እሳትና በረዶ ዐመዳይና ጭጋግ ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ
\s5
\v 9 ተራሮችና ኮረብቶች፣ የፍሬ ዛፎችና ዝግቦች ሁሉ አመስግኑ፡፡
\v 10 የዱር አራዊት፣ የቤት እንስሳት በምድር የሚርመሰመሱ ፍጥረቶችና ወፎችም ሁሉ
\s5
\v 11 የምድር ነገሥታትና ሕዝቦች ሁሉ መሳፍንቶችና የምድር ገዦች ሁሉ ያህዌን አመስግኑ፡፡
\v 12 ወጣት ወንዶችና ወጣት ሴቶች አረጋውያንና ሕፃናት ያመስግኑት፡፡
\s5
\v 13 የእርሱ ስም ብቻውን ከፍ ከፍ ብሎአልና ክብሩም ከምድርና ከሰማያት በላይ ነውና የያህዌን ስም ያመስግኑ፡፡
\v 14 እርሱ ለሕዝቡ ቀንድን አስነሥቶአል ለቅዱሳኑ ሁሉ ምስጋና፣ እጅግ ቅርቡ ለሆነው ሕዝቡ ለእስራኤል ልጆች፡፡ ያህዌን አመስግኑ፡፡
\s5
\c 149
\p
\v 1 ያህዌን አመስግኑ ለያህዌ አዲስ መዝሙር ዘምሩ
\s5
\v 2 በቅዱሳን ጉባኤ ምስጋናውን አቅርቡ፡፡ እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤት ያድርጉ፡፡
\v 3 ስሙን በሽብሸባ ያመስግኑ በከበሮና በመሰንቆ ይዘምሩለት፡፡
\s5
\v 4 ያህዌ በሕዝቡ ደስ ይለዋል በማዳኑ ትሑታንን ያከብራቸዋል፡፡
\v 5 ቅዱሳን በድል ደስ ይበላቸው በመኝታቸውም ላይ እልል ይበሉ፡፡
\s5
\v 6 የእግዚአብሔር ምስጋና በአንደበታቸው በሁለት ወገን የተሳለ ሰይፍም በእጃቸው ይሁን፡፡
\v 7 ይህም በአሕዛብ ላይ በቀልን፣ በሕዝቦችም ላይ ፍርድን ያደርጉ ዘንድ
\s5
\v 8 ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት መሳፍንቶቻቸውንም በእግር ብረት ያስራሉ፡፡
\v 9 ይህም በእነርሱ ላይ የተጻፈውን ፍርድ ለመፈጸም ነው፡፡ ይህ ለቅዱሳኑ ሁሉ ክብር ይሆናል፡፡ ያህዌን አመስግኑ፡፡
\s5
\c 150
\p
\v 1 ያህዌን አመስግኑ እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት
\v 2 ስለ ብርቱ ሥራው አመስግኑት ከአእምሮ በላይ ስለሆነው ታላቅነቱ አመስግኑት፡፡
\s5
\v 3 በመለከት ድምፅ አመስግኑት በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት፡፡
\v 4 በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑ በባለ አውታርና የእስትንፋስ መሣሪያ አመስግኑት፡፡
\v 5 ከፍ ያለ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል ወድሱት፡፡
\s5
\v 6 እስትንፋስ ለው ሁሉ ያህዌን ያመስግን፡፡ ያህዌን አመስግኑ፡፡